Friday, September 26, 2014

Eritrean Man Pleads Guilty to Smuggling Undocumented Eritreans and Ethiopians into the USA


Habtom Merhay Pleads Guilty to Smuggling Undocumented Eritreans and Ethiopians into the USA

WASHINGTON – A national of Eritrea and citizen of the United Kingdom pled guilty today to smuggling undocumented immigrants from Eritrea and Ethiopia into the United States.

Assistant Attorney General Leslie R. Caldwell of the Justice Department’s Criminal Division, U.S. Attorney Ronald C. Machen Jr. of the District of Columbia, and Special Agent in Charge Clark E. Settles of U.S. Immigration and Customs Enforcement’s (ICE) Homeland Security Investigations’ (HSI) Washington, D.C., Field Office made the announcement.

According to his plea agreement, Habtom Merhay, 47, who operated primarily from his residence in Dubai, orchestrated the unlawful smuggling of up to 99 undocumented African immigrants to the United States for profit.  Specifically, Merhay admitted that in exchange for fees up to $14,000, he smuggled immigrants into the United States by providing fraudulent travel documents, purchasing airline tickets for travel to

South and Central America, and then coordinating with a network of smugglers to facilitate the travel by air, land and water across Central America and Mexico and into the United States.

Merhay pled guilty today before U.S. District Judge Reggie B. Walton of the District of Columbia, and is scheduled for sentencing on Dec. 16, 2014.  Merhay was in the custody of Moroccan authorities between his arrest in Marrakech, Morocco, in August 2013 and extradition to the United States on April 25, 2014.


The investigation was led by HSI’s Washington, D.C., Field Office, with the support of the Human Smuggling Trafficking Center and the U.S. Customs and Border Protection’s National Targeting Center.  This case is being prosecuted by Trial Attorney Jay Bauer of the Criminal Division’s Human Rights and Special Prosecutions Section and Assistant U.S. Attorney Frederick Yette of the District of Columbia.  The extradition was handled by Dan E. Stigall of the Criminal Division’s Office of International Affairs.

The Department of Justice and HSI expressed their appreciation for the significant assistance provided by the Moroccan Ministry of Justice.

Source: Justice.gov //diretube.com

የመቐለ ታሳሪዎች ስም ዝርዝር….!

http://satenaw.com/

  • 739
     
    Share
የፍትህ ያለ?
justiceባለፈው ሓሙስ 08 / 01 / 2007 ዓ ም በሓወልቲ ክፍለ ከተማ በየነባር ይዞታ ማፅደቅና ያለ ማፅደቅ ምክንያት በተፈጠረ ኣለ መግባባት 20 ሰዎች ተደብድበው መታሰራቸው ገልጬ ነበረ።
እንዲታሰሩ ያዘዘውም የክፍለ ከተማዋ ኣስተዳዳሪ ኣቶ በርሀ ፀጋይ መሆኑን ጠቅሼ ነበር።
በወቅቱ ከታሰውሩ ኑዋሪዎች
፩) ለኣከ ገብረሂወት
፩) ሃለቃ ሙሉ ገብረሰላሴ
፫) ኣቶ በርሀ ፋንቱ የ80 ዓመት ኣዛውንት
፬) ቐሺ ፍቕረ ሓዱሽ
፭) ሃለቃ ጠዓመ በርሀ
፮) ገብረ ታደሰ
፯) ወይዘሮ ለተኪሮስ ወልዱ
፰) መልኣኩ ፀጋይ
፱) ገብረሂወት ኣፅበሃ
፲) መሓሪ ተጠምቀ
፲፩) ወይዘሮ ፅርሃ ካሕሳይ
፲፪) ወይዘሮ ተክለኪሮፕስ ገብረሚካኤል
፲፫) ወይዘሮ መድሂን ሲሆኑ የማሳሰርያ ምክንያት የነባር ይዞታ የማፅደቅ መብት እያላቸው ኣስተዳዳሪዎች ሲከለክሉዋቸው የይገባናል ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። ለዚህ ተቃውሟቸው በስብሰባው በመግለፃቸውና ኣብየቱታ ወደላይ ኣካላት( እስከ ፌደራል ደረጃ እናቀርባለን ) በማለታቸው ነው።
ሃለቃ ሙሉ ገብረስላሴ የተባለው የቀጠና 8 ሊቀ መንበር የህዝቡ የይገባኛል ጥያቄ ደግፈሃል ብለው በስብሰባው ኣውርደው እንዲያውም ኣንተ ነህ ያነሳሳሃቸው ተብሎ ታስረዋል።
የሞሞና ቀበሌ ኣስተዳዳሪ ኣቶ ግደይ ረዳም የህዝቡ ጥያቄ ደግፈሃል ተብሎ ከሃላፊነቱ በማውረድ ለብቻው በፖሊስ እንዲታሰር ኣድርገዋል።
ይህ የዓፈና ተግባር የህወሓት ካድሬዎች ከህዝቡ መሬቱ እየነጠቁ በሊዝ ስም የሚቸበችቡበት የተለመደ ሱስ ሲሆን ተቃውሞኣቸው ለገለፁ ተበዳዮች በጎ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዱላና እስርቤት ቀንታቸዋል።
ህዝቡ በህወሓት መንግስት ተማረዋል። ኣንገት ላንገት ተናንቆ እየተፋለማቸው ይገኛል።
ድል ልጭቁን ህዝባችን….!

