Friday, November 22, 2013

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ሀይለማሪያም, የትኛው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባ ነበር ????

pm haile
ጤና ባለው ፖለቲካ ቢሆን ኖሮ እዚህ ስልጣን ላይ የወጣ አካል መሸም ነጋም ለአገሩ ብሄራዊ ጥቅም፣ ለዜጎች መብትና ክብር መጨነቁ የግድ ነበር............
እናም ስልጣኑ ሳይሰጣቸው ባለስልጣን የመሰሉት አቶ ሀይለማሪያም ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ፣ ለኢትዮጵያውያን ሳይጨነቁ፣ ለኢትዮጵያውያን ሳይሰሩ ለአፍሪካውያን ለመቆም መሞከራቸው አስቂኝም፣አሳዛኝም፣ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን ሳያስቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን አይቻልም፡፡ ስለ ኢትዮጵያዊ በደልና ሰቆቃ ሳይናገሩ አፍሪካዊ መሆን አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያውያን  ስደትና መከራ ይህን ያህል ሳይጨነቁ ,ስለማይነካቸው የደቡብ አፍሪካ፣ የሞሪሺየስ፣ የሲሸልስ፣ የግብጽ…ዜጎች ከአፍሪካና የአረቡ ዓለም መልካም ግንኙነት የሚጠቀሙትን ለመተንተን፣ ለማስረዳት ሲቃጣቸው ......አሳዛኝ፣ ነው.!!!!
በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ አፍሪካዊ መሆን አይቻል ,ጠቅላይ ሚንስትርነት በስምም ቢሆን የአገሪቱ ስልጣን ሁሉ የበላይ ነ፡፡ዜጎቻችን ከአረቡ አናት ከሆነችው ሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች እየታረዱ የአረቡንና የአፍሪካን ግንኙነት ሲያወድሱ ሰንብተዋል፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ ቁስለትና ክብር መዋረድ አንድም ነገር ያልተነፈሱት ስለ አፍሪካውያን ዜጎች የወደፊት እጣ ፈንታ ደስኩረው ተመልሰዋል፡፡
  ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሙቀት በአፍሪካውያን ላይ ስለሚያመጣው ችግር በመናገር  ቻ ከኩየት ወደ ፖላንድ ያቀኑት  አቶ ሀይለማሪያም ተመልሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስት የእኛዎቹ ህዝቦች ሳውዲ ጎዳና ላይ በስለት እየሞቱ፣ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተደፈሩ    የአየር ንብረት ችግር  ሙቀት ስለሚያመጣው ችግር በመናገር  በአሁኑ ወቅት የትኛው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባ ነበር ????
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር  አቶ ሀይለማሪያም ,ስለ ኢትዮጵያውያን  ሳያስቡ ,ለአፍሪካውያን ለመቆም መሞከ አሳዛኝ፣ነው!!!!

No comments:

Post a Comment