Thursday, November 28, 2013

ኢትዮጵያና ዩኤስ አሜሪካ በኬኔዲ ዘመን

ባለፈዉ ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት ዘክራ ዉላለች። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ ህዳር 22 ፤ 1963 ዓ,ም ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሰለባ የሆኑት ስልጣን ላይ ከወጤ ሶስተኛ ዓመታቸ ን ሊይዙ ትንሽ ወራቶች እንደቀራቸዉ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ።

selam
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ በዚያ ወቅት ከኢትዮጵያዉ ንጉሰነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ተመልክቶአል። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል። በለቱ ዝግጅታችን ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት፤ ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንቃኛለን ።
ዩናይትድ ስቴትስ በታጣቂ የተገደሉትን የሀገሪትዋን 35 ተኛ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ 50 ዓመት ዘክራ ዉላለች። በዚህ ቀን የሀገሪትዋ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ ተዉለብልቦአል። ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ በተገደሉበት ሃምሳኛ ዓመት በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ ልክ ከ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ ልዩ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ተነግሮአል። ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ካለፉት 50 ኛ ዓመታት ወዲህ እጅግ ተወዳጁ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት መሆናቸዉም ተዘግቦአል።
8u7
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ። በዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ የሆኑት የንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ ሳህለ ስላሴን በስልክ አግኝተን ጠይቀናቸዉ ነበር፤
የ 53 ዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ የልዑል ሳህለ ስላሴ እና የልዕተ ማህፀንተ ሃብተማርያም ብቸኛ ልጅ ናቸዉ። እንደ ልዑል ኤርምያስ፤ በጆኔፍ ኬኔዲ ዘመን ስልጣን፤ አንዳንድ ዘመናዊ ስልጣኔ ገብቶአል፤
በጆኔፍ ኬኔዲ የስልጣን ዘመን እድሜም የደረሰ ስለነበር ብዙ ነገሮችን አአስታዉሳለሁ ያሉን በተመድ 28 ዓመታት ያገለገሉት እና በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤ ቀደም ሲል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን ብዙ ግዜ ቢጎበኙም፤ እንደ ጆኔፍ ኬኔዲ በደማቅ አቀባበል አልተደረገላቸዉም ሲሉ ይገልጻሉ፤
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸዉን ኢትዮጵያ እንደተከታተሉ የሚገልፁት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ በኢንግሊዝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን በመቀጠል፤ በዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንደተከታተሉ ተጠቅሶአል። ልዑል ኤርምያስ ጃንሆይ ጆኔፍ ኬኔዲ ሊገደሉ አንድ ወር በፊት አሜሪካን እንደነበሩ ገልፀዉልናል።
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸዉን ኢትዮጵያ መከታተላቸዉ የተመለከተዉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ በኢንግሊዝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን በመቀጠል፤ በዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንደተከታተሉ ተጠቅሶአል። ልዑል ኤርምያስ ጃንሆይ ጆኔፍ ኬኔዲ ሊገደሉ አንድ ወር በፊት አሜሪካን እንደነበሩ እንዲህ ያስታዉሳሉ።
ቀድሞ በተመድ ሰራተኛ የነበሩት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤ በበኩላቸዉ ምንም እንኳ በዚያ ወቅት የጆን ኤፍ ኬኔዲ እና የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ወዳጅነት የጠነከረ ቢሆንም ቅሉ፤ ጃንሆይ ለሀገራቸዉ ያስፈልገኛል ያሉት ርዳታን ከአሜሪካ አላገኙም ሲሉ ተናግረዋል።
poi
ከአሜሪካዉያን ደስ ያለኝ ነገር፤ ያለፉትን የታሪክ ሰዎች ማስታወሳቸዉ ነዉ የሚሉት ልዑል ኤርምያስ ሳህለ ስላሴ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተገቢዉን ክብር እንዲሰጣቸዉ ምኞቴ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጀርመን ሀገርም እጅግ ተወዳጅ ናቸዉ። ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የዛሬ 50 ዓመት ምዕራብ በርሊንን በጎበኙበት ወቅት በጀርመንኛ ICH BIN EIN BERLINER „በርሊናዊ ነኝ“፤ነፃ ሰዎች ሁሉ የትም ይኑሩ የት የበርሊን ዜጎች ናቸው። እናም እንደ አንድ ነፃ ሰው ICH BIN EIN BERLINER „በርሊናዊ ነኝ“ ስል ኩራት ይሰማኛል ሲሉ በተናገሩት በዚህ አባባላቸው ዘወትር ይታወሳሉ።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ
ሊንኩን በመንት ዝርዝር ዘገባውን ያዳምቱ

No comments:

Post a Comment