Monday, September 16, 2013

ለጥንቃቄ፦ ካድሬዎች በሞቫይል ስልክ እያደናበሩ ነው!

ለጥንቃቄ፦ ካድሬዎች በሞቫይል ስልክ እያደናበሩ ነው! የህወሓት መሪዎች የመረጃ ምንጮቼ ለመሰለልና ምናልባት ኔትዎርክ እንዳለኝ ለማወቅ ከኔ ጋር ቅርበት ወዳላቸው ሰዎች (በካድሬዎቻቸው በኩል) ‘አብርሃ ደስታ’ መስለው በመደወል ዜጎችን እያወናበዱ መሆናቸው ደርሼበታለሁ። ‘አብርሃ ደስታን ሊያውቁ ይችላሉ’ ተብለው ለሚገመቱ ሰዎች (ካድሬዎቹ) እየደወሉ ‘አብርሃ ደስታ ነኝ፤ ….. ለምናምን ነገር ፈልጌሃለሁ፣ የት ነህ፣ መረጃ ስጠኝ ወዘተረፈ …’ እያሉ ንፁሃን ዜጎች እያደናበሩ ነው። ዜጎች ለማደናበርና ለመሰለል ከተዘጋጁ ካድሬዎች (የአብርሃን ጉዳይ ለማጥናት) ወደ ሐውዜን ተልከው የጥፋት ተልእኳቸውን እየፈፀሙ ያሉ 13 ግለ ሰቦች ሲሆኑ በመቐለ ደግሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አሉ። ወደ ሐውዜን ከተላኩ የተወሰኑ ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል። ስለዚህ በሐውዜን፣ መቐለ እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች የምትገኙ ጓደኞቼ 'አብርሃ ደስታ ነኝ' ብሎ ለሚደውልላቹ ማንኛውም ሰው ከማመናቹና መረጃ ከመስጠታቹ በፊት እንድታረጋግጡ በትህትና አሳስባለሁኝ። 'አብርሃ ደስታ ነኝ' የሚል ደዋይ ካጋጠማቹ የተደወለላቹሁ ስልክ ቁጥር በፌስቡክ መልእክት አድርሱኝ። ማንነቱ አጣርተን እናጋልጠዋለን። ስልክ ቁጥሬን የምታውቁ ካላቹ ደግሞ እኔ መሆኔን ደውላቹ አረጋግጡ፤ አደራ። ሰሙኑ አቶ አባይ ወልዱ ታማኝ የተባሉ የፓርቲው ሰዎች ሰብስቦ በአብርሃ ደስታ እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንከር ያለ የስለላ ተግባር መከናወን እንዳለበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። የአባይ ወልዱ ዛቻ ትርጉም የሚሰጠው ባይሆንም ጥንቃቄ ማድረጉ ግን ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ቴሌን በሕገወጥ መንገድ ለፓርቲ ስለላ እየተጠቀመ ነው። ብዙ ጉዳትም ሊያደርስ ይችላል። ህወሓት የመንግስት ሃብት (ቴሌን) ለግል (ለፓርቲ) ጥቅም በማዋል በሙስና ሊከሰስ በተገባ ነበር። ለካ ቴሌን ለፓርቲ ጥቅም ለማዋል ነው በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገው። ግን... በአሁኑ ሰዓት የደህንነት ሰዎች በጣም ተዳክመዋል። በስለላ እየተሰማሩ ያሉ የደህንነት ሰዎች ሳይሆኑ ተራ (ግን ታማኝ የሚባሉ) ካድሬዎች ናቸው። እነዚህ ሆድ-አደሮች ማሸነፍ ደግሞ ቀላል ነው። It is so!!! source http://www.maledatimes.com/

No comments:

Post a Comment