Monday, September 16, 2013


የአገራችን ገዢ ድርጅት ህወአት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ:;ከ እርስ በ ርስ ሹክቻው አንስቶ የ ውሃ ጦርነት ተጨምሮበት የተረገጠው የመሃል አገር ህዝብ የ መብት ጥያቄን ተከትሎ ራሱን ክፉኛ እንዳስጨነቀው ይመሰክራሉ:: በጎረቤት አገሮች መሰረታቸውን በማድረግ ጸረ -ህወአት ትግል የሚያደጉ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ቁጥር ከአመት አመት እየጨመረ በመምጣቱ ለስር-አቱ መዝረክረክ እና ውስጡ በፍራቻ እየተዋጠ መምጣት በዋነኝነት ተጠቃሽ እንደሆነ አድርገው የሚያስቀምጡ ታዛቢዎችም አልጠፉም:: የደነበረው ህወአት ውስጡን ሰላም አድርጎ በመጠኑም ቢሆን መረጋጋት ለመፍጠር እና ገዢነቱን ለማስቀጠል እንደዋንኛ አጀንዳ አድርጎ ያስቀመጠው በጠላትነት ላመታት ሽብርተኛ እያለ ሲፈርጅ የኖረውን የኤርትራን መንግስት ጋራ ሰላም መፍጠር እና እርቅ ማድረግን ነው::ለዚህም ተልእኮ የድርጅቱ ዋንኛ ነባር ታጋይ ባለስልጣናትም ባይሆኑ :ተስበው ወስጡ በገቡት አሁን በ ፕሬዚደንቱ እና ቀደም ሲል ደግሞ በአቶ ሃ/ማሪያም ደሳለኝ በኩል ተመሳሳይ ልመና አዘል የሰላም ድርድር ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወሳል:: የድርጅቱ ነባር ታጋይ ባለስልጣን ለምን አፍ አዋጥተው ከኤርትራ መንግስት ጋር እንደራደር ለማለት ፈሩ? አሁንም ከ ኤርትራ መንግስት በኩል ምላሹ ዝምታ ከሆነ በቀጣይነትስ ህወአት ከ አቶ ግርማ እና ሃ/ማርያው ውጪ ማንን ልኮ የአቶ ኢሳያስን ደጅ ይጠናል ?ሃይሌ ገ/ስላሴን?ያም ሆነ ይህ 22 አመት ስለዠግንነቱ ሲሰብክልን የነበረው ዠግናው የ ህወአት ሰራዊት የመኖር ህልውናው ጉዳይ 'የአሸባሪ አጋር' በሚላት አገር እና መሪው አቶ እጅ ወድቅዋል::እድሜው በ ኢቶጳ ምድር በገዢነት እንዲረዝም ያሉትን እሺ ብሎ ለድርድር መቅረብ...አልያም እድሜ ማሳጠር! ጀግና ሲለምን ሲያሳዝን

No comments:

Post a Comment