To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, September 16, 2013
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ሊመሰረትባቸው ነው
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ሊመሰረትባቸው ነው
Posted by raheltakele
አዲስ አበባ፣ነሃሴ 29፣2005 የኢትዮድያ አርበኞች ግንባር አባል ናቸው በሚል የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው
ተከሳሾቹ ጸጋው አለሙ፤ ዋስይሁን ንጉሱ፤ ጎዳዳው ፈረደ፤ ማማይ ታከለ እና ተገኝ ሲሳይ ናቸው
የፌደራል አቃቤህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ የመኖሪያ አድራሻቸው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ነው
እንደ ክሱ በተለይ 1ኛው ተከሳሽ ጸጋው አለሙ በ 2000 አ/ም ኤርትራ በመሄድ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ወደ ሃገር ቤት ከተመለሰ በኋላ መዝገቡ ከርሱ ጋር የተካተቱ 2 ተከሳሾችን ሚያዚያ 2005 አ/ም፤
በአማራ ክልል ጸገዴ ግረዳ ሶርቃ ቀበሌ ከኤርትራ ያገኘውን ስልጠና አካፍሏቸው እነርሱ ኤርትራ በመሄድ ተመሳሳይ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ ኢትዮዽያ እንደሚመለሱ ነግሯቸው ወደ ኤርትራ ሲሸኛቸው በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ ላይ ተይዛል ።
በክስ መዝገቡ የተመለከቱ ሌሎች 4ቱም ተከሳሾች በተለያዩ ጊዜያት በጸገዴ ግረዳ ሶርቃ ቀበሌ የጉዞ ዝግጅት ካደረጉ በኋላ ሚያዚያ 16 በትግራይ ክልል ይካድራ ከተማ ተይዘዋል
አቃቤህግ በሌላ ክስ ፤ በመዝገቡ የተመለከቱ ዋስይሁን ንጉሱ እና ተገኝ ሲሳይ ኤርትራ እና አውሮፓ ከሚገኙ የአሸባሪው ድርጅት የተለያዩ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር አባላትን እየመለመሉ ወደ ኤርትራ ልከዋል
በመሆኑም ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ተረኛ ችሎት ከጸረ ሽብር ህጉ አንጻር የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ክሱን ለማሰማት ለጥቅምት 7 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment