Friday, September 27, 2013

ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት ተባለ

የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል። በቅርቡ በወልድያ ከተማ የወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች ባነሱት አመጽ መንገድ ዘግተው ወደ ላሊበላ ፤ ሰቆጣ ፣ ደሴ እና አዲስ አበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት ጉዞዎች እንዲስተጓጎሉ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አመጹን አነሳስታችሁዋል የተባሉ 13 ታዳጊ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የደህነነት ሐይሎች አጣራነው ባሉት መረጃ አመጹን ሼክ አላሙዲን ከጀርባ ሆነው ደግፈውታል። የኢህአዴግ አመራር እና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የጸረ ሽብር ግብረ ሐይል በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ውይይት ካደረጉበት በኃላ ፣ በባለሀብቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ባይቻልም በወዳጆቻቸው በኩል ምክር አንዲሰጣቸው በአቶ በረከት ስምኦን የሚመራ አንድ ቡድን መዋቀሩን ለማወቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሼክ አላሙዲን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታክስ እና ከግንባታ ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የደህንነት መስሪያ ቤት በባለሀብቱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መረጃ እንዳገኘ ቢገልጽም፣ መረጃውን እንዴት እንዳገኘው አልታወቀም። አንዳንድ ወገኖች ግን የሼክ አላሙዲን ከህግ በላይ መሆን ያሳሳበው መንግስት፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ባለሀብቱን ለመምታት የፈጠረው ዘዴ ሊሆን ይችላል ይላሉ። በጉዳዩ ዙሪያ ሼክ አላሙዲንን ወይም ወኪሎቻቸውን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ሼህ አሊ አላሙዲን ለኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። source https://www.facebook.com/justiceallethiopian

No comments:

Post a Comment