Thursday, September 25, 2014

የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ በአቶ በረከት ማስጠንቀቂያ ተጠናቀቀ


  • 703
     
    Share
ነገረ ኢትዮጵያ 
• ‹‹ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› አቶ በረከት
• ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ የተጻፈ ህግ አይሰራም›› ዳኞች

አቶ በረከት
አቶ በረከት
ከሁለት ሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የፈጀው ባህርዳር ላይ የተደረገው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ ትናንት መስከረም 14/2007 ዓ.ም በአቶ በረከት ስምኦን ማስጠንቀቂያ መጠናቀቁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ስብሰባውን የዘጉት አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ፖሊስ፣ አቀቤ ህግና ዳኛ ከአስፈጻሚው (ከካቢኔው) ጋር ተስማምቶና እጅና ጓንት ሆኖ መስራ አለበት፡፡ ይህ ነው ልማታዊ የፍትህ ስርዓት፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በተቃራኒው ተሰብሳቢዎቹ ‹‹ከአስፈጻሚው አካል ጋር እጅና ጓንት ሆናችሁ ስሩ ማለት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር መፍቀድ ነው፣ ሊሰበስበን ይገባ የነበረው የካቢኔ አካል ሳይሆን የራሳችን ተቋም የሆነው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፣ ስልጠናው በራሱ የዳኝነት ስርዓቱን፣ ተቋሙንና ግለሰባዊ መብታችንን የጣሰ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን እንደገለጹ ታውቋል፡፡ በአንጻሩ አቶ በረከት ‹‹አሜሪካን ጨምሮ በየትኛውም አገር የፍትህ ስርዓት አስፈጻሚ አካሉ ጣልቃ ይገባል፣ ይህ የምታነሱት ሀሳብ አደናቃፊ ሀሳብ ነው፣ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› ማለታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
በስብሰባው ላይ የተገኙት ዳኞችም ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ አድር የተባለውን ማድረግ ነው፣ የተጻፈው ህግ አይሰራም›› በሚል የወረደላቸውን ትዕዛዝ እንደሚያስፈጽሙ ጠቁመዋል፡፡ በስብሰባው የተገኙት ሰብሳቢ ዳኛ (የተቋም ባለቤት)ና የስራ ሂደት አስተባባሪ በስብሰባው ላልተገኙት ባልደረቦቻቸው ከእነ አቶ በረከት በወረደላቸውን ትዕዛዝ መሰረት ‹‹አቅጣጫ ይሰጣሉ››ም ተብሏል፡፡
-- Ze-Habesha 

ስዊድን የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች


  • 2479
     
    Share
ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው አሉ
ስዊድንና ኤርትራ በዲፕሎማቲክ የእሰጣ እገባ ውስጥ ከገቡ በርከት ያሉ ጊዜያት የተቆጠሩ ሲሆን በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ባልተገባ ተግባር ተገኝተዋል በሚል የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ስዊድንን በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ የስዊድን መንግስት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ እጅ አለበት ብለዋል። በስዊድን የወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የስዊድን መንግስት በኤርትራ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ላይ በዚያው በስዊድን ክስ መመስረቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሻክሯል።
isayas afewerki
የኤርትራ መንግስት ዋነኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ በተለያዩ ሀገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ላይ የጣለው ሁለት በመቶ የገቢ ታክስ ሲሆን በድርጊት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን በኢምባሲያቸው ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በስዊድን የሚገኙ ኤርትራውያንም ኢምባሲያቸው የሚጠበቅባቸውን የታክስ መጠን ካልከፈሉ የተለያዩ የዜግነትና የጉዞ ዶክመንቶችን ከመከልከል ባለፈ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማያዣነት ተጠቅሞ እስከማስፈራራት ደርሷል በሚል ለስዊድን መንግስት ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መንግስት በስዊድን በሚገኙ ኤርትራውያን እና የስዊድን ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የተደራጀ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን የተቃውሞ አደራጅ ግለሰቦችን ለይቶ ለመከታተል በስዊድን የሚገኘውን ኤምባሲውን እና ዲፕሎማቶችን ይጠቀማል በሚልም ጭምር ነው የስዊድን ባለስልጣት የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ለማባረር በምክንያትነት ያስቀመጡት።
የኤርትራ መንግስት በየሀገሩ በሚገኙ ኤምባሲዎቹ አማካኝነት ከኤርትራ ዲያስፖራዎች በታክስ መልኩ በሚሰበሰበው ሁለት በመቶ ገቢ ሽብርተኞችና በፋይናንስ እያገዘ ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለበት ዓመታት ተቆጥረዋል። ሆኖም ከማዕቀቡ በኋላ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት በተለያየ ሀገራት ኤምባሲዎች በኩል ታክሱን ለመሰብሰብ የሚያደርገው ሙከራ በየሀገራቱ መንግስታት ተቃውሞ እያስነሳበት ነው። ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ መልኩ ካናዳና ኤርትራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት በቶሮንቶ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ እስከማባረር ደርሷል።
የስዊድን እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው ብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኤርትራ መንግስት ሁለት በመቶ ታክሱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በሽብርተኝነት ለማተራመስ ይጠቀምበታል በሚል ማዕቀቡ እንዲጣልበት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሚናን መጫወታቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ጂስካ አፍሪካ ኦንላይን ዘግቧል። (ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)
-- Ze-Habesha 

