Thursday, November 28, 2013

በቅርቡ ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርሲቲ በተነሳው ሁከት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት ምስል ይፋ ሆነ (18+) NOV 28,2013


22በሳውዲ አረቢያ ከእሳት ወደ ረመጥ ያመራው የወገኖቻችን ህይወት አሰቃቂ እና ዘግናኝ በሆኑ አደጋዎች ታጅቦ ግፍ እና መከራው ቀጥሏል::
በቅርቡ ሪያድ አሚራ ኑራ ዩነቨርስቲ በተነሳው ሁከት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት ምስል ይፋ ሆነ። ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም።
ኖቬብር 24 2013 ምሽት ሚን ዛህሚያ እይተባለ ከሚነገርለት ግዜያዊ መጠለያ «ወገን ማሰቃያ » ጣቢያ በ17 አውቶብስ ተጭነው ኤርፖርት እንወስዳችሃለን ተበልው ሪያድ ከተማ መለዝ እይተባለ ወደ ሚጠራ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ እንዳቀኑ በሚገርላቸው እገኖቻችን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር እህታችን አሰቃቂ ሞት ይፋ ሆነ ።
 በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወክለው ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደግቡ የሚነገርላቸው የልዑካን ቡድን አባላቶች ይህን የወገኖቻችንን ዘግናኝ አሟሟት በዓይናቸው አይተውት እንደነብር የሚናገሩ ምንጮች ህይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ላለፈቸው ነፍሰጡር ከማዘን ይልቅ ጉዳዩ ይፋ እንዳይወጣ አደጋው በተከሰተበት ወቅት ፎቶ ያነሱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን የቅረጹትን ይህን ምስል ለማንም አሳልፈው እንዳይሰጡ ያስፈሯሯቸው ነደነበር ገልጸዋል።
11በሳውድ አረኢያ ወገኖቻችን ላይ እይደረሰ ባለው አሰቃቂ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ከመቸውም ግዜ በላይ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ስለሚገኙ ድምጻቸውንን ከፍ አድርገን መጮህ ይጠበቅብናል ።

No comments:

Post a Comment