To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, September 2, 2013
ሰበር ዜና! የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በቀውጢ ስብሰባ ላይ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በቀውጢ ስብሰባ ተጠምደዋል። አባላቶቹ በመካከላቸው እየተፈጠረ ስላለ ክፍተት እርስበርስ እየተገማገሙ ሲሆን ከስብሰባው በኋላ አዳዲስ የመንግስትና የፓርቲ
አደረጃጀቶች እንዲሁም የስልጣን ሽግሽግና መቀያየር እንደሚኖር ይጠበቃል።
የህወሓቶች ዋነኛ አከራካሪ አጀንዳ የት.እ.ም.ት ጉዳይ ሁነዋል። ትእምት ማን ይምራው? እንዴት ይተዳደር? የተፈጠረ ችግር እንዴት እንፍታው? … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች እያከራከሩ ነው። ከስብሰባው በኋላ በትእምት የስራ አመራር ለውጥ እንደሚኖር ተገምቷል።
የህወሓቶች ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ የሌሎች የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስብሰባ ይከተላል። ከዛ የአጋር ድርጅቶች፤ ቀጥሎም የአምባሳደሮችና የመንግስት ተወካይ ባለስልጣናት ስብሰባ ይካሄዳል።
ኢህአዴጎች አጠቃላይ የመንግስት አደረጃጀት ለውጥና የባለስልጣናት መቀያየር ለማድረግ አቅደዋል።
ኢህአዴግና ስብሰባ የ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ። እኔ ደግሞ ስብሰባ ሲደብረኝ!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment