Tuesday, September 3, 2013

September 3, 2013 "አዜብን ማሰር፣ መለስን ከሞት ቀስቅሶ ለፍርድ ማቆም ነው"

መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው “የሙስና ባህር” ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ። azeb-mesfin-e አቶ መለስ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል።
ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት “ባለሃብቶች” መካከል ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር እንደሚነግዱ የሚታወቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የስጋታቸው መነሻና እምብርት ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ያለታክስ በሚገቡ ምርቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ በቴሌ የህገወጥ ማስደወል ወንጀል፣ በጫት ኤክስፖርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በስፋት ቢዝነስ እንደሚያጫውቱ የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ በገንዘብ የከበሩትን ያህል በርካታ ጠላት እንዳፈሩም የሚቀርቧቸው ይናገራሉ። azeb 2 ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ያስረከቡት አቶ ስብሃት ነጋ በተደጋጋሚ ስለሙስና መናገር የጀመሩት አቶ መለስ አፈር ሳይቀምሱ ነበር። ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ጡንቻና በዘመቻ በጀት ተመድቦለት “ባለራዕይ፣ ታላቁ መሪ” በሚል የተሰጣቸውን የሸቀጥ ስም ተገን አድርገው ሙስና ውስጥ መነከራቸውን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ስም አይጥቀሱ እንጂ ነገራቸው ሁሉ ከወ/ሮ አዜብ ደጅ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሚናገሩት የአደባባይ ምስጢር ነው። አቶ ስብሃት ነጋ ከመለስ ሞት በኋላ ይህንኑ አቋማቸውን አጠንክረው የገፉበት ቢሆንም በፖለቲካ አሰላለፋቸው ተሸናፊ በመሆናቸው ለማፈግፈግ ተገደው እንደነበር የሚናገሩ አሉ። ከውስጥ አዋቂዎች እንደሚሰማውና በተባራሪ እንደሚነገረው አቶ ስብሃት ዳግም አሸናፊውን ቡድን ተመልሰው ተቀላቅለዋል። ለዚህም ይመስላል እሳቸው ምን ያህል የጸዱ ስለመሆናቸው መረጃ ባይኖርም አሁን ከተጀመረው የሙስና ዘመቻ ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቆመው። አንዳንዶች እንደሚሉት ህወሃት በትከፋፈለ ጊዜ (ዘመነ ህንፍሽፍሽ) አቶ አባይ ጸሐዬ ውህዳኑን ተቀላቅለው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ መለስን በመቀላቀል የተጫወቱትን የ”መንታ”/ደብል/ ስልት፣ የመለስ ሞትን ተከትሎ ለተነሳው የሃይል ሰልፍ ትንቅንቅ አቶ ስብሃት ነጋም ተጠቅመውበታል። በዚሁ ስልታዊ አካሄድም የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ክንፍ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስችለዋል። አዜብ መስፍን ለምን አይታሰሩም? ከሙስና ጋር ስማቸው በስፋት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ፤ በባለቤታቸው እንደ ቪኖ ቡሽ ድንገት ሲፈተለኩ በሃዘን ድባብ ውስጥ ሆነው የጀመሩት ዘመቻ የቀልድ መሃላ ይዘት ያለው ነው። በ”ፖለቲካ ቁጭ በሉ” እንዲመለኩ የተደረጉትን አቶ መለስን ደጋግሞ በመጥራት አዜብ መስፍን “የመለስ ራዕይ ካልተቀየረና ሌጋሲው እስካልተበረዘ ድረስ …” እያሉ ካድሬውንና ቀሪውን የህወሃት ሰዎች መማጸን ላይ አተኩረው ነበር። በሄዱበትና ባገደሙበት የባለቤታቸው ስምና ዝና ላፍታም ካንደበታቸው የማይለያቸው ወ/ሮ አዜብ ጀርባቸውን ስለሚያውቁት የመለስን ስም የሚያንጠለጥሉት ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነም ከታች እስከ ላይ ስምምነት አለ። