Tuesday, September 24, 2013

15 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባለት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው የተቀሩት ስኬታማ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው

አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና
የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉትን የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ የታሰሩት አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ ኃላፊውም “ህጋዊ ሰልፍ እንደምታደርጉ እናውቃለን ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ አመራሮቹ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነርንና የከተማዋን መስተዳድር ሃላፊዎች ለማነጋገር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በተለያየ አቅጣጫ የተሰማሩት ሌሎቹ የአንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማደረግ ላይ ናቸው፡ source http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/24/6761/ posted by Aseged Tamen e

No comments:

Post a Comment