Friday, September 20, 2013

ሻእቢያ ካሰራቸው አስረአንድ ባለስልጣናቱ ዘጠኙ አብዮቱ በልቷቸዋል ተባለ:: ወያኔ የበላቻቸውን ማን ይስታውሳቸው?

ሻእቢያ ካሰራቸው አስረአንድ ባለስልጣናቱ ዘጠኙ አብዮቱ በልቷቸዋል ተባለ:: ወያኔ የበላቻቸውን ማን ይስታውሳቸው? Sep 20/2013

ዲሞክራሲያዊ መሻሻሎችን በደብዳቤ ኢሳያስ አፍወርቂን በመጠየቃቸው ከአስራሁለት አመት በፊት የኢሳያስ አፍወርቂ መንግስት ካሰራቸው አስረአንድ ከፍተኛ ባለስልጣኖቹ ውስጥ በህይወት የሚገኙት ሁለቱ ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ የአለም ፓርላማዎች ህብረት የሰብኣዊ መብት ሃላፊ ሁዬ ዜንጋ አስታውቀዋል:: ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጴጥሮስ ሰልሞን እና ሃይሌ ወልደተንሳይ ውጭ ሌሎቹ በህይወት የሉም ሲሉ ተናግረዋል:: የኢርትራ ብሄራዊ ሸንጎ አባላት እና ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩት እና በመስከረም 1994 (ሴፕተምበር 2001) በቁጥጥር ስር ውለው የታሰሩት:- እቁባ አብርሃ - ባራኺ ገብረስላሴ - ሃሚድ ሃማድ - ሳላ ኪኪያ - ጀርማኒ ናቲ - እስጢፋኖስ ስዩም -መሃሙድ አህመድ ሸሪፎ - ጰጥሮስ ሰሎሞን - ሃይሌ ወልደተንሳይ - አስቴር ፍሰሃጸሆን - ብርሃኔ ገብረእግዜር ናቸው:: እዚህ ጋር ያዳምጡት :- http://amharic.voanews.com/flashaudio.html

No comments:

Post a Comment