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከደረሱት አስተያየቶች መካከል “ካድሬው ባብዛኛው፣ የበላይ አመራሩ በከፊል አዜብስ?” በማለት ለምን በቁጥጥር ስር እንደማይውሉ የሚጠይቁትና የሚነጋገሩት በገሃድ ነው። ይሁን እንጂ አዜብ ለምን እንዲታሰሩ የፍርድቤት ትዕዛዝ (ዋራንት) አይቆረጥባቸውም? ለሚለው የሚሰጠው መልስ “የመለስ ሌጋሲ እንዳይወድም፣ እንዳይቆሽሽ፣ የተሰራው የረከሰና የሸቀጥ ያህል በፖለቲካ ውዳሴ የተገነባው ከንቱ ዝና እንዳይቆሽሽ፣ ብሎም ሌላ ጥያቄ እንዳያስነሳ ነው” የሚል ነው። azeb 1 አቶ ስብሃት ሲመሩት የነበረው ኤፈርትን በሳቸው አዲስ አመራርና በመለስ ልዩ አመራር ሰጪነት በሺህ ለሚቆጠሩ የትግራይ ልጆች የስራ እድል ማዘጋጀቱን፣ ትግራይ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች እንደሚከፈቱና ሲደበቅ የነበረው በጀት በዶላር ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በማድረግ ስብሃት ነጋን የማሳጣት እጅ አዙር ዘመቻቸውን አጣድፈው የጀመሩት ወ/ሮ አዜብ የትግራይን ህዝብ ልብ ለማግኘትና አቶ ስብሃት የሚከፍቱባቸውን ዘመቻ አስቀድሞ ለመቋቋም በማሰብ ነበር። ህወሃት የክልሎችን በጀት እልብ አድርጎ የሚጠባበት የብር ማሽኑ የሆነውን ሜጋ ኢንትርፕራይዝን ይመሩ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከምርጫ1997 በኋላ በድርጅት አቋም፣ በአቶ መለስ ፊርማና ውሳኔ እንዲነሱ መደረጉን፤ ከሃላፊነት የተነሱበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አኩርፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው “በሽማግሌ” ከባለቤታቸው ጋር እንደታረቁ፣ ሽምግልናውን ባከናወኑት ሰው አማካይነት ወ/ሮ አዜብ የተነጠቁት ሹመት እንዲመለስላቸው መደረጉን እንደሚያውቁ የሚናገሩ ክፍሎች “ኢትዮጵያ ውስጥ ህግና ፍትህ ለሰከንድ ቢተገበር ህገወጥ ስልክ በማስደወል የሜጋን ቢሮ ለዋና ማቀናበሪያና የተጠቀሙበት ወ/ሮ አዜብ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ ሊሆኑ በተገባ ነበር። የመለስ ሌጋሲ እንግዲህ ይህን ነው” በማለት ይጠይቃሉ። እነዚህ ክፍሎችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች አዜብ መስፍን የፖለቲካ ሃይላቸው የተቦረቦረ፣ ከበዋቸው የነበሩት ሃይሎች የተመናመኑ፣ እንደ ተርብ የሚናደፈው አንደበታቸውና ባህሪያቸው እንደበረዶ የቀዘቀዘበት ወቅት ላይ እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው። በጸለመ ልብስ የሚታዩትና የሃዘን ጥቁር ልብሳቸውን ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት ወ/ሮ አዜብ ተቅለስላሽ ሰው ሆነው መታየታቸው ስጋታቸው ማየሉን የሚያሳይ እንደሆነ የሚመሰክሩት ክፍሎች “አዜብ መስፍን ወዳጅ እንደሌላቸውና በተለይም በህወሃት ሰዎችና ካድሬዎች azeb-mesfin ዘንድ ስለማይወደዱ ዙሪያቸውን ከሚዞራቸው የሙስና ደወል ማምለጥ ስለሚችሉበት ሁኔታ ሊያስቡ እንደሚችሉ እንገምታለን” ይላሉ። ለአብነትም ሲያኮርፉ ወደ ሳዑዲ እንደሚሄዱና በዱባይ ሪል ስቴት እንዳላቸው ስለሚታሙ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደዚያው