Imageአሁን በደረሰን መረጃ መሰረት .............
በዞኑ ጠንካራ የሚባሉትን ሁለት ልጆች የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ ወጨፎ አደሞ እና ታደመ ሞሃ የተባሉትን ወጣቶች ከትናንት ምሽት ጀምሮ መሳሪያ ትሸጣላችሁ በማለት አስረዉ ደብድበዋቸዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸዉንም ያስፈራሩ ሲሆን ፍተሻ በማድረግ ምንም ነገር ሊያገኙ ባለመቻላቸዉ ተመልሰዉ ሲደበድቧቸዉ እንዳመሹ ከስፍራዉ ላለዉ አባላችን ከዉስጥ ካሉ ሰዎች ሊታወቅ ችሏል፡፡ በድብደባዉ በተለይም ወጨፎ የተባለዉ በተክለ ሰዉነትም ጠንከር ያለ ወጣት ለአራት በመሆን ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዉበታል፡፡ ብልቱን ሳይቀር ክፉኛ እንደመቱት ምንጫችን አረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል ታስረዉ በሚገኙበት በወላይታ መርካቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘዉ ፖሊስ ጣቢያ ሰዎች እንዳይጠይቋቸዉ ተከልክሏል፡፡ በዚህ ሳያበቃም በአባላት ላይ የማስፈራራት ዘመቻ መከፈቱን እንዲሁም ሰሞኑን ፓርቲዉን በዞኑ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ፍላየሮችን ሲያድሉ የነበሩ ወጣቶችን
በተለያየ ቦታ እያፈኑ እያስፈራሩ እንደሆነ ታዉቋል፡፡