Saturday, November 23, 2013

የወያኔ የግድያ እቅድ መክሸፍ ለሁመራና ወለወቃይት ጸገዴ ወጣቶች ችግር ፈጠረ

ፋሽስት ወያኔ ‘ወያኔ ኦ ሚሊኒየም’ ብሎ ሰይሞት የነበረውና በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌና የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አመራሮች ላይ የተጠነሰሰ የግድያ እቅድ ከከሸፈ ወዲህ ህዝባዊ ሃይሉ ይገኝበታል ተብለው በተጠረጠሩት አጎራባች ወረዳዎች በሚገኙ ወጣቶች ላይ የተጠናከረ አሰሳ በማድረግ ወጣቶችን በማሰር ላይ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ፋሽስት ወያኔ ልክ እንደቆሰለ አንበሳ እዚህም እዚያም በፍርሃት በመንደርደር በሁመራና በወልቃይት ጸገዴ የሚገኙ ወጣቶችን እያሰረ ይገኛል። ድርጊቱ ብዙዎችን እንዳሳሰበ የተገለጸ ሲሆን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ባካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ሕዝባዊ ሃይሉ እየገኘው ባለው ስምና ዝና ተስበው ሊቀላቀሉ ይችላሉ ብሎ የሰጋው ወያኔ ይህን የእስር ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ይጠቁማሉ።
ባካባቢው እያየው ባለው ነባራዊ ሂዎት ያልተደሰተው ወጣት፣ የነገ ተስፋየ ምንድን ነው ብሎ መልስ ያጣው ወጣት፣ ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ ቀስ በቀስ እየሞተ መሆኑን የተረዳው ወጣት እንኳን ከተጠናከረ ድርጅት ጋር መቀላቀል ይቅርና በራሱም ጠንካራ የተቃውሞ ድርጅት ሊያቃቁም ይችላል የሚሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ “የህ አይነቱ የፋሽስት ወያኔ ድርጊት ወጣቱን የበለጠ ተቃዋሚ ያደርገዋል እንጂ አያለዝበውም”። ለዚህም ነው ባሁኑ ሰአት ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጋይ እየጎረፈለት መሆኑ የሚሰማው ይላሉ። ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ፋሽስት ወያኔን በማስወገድ ሕዝቦቿ በመከባበር የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገውን ሂደት ለማገዝ በትጥቅ ትግል ወያኔን ለመፋለም ዝግጅት እያደረገ ያለ የተቃውሞ ድርጅት ነው።

No comments:

Post a Comment