Sunday, January 26, 2014

ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ ተገልብጦ 16 ሰዎች ሞቱ

ትናንት አመሻሽ ላይ ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ32 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ።
ከሟቾቹ ውስጥ ዘጠኙ ወንዶች ሲሆኑ ሰባቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።
ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ የ2 አመት ህጻን ያለ ምንም ጉዳት ተርፏል።
Buscaraccidentአደጋው የደረሰው በጌዲዮ ዞን በይርጋ ጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ ሲሆን ፥ ከፍተኛ ቁልቁለት ባለበት መንገድ ላይ በፍጥነት ማሽከርከር የአደጋው መንስኤ ነው የይርጋ ጨፌ ወረዳ የትራፊኮች አስተባባሪ ምክትል ሳጅን እድገት አምባዬ እንዳሉት።
ከዚህ በፊትም በዚህ ቦታ ላይ የተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች ይደርሱ እንደነበርም አስተባባሪው ገልጸዋል።
ተጎጂዎቹ በዲላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝና የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment