በዛሬው እለት በዚህ ሰአት ራቢን አደባባይ በሺዎች በሚቆጠሩ ስደተኞች ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ እያደረጉ መሆኑን የ እስራኤል የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው :: ስደተኞች የምንሄድበት የለም!! ሃገር የለንም!! የመኖር መብታችን ይከበር !!የሰባዊ መብታችን ይከበር!! ለስደተኞች እውቅና ይሰጥ !! የተዘጉ በሮች ይከፈቱ!! የሚሉ ሰልፈኞች አደባባዩን አጨናንቀውታል:: ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የ እስራኤል መንግስት በስደተኞች ላይ ያወጣውን ህገ መንግስት ካልሰረዘ ለ ሦስት ቀን ያህል የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በዚህ የስራ ማቆም አድማም ተጎጂዎች ሆቴሎች ሬስቶራንቶች እና የቴል -አቪቭ ከተማም ከ 2000 በላይ ስደተኛ ሰራተኞችን በተዘዋዋሪ ቀጥራ እንደምታሰራ የዘና ምንጮች ጠቅሰዋል።
No comments:
Post a Comment