To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Thursday, September 5, 2013
በረከት ስምኦን ማነው??? እውነተኛው በረከት ስምኦን አሁንም በህይወት ፓሪስ ይገኛል።
የበረከት የልጅነት ስም ከእነአባቱ፣ “መብራህቱ ገብረህይወት” ይባላል። ወደ ትግል ከወጣ በሁዋላ ስሙን “በረከት ስምኦን” ሲል ቀየረው። ስሙን ከእነ አባቱ ለምን እንደቀየረው ብዙ ሰዎችአያውቁም። በትግሉ ጊዜ ስምህን እንጂ የአባትህን መቀየር የተለመደ አልነበረም። ለምሳሌ መለስ፣ ስብሃት፣ ስዬ፣ ሳሞራ፣ ሃየሎም፣ ህላዌ፣ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል። ስማቸውን እንጂ የአባታቸውን ስም አልቀየሩም። ምክንያቱም ስም መለወጥ ያስፈለገው ለቤተሰባቸው ደህንነት ሲባል ብቻ ነበር። የአባት ስም ለመለወጥ ምክንያት አልነበረውም። እንዲያውም ብዙዎቹ ደርግ ከወደቀ በሁዋላ ወደ ልጅነት ስማቸው ተመልሰዋል። በረከት ከእነዚህ ሁሉ ተለይቶ ስሙን ብቻ ሳይሆን የአባቱንም ስም ቀየረ። በዚያውም ፀና። የአባትህን ስም ለመቀየር የግድ አንድ ምክንያት መኖር አለበት። ምናልባት አባትህን የምትጠላ ከሆነ፣ ዲቃላ ሆነህ በእንጀራ አባትህ የምትጠራ ከሆነ፣ የመሳሰሉ ምክንያቶች በረከት ስምኦን ማነው??? እውነተኛው በረከት ስምኦን አሁንም በህይወት ፓሪስ ይገኛል።
የአባትህን ስም ሊያስቀይሩ ይችላሉ። ስትቀይርም የእውነተኛ አባትህን ስም ታደርጋለህ። ወይም አባትህ ስሙ የማይታወቅ ከሆነ የእናትህን አባት ስም ልታደርግ ትችላለህ። አሊያም ደግሞ እንደ በአሉ ግርማ በአሳደገህ ሰው ስም ልትጠራ ትችላለህ። ይሄ ተለመደ ነው። በቅርብ እንደማውቀው በረከት ወላጅ አባቱን በጣም ያከብራል፣ ይወዳልም። በጎን የተወለደም አይደለም። መልኩም አባቱን ነው የሚመስለው። ወላጅ አባቱ አቦይ ገብረህይወት ባህላዊ መሃንዲስ ነበሩ። በጎንደር ዙሪያ የሚገኙ ቤተክርስትያናትን በአብዛኛው የገነቡት እሳቸው ናቸው። ቤተሰባቸውን አጥብቀው የሚወዱ፣ ልጆቻቸውን ለመስተማር እና ጥሩ ደረጃ ለማድረስ የደከሙ አባት ነበሩ። እና ታዲያ በረከት ስምኦን እንዲህ ያሉ ድንቅ አባቱን ከስሙ ላይ ፍቆ ለመጣል ለምን ወሰነ? ታሪኩ አስቂኝ ነው… በረከት ስምኦን የሚባል የኢህአፓ ታጋይ ነበር። አዲሳባ ተወልዶ ያደገ፣ ሊሴ ገብረማርያም የተማረ ኤርትራዊ ነው። በትግሉ ወቅት ይህ ልጅ ባልታወቀ ምክንያት ከትግሉ ሜዳ ተሰወረ። ድንገት ስለተሰወረ ብዙዎች የኢህአፓ አባላት በረከት ስምኦን የተሰዋ መሰላቸው። በዚህ ጊዜ መብራህቱ ገብረህይወት በረከት ስምኦን የተባለውን የተሰዋ የትግል ጓዱን ለማስታወስ ስሙን በስሙ ሰየማት። እናም በረከት ስምኦን እየተባለ መጠራት ጀመረ።6/15/13 በረከት ስምኦን ማነው???እውነተኛው በረከት ስምኦን አሁንም በህይወት ፓሪስ ይገኛል።
የሚያስገርመው ታሪክ ግን እውነተኛው በረከት ስምኦን አልተሰዋም ነበር። እውነተኛው በረከት ስምኦን አሁንም በህይወት ፓሪስ ይገኛል። በህይወት እያለ፣ በጠራራ ፀሃይ ስሙ በመዘረፉ በጣም እንደሚበሳጭም ሰምቻለሁ። እውነተኛው በረከት፣ ሩት እና ሃና የተባሉ እህቶች አሉት። ሃና ስምኦን ፓሪስ ላይ የኤርትራ አምባሳደር ነበረች። አሁን የት እንዳለች አላውቅም። ሩት ስምኦን የሻእቢያ ታጋይ እና ጋዜጠኛ ስትሆን፣ አስመራ ትገኛለች። ባልተሰዋ ሰው ስም፣ በአላማ በማይገናኙ ሰው ስም፣ ራሱን የሚጠራው ታሪከኛው መብራህቱ አማራ ሳይሆን አማራ ነኝ ይላል፣ በረከት ስምኦን ሳይሆን በረከት ስምኦን ነኝ ይላል። ይሄ ሰውዬ መቼ ነው እራሱን የሚሆነው? ጤነኛ የሆነ ሰው የራሱን ስም ሙሉ በሙሉ ሰርዞ፣ ያልሞተን ሰው ስም ከእነ አባቱ እንዴት ይዘርፋል? (እውነተኛው በረከት፣ ፎቶኮፒውን በረከት በመክሰስ ስሙን ማስመለስ ይችላል። በርግጥ የህግ ሰዎች አስተያየት ሊሰጡበት ይችላሉ። ፓሪስ የሚገኙ ጋዜጠኞችም እውነተኛውን በረከት ቢያነጋግሩት ጥሩ ነው። በህይወት እያለ በስሙ ይሄ ሁሉ ግፍ ሲሰራ ዝም ማለት ያለበት አይመስለኝም…) ወደ ዋናው ነጥብ ልመለስና የመብራህቱ ገብረህይወት ታላቅ ወንድም ካሳሁን ገብረህይወት ይባላል። ስለዚህ መፅሃፉን “ለወንድሜ ለካሳሁን ገብረህይወት መታሰቢያ ይሁን” ማለቱ ውሸት የለበትም። ዝቅ ብሎ ግን እንዲህ ይላል። “እነሆ በተለምክልኝ መንገድ እጓዛለሁ” እዚህ ላይ በረከት እንደገና እውነትን ገለበጣት። ካሳሁን ለበረከት የፖለቲካ መንገድ አልተለመለትም። ካሳሁን ኤርትራ ተወልዶ ጎንደር አደገ። ከዚያም የኢህአፓ ታጋይ ሆነ። በኢህአፓ ውስጥ ሳለ የጎሳ ፖለቲካን የሚቃወም፣ እንደማንኛውም የወቅቱ የኢህአፓ ወጣት ህብረብሄራዊ አደረጃጀት እና መስመርን የሚመርጥ ነበር። በግልባጩ መብራህቱ በታላቅ ወንድሙ ተፅእኖ የብሄር አደረጃጀትና አስተሳሰብን የሚቃወም ሆኖ ነበር ትግሉን የጀመረው። ካሳሁን የተሰዋው ከህወሃት ጋር በተደረገው ጦርነት ነው። ማለትም ካሳሁን የተገደለው በህወሃት ጥይት ነው። በረከት ስምኦን ወደ ህወሃት የገባው ከካሳሁን መገደል በሁዋላ ነው። እንዴትና በየት በኩል ነው፣ ካሳሁን ይህን የወያኔ አላማ ለበረከት ያወረሰው? ካሳሁን ምንም እንኳ ወንድሙ ቢሆንም፣ በዚህ መንገድ ታሪኩን ሊያበላሽበት መብት የለውም… በረከት በጣም የተምታታበት ሰው ነው። ኢትዮጵያን ይዞአት ገደል ሳይገባ መሄጃውን ቢፈልግ ለዚህች አገር ትልቅ ውለታ እንደሰራ ይቆጠራል። ከበረከት የተምታቱ ታሪኮች ዋናው በዘሩ ኤርትራዊ ሆኖ ሳለ የአማራ ድርጅት መሪ መሆኑ ነው። ይሄ ከሞራል አንፃር ለአማራ ህዝብ ስድብ ነው። በረከት በህብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያን ቢመራ ጥያቄ ባልተነሳበት። ሰው ተወልዶ ያደገበት አገሩ መሆኑ ይታመናል። የዘር ፖለቲካ የሚያራምድ ግን የግድ እሱም ዘሩን ግልፅ ማድረግ ይጠበቅበታል። “አማራ በዘሩ መደራጀት አለበት” ብለው ሲያበቁ፣ አማራ ያልሆነ እንዴት አማራን ይወክላል? ኢህዴን ወደ ብሄራዊ ድርጅት ሲለወጥ፣ በረከት ለራሱም ሆነ ለአማራ ህዝብ ክብር ሲል ራሱን ከአማራ ድርጅት መሪነት ማግለል ነበረበት። በረከት ስምኦን ስለዚህ ጉዳይ መፅሃፉ ላይ አላነሳም። ይልቁን በቀጣይ 20 አመታት እንዴት ኢትዮጵያን እንደሚያስተዳድራት ፍንጭ ሰጥቶናል። ይህን ማስታወሻ ለማስፈር የተነሳሁትም በመቋጫው መረጃ ምክንያት ነው። “…(አሮጌው) የአመራር ትውልድ ቦታውን ለአዲሱ የአመራር ትውልድ የሚያስረክብበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ስለዚህም ከፊት መስመር ገለል ብለን፣ ከሁዋላና ከጎን ሆነን መደገፍ አለብን በተባባልነው መሰረት የአመራር መተካካቱን ማስፈፀም ጀምረናል…” የተሰመረበት አረፍተነገር የኢህአዴግን የ2015 እቅድ የሚጠቁም ነው። እንደተሰመረበት መረጃ ከሆነ መለስና በረከት መንግስታዊ የሃላፊነት ቦታቸውን ሊለቁ ተዘጋጅተዋል። ማለትም “ከፊት መስመር ገለል” ይላሉ። “ከሁዋላና ከጎን” ሆነው ይደግፋሉ። “እስከመቼ?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የለውም። አስር ወይም ሃያ አመታት! በዚህ ስልት አገዛዙ ይቀጥላል። “መደገፍ” ሲሉ መንዳት ማለታቸው ነው። መርጠው የሚያመጧቸው እንደ ጋሪ ፈረስ ለመነዳት ፈቃደኛ የሚሆኑትን ይሆናል። መለስና በረከት ፑቲን የፈፀመውን አይነት ቁማር ሊጫወቱ የቤት ስራቸውን ሰርተው ጨርሰዋል። ይህንንም በቅርብ ጊዜ በተግባር የምናየው ይሆናል። “ከጎን መርዳት” የሚለው በምክትል ሚኒስትርነት የሚቀመጡትን የሚጠቁም ነው። ለአብነት ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሃይለማርያም ደሳለኝን ከጎን ሆኖ እየመራው ነው። ስለዚህ ነባሮቹ የምክትል ሚኒስትሮችን ቦታ እየያዙ፣ አሻንጉሊቶችን በሚኒስትርነት ያስቀምጧቸዋል። “በተባባልነው መሰረት” የሚለው አባባል የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ውሳኔን የሚመለከት ነው። በቀጣዩ ያልታወቁ አመታት ኢትዮጵያን እንዴት መምራት እንዳለባቸው የደረሱበትን ውሳኔ ጠቁመውናል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
በጣም ይገርማል ስም ሳይኖርህ ስለ በረከት አልፎም ለማይመለሰዉና ለዘላለም እረፍት ላይ ያለዉን ነፅህ ታጋይ ስም መለሰ ዜናዊይን አንስተህ ንዝንዝ የሚመሰል የስራ ፈት ሃሳብህን ትለፍፋለህ ምንም ምንም በለ በረከት ስሞኦን ከልቡ የታገለና ያታገለ ታጋይ ነዉ መለስም ለራሱ ሳይኖር ለኢትዮ ህዝብ ደከመኝ ሳይል እራሱን የሰዋ እዉነተኛ የኢትዮ ልጆች ናቸዉ፡፡
ReplyDeleteለመሆኑ አንተ ስለትግል፣አንተ ስለህዝብ ስልጣን፣አንተ ስለ እዉነት እንዴትስ ልታዉቅ ትችላለህ አንተ እኮ ስለ ዘር ልዩነት ነዉ እያወራህ ያለከዉ እዉነተኛዉ እዉቀትህ እሱ ነዉ ፡፡