Tuesday, September 23, 2014

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001 ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ” ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡፡
temesgen-desalegn
የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን አዋቂነት” ላይ የቆመው መንግስት ምን ያህል በጠባብ የወንዝ ልጅነት የተተበተበ እና በዘራፊ ባለሥልጣናት የተዋቀረ እንደሆነ በስፋት ተርኮልናል፡፡ በተለይም ሙስና እና የህወሓት ካድሬዎች የበላይነትን በተመለከተ በማስረጃ አስደግፎ በተዋበ ስነ-ጽሑፋዊ ቋንቋ ዘርዝሮልናል (በርግጥ “የጋዜጠኛው” አሊያም “የደራሲው ማስታወሻ” የሚያነቡ እስኪመስልዎ ድረስ የመጽሐፉን አርትኦት ተስፋዬ ገ/አብ ወይም የተስፋዬ ብዕር ተፅእኖ ያለበት ደራሲ ብዙ እንደለፋበት በግልፅ ማስታወቁን መካድ አይቻልም)፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ዛሬም ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉ የቀድሞ ጓዶቹ ለህሊናቸው ሲሉ በድብቅ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ደፍረው እንዲያጋልጡ በጠየቀበት ብዕሩ፣ የራሱንም ጥፋቶች እና በትዕዛዝም ይሁን በግል ተነሳሽነት በደል ያደረሰባቸውን ንፁሃን በይፋ ይቅርታ ቢጠይቅ መልካም ነበር፤ አሁንም ቢሆን ለዚህ አይነቱ ቅንነትና በጎ አርአያነት ገና አልረፈደም፡፡ ርግጥ ነው የስደት ምርጫው ባደረጋት ሀገረ-አሜሪካ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ድርጅቱ ኢህአዴግ ይሰራው በነበረው ሕገ-ወጥ ድርጊትና የጭካኔ እርምጃ አልፎ አልፎ ቢሮውን ዘግቶ እንደሚያለቅስ፣ ባስ ሲልም ህሊናውን ቆጥቁጦት ታምሞ አልጋ ላይ እንደሚውል በመግለፅ የራሱን ጲላጦሳዊነት ለመስበክ መልፋቱን ስናስተውል፤ ጸሐፊው የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሪ በነበረበት ወቅት የበደለውን ሕዝብ ይቅርታ የመጠየቅ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት (ቢያንስ በዚህ ሰዓት) የለውም ብለን ማዘናችን አይቀርም፡፡
እንዲሁም ከሀገር እንዲወጣ የተገደደበት ምክንያት ተብሎ ስለተናፈሰው ወሬ ትንፍሽ አለማለቱ በበኩሌ አስተዛዛቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፤ በወቅቱ የስደቱ መነሾ ተደርጎ በከተማዋ በስፋት የተናኘው፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ እና “የግንቦት 7 አባላት ናችሁ” የተባሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ለአንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ “ሙከራው መፈንቅለ መንግስት ነው” የሚል መግለጫ በመስጠቱ እንደነበረ ነው፤ በዚህም እጅግ የተበሳጨው ጠ/ሚኒስትሩ፣ አለቃው በረከት ስምዖን ላይ ጭምር የጭቃ-ጅራፉን ከማወናጨፉም በላይ፣ ኤርሚያስን ያለ ሥራ እንዳንሳፈፈው መወራቱን አስታውሳለሁ፤ ይህንን መረጃ አምኖ ወደመቀበሉ የሚገፋን ደግሞ በዚያው ሰሞን መለስ ዜናዊ ራሱ በቴሌቪዥን ቀርቦ ‘…የተደረገው ነገር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፣ ከአልቃይዳና አልሸባብ ጋር ሲነፃፀሩ የእኛዎቹ አማተሪሽ (ልምድ አልባ) ናቸው’ እያለ የሚኒስትር ዴኤታውን ንግግር ለማስተባበል ሲዳክር የመስተዋሉ እውነታ
ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ከዚህ ግልፅ ሹክሹክታ በኋላ በትምህርት ሰበብ ሀገር ለቅቆ መሰደዱ የአንድ ሰሞን የከተማ ወሬ ሆኖ ነበር፡፡ እነሆም ወንድም ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ጉዳይ ዳጉስ ባለው መጽሐፉ ውስጥ ሽራፊ ገፅ ሊሰጠው አለመቻሉ እዚህ ጋ በትዝብት እንዳነሳው መገደዴን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ አሸንፈሀልና በዝብዘህ ብላ!
ህወሓት-ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ በግርማ ብሩ አነጋገር “