ሊያመሩ እንደሚችሉ ምልክት እንዳለ ይጠቁማሉ። በዱባይ አላቸው ስለሚባለውና በሌሎች ተቋራጭ ድርጅቶች ስም ስለተገነቡት ቤቶችና ንብረቶቻቸው እነዚህ ክፍሎች ለጊዜው ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። በሌላ ወገን ግን አሁን የባለቤታቸውን የፋውንዴሽን ስራ እንዲሰሩ የተመደቡት ወ/ሮ አዜብ የእነ በረከት ስምዖን ቡድን በመሆናቸው፣ ለዚሁ ቡድን ቀኝ እጅ የሆኑት የደህንነቱ አውራ አቶ አሰፋና ሸራተን ያሉት ባለሃብት እጅግ ወዳጃቸው በመሆናቸው ቀስ በቀስ እንዲከስሙ ይደረጋል እንጂ አይታሰሩም ሲሉ በድፍረት ይናገራሉ። ወ/ሮ አዜብን ማሰር ማለት አቶ መለስን ከመቃብር አውጥቶ እንደገና ፍርድ አደባባይ የማቅረብ ያህል እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች “ታላቁ፣ ባለራዕዩ፣ አስተዋዩ፣ አርቆ አሳቢው፣ የደሆች አባት፣ ራሱን ‘ለኢትዮጵያ’ አንድዶ የሞተ፣ አንዲት ሃሳብ ይዞ ወደ (ኢትዮጵያ) ምድር የመጣው አዳኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣ ዜጎቹን በቀን ሶስቴ እንዲበሉ ያስደረገው፣ የአፍሪካ አንደበት፣ የዓለም ቅርስ፣ የወደፊቱ ኢትዮጵያ ተምሳሌት፣ የታሪክ አውራ፣ እርምና ወንጀል የሌለበት … በማለት ህወሃት ሆን ብሎ የገነባውን ስም አዜብን በማሰር አፈር አይከተውም” በማለት አዜብ ሊታሰሩ የማይችሉበትን ምክንያት ያመላክታሉ። የመጨረሻው መጀመሪያ birhane ብርሃነ ኪዳነማርያም ወ/ሮ አዜብ የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ስለመሆናቸው ምልክቶች እንዳሉ የሚጠቅሱ አሉ። ያለ ከልካይ ሲመሩትና ሲነዱት ከነበረው ግዙፉ የህወሃት የገንዘብ ቋት ኤፈርት ተሰናብተዋል። ወንበራቸውን እንዲቀሟቸው የተደረጉት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ዋና ስራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብርሃነ ኪዳነማርያም (ብርሃነ-ማረት) የቀድሞው የፍቅር ወዳጃቸው ናቸው። በደህንነት ውስጥ አድራጊና ፈጣሪ የነበሩት የቅርብ የንግድ ሸሪካቸው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የሚጠየፉትን ወህኒ ገብተውበታል። በከፍተኛ የንግድ ቅርርብና ሽርክና የሚወዳጇቸው አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ከታሰሩ ወራት ተቆጥሯል። የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ከቀረጥ ነጻ በመፍቀድ አብረዋቸው በኤፈርት ታርጋ ገንዘብ ሲያልቡ ኖረው አሁን ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። የቴሌ የሙስና ቅሌትና በኦሮሚያ የመሬት ንግድ አብረዋቸው ሲሳተፉ የነበሩ ሁሉ ዋራንቲ ተቆርጦባቸው እስር ቤት ገብተዋል። እንግዲህ በዚህ ሁሉ መዓት ውስጥ ያልተነኩት ወ/ሮ አዜብ ብቻ ናቸው። ለፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ወቅት ወ/ሮ አዜብን በትዕዛዝ ሰጪነትና በንግድ አጋርነት ዋና ተባባሪ መሆናቸውን በማመልከት መስክረዋል። ከዚህም በላይ በርካታ ጥቆማ አለ። በነዚህና በበርካታ ምክንያቶች ጣት የተቀሰረባቸው ወ/ሮ አዜብ አሁን የቀብርና የተስካር፣ ሙት ዓመት ዘካሪና የማስታወሻ ግንባታ ኮሚቴ ሃላፊ ሆነው ተቀምጠዋል። የመጀመሪያው መጨረሻ “መገለል” እንደሆነ፣ ከዚያም እውነተኛው መጨረሻ ሊገጥማቸው እንደሚችል ግምታቸውን የሚሰጡ ተበራክተዋል። “ከቶውንም አይታሰሩም። ለመለስ ሲባል “የሚሉት ደግሞ መጨረሻቸው ከኢህአዴግና አሁን ካለው የቡድን ፍትጊያ ጋር እንደሚሆን ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment