ሰንደቅ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው፦
በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታርመሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችንጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስትብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነየመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎመታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉአስረድተዋል።
በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራርመሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።
የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለትይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤትየ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ምመጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።
በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞንጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብአይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልንእንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎችወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውንተናግረዋል።
በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብምስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታአቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ምጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11994
በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታርመሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችንጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስትብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነየመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎመታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉአስረድተዋል።
የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለትይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤትየ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ምመጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።
በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞንጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብአይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልንእንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎችወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውንተናግረዋል።
በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብምስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታአቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ምጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11994
No comments:
Post a Comment