Sunday, September 15, 2013

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ !!!

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ !!! September 15/09/2013 የወያኔ መንግስት በዓባይ ግድብ ሰበብ የባንድ ሽያጭ ለማድረግ እና በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለመዝረፍ በየሀገሩ የሚያደርገውን የአባይ ቦንድ ሽያጭ ጉዞ ቀጥሏበታል :: ነገር ግነ ወያኔ በየ ሀገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል በ Calgary ካናዳ ፣በ ኖርዌይ ኦሰሎ እና ስታቫንገር ከተማ ፣ በ አሜሪካ Houston ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በተለያዩ አገራት እንዲሁም በቅርቡ በስዊድን ጉተን በርግ ከተማ የወያኔ አሽከሮች በቆራጥ ኢትዮጵያኖች ጀግኖች ልጆች ቡጤ ሳይቀር ቀምሰው አንገዳቸውን ደፍተው በውርደት የተከራዪትን አዳራሸ ለቀው የወጡበት ትርዒት አስቂኝ እና አስገራሚ ነበር:: ነገር ግነ ወያኔ በአባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ስም ገንዘብ ለመዝረፍ በየ አገሩ እያደረገው ያለው ጉዞ ግን እንደሰበው ሳይሆንለት ውርደትን እና አፍረትን መቅመሱን ስራዬ ብሎ ተያይዙት እያለ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንዲሉ የወያኔ አሽከሮቸ በውጪ ሀገር በሚኖረው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በየ ሀገሩ ምን ያከል እንደተጠሉ እና ተቀባይነት እንደሌላቸው ልባቸው እያወቀው ነገር ግን በእንቢርተኝነት ልባቸው የደነደነ የወያኔ ተላላኪዎች ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማሰብ አይናቸውን በጨው ታጥበው በአባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ስም በየ ሀገሩ እየዞሩ የኢትዮጵያውያንን ገንዘብ ለመዝረፍ የሚያደርጉትን ጉዙ አላቆሙም :: ነገር ግን አሁንም ወደፊትም መቺም እና የትም ቢሁን ወያኔ የሚሳካለት አይመሰለኝም ሊያጋጥመው እና ሊሆንበት የሚችለው ይኺው ነው :: ምክንያቱም ነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው እና ቅድሚያ በኢትዮጵያ ላይ እንዲሆን የሚመኛው የተወቀ እና ግልጽ ነው:: ከአባይ መገደብ በፊት ዘረኝነት ይገደብ ፣ ፍትህ እና ነፃነት ያስፈልገናል፣ በግፍ እና በጭካኔ የታሰሮት ዜጎቻችን ይፈቱ ፣ ወያኔ ሌባ ነው እና የመሳሰሉትን ቃላቶች ሲሆኑ እነዚህንም ቃላቶች ወያኔ ሊሰማው እና ሊቀበለው የማይፈልገው ነገር ግን በአባይ ግድብ ስም የቦንድ ሽያጭ ገንዘብ ከሕዝቡ ለመዝረፍ በሚያደርገው ሮጫ የትም ሀገር ወያኔ ሊያጋጥመው የሚቸሉ የነጻነት ድምጹች ናቸው :: ይህም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ድምጽ ብቻ ሳይሆን በነጻነት የመናገር እና የመቃወም መብቶቻቸው ተገፎ በአረመኔው እና በጨካኙ የወያኔ መንግስት መብቶቻቸው ተረግጡ እና ተገፎ በወደዱት እና በመረጡት ሳይሆን በጉልበተኛው መንግስት በጉልበት እየተገዙ ያሉት የመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው :: ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወያኔ መንግሰት ያለውን መጥፎ ጥላቻ እና በእዚህ አረመኔ የወያኔ መንግስት መገዛት ምን ያክል እንዳንገሸገሸው በተግባር የሚያሳይ ነው :: ስለዚህ የወያኔ ባለስልጣኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ መቼም ቢሆን የትም ቢሆን ተቀባይነት እንደሊላቸው ሊያውቆት እና ሊገነዘቡት ይገባል:: አሁንም ወደፊትም ውርደት እና ውድቀት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዘብ !!!

No comments:

Post a Comment