Sunday, November 24, 2013

ምልምል አርበኞችን አሰልጥኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/ አስመረቀ –




የኢሕአግ የስልጠና ማዕከል ለወራት ያህል ለምልምል አርበኞች ሲሰጥ የነበረው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና በህዳር 12-2006 ዓ/ም አጠናቋል። 
በህዳር 12-2006 ዓ/ም በተከናወነው የምልምል አርበኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት የኢሕ አግ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተው እንኳን ለምረቃው ዕለት አደረሳችሁ ካሉ በኋላ በጽናት የኢትዮጵያን ተጠቅሶ የማያልቅ ተግዳሮት መፍትሂ ለመሻትና አንድነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመገንባት በሚደረገው ትግል የሚሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት ከወዲሁ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠቁመዋል።

በስልጠናው የተሻለ ብቃት ላሳዩ ተመራቂዎችና ሴት ተመራቂዎች ከአመራሩ የማበረታቻ ሽልማት ተቀብለዋል ዝግጅቱም በድርጅታዊ መዝሙር ጀምሮ ሞቅ ደመቅ ባለና የጀግኖችን ተጋድሎ በሚገልጽ መልኩ በድራማ፣ በስነ-ጽሁፍ፣ ቀስቃሽ በሆኑ ዘፈኖች፣ ቀረርቶዎች፣ በውታደራዊ ሰልፍ ትርኢትና በመሳሰሉት ትዕይንቶች ታጅቦ ተከብሯል።

ስልጠናውን የተካፈሉ ምልምል አርበኞች ከምልምል አርበኝነት ወደ ሙሉ አርበኛ መሸጋገራቸው ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸው የድርጅቱ የስልጠና ማዕከል ያሰነቃቸው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና ቀድሞ ከነበራቸው የዕውቀትና የአካል ብቃት አንጻር የተሻለ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸው የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመቀየርና በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ሲንቀሳቀስ ባልታየው አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ላይየአገርና የወገን ችግር ፈች ኢትዮጵያዊ ተልዕኮ ለመወጣት ራሳቸውን በቆራጥነት መንፈስ እንዳዘጋጁ አስታውቀዋል። 

ተመራቂ አርበኞቹ አክለው እንዳብራሩት በተለይ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወገን እንደሌላቸው ሁሉ ታርደው በየጎዳናው መጣላቸው ሊታገሱት የማይችሉት አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ አስረግጠው ለዚሁ አጸፋ በእብሪተኛው ወያኔ ቡድን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የወገን ደራሽ መሆናችንን እናስመሰክራለን ሲሉ በቁጣ መልክ ግገልጸዋል። 

አንድነት ሃይል ነው!

Source : ኢሕአግ.



No comments:

Post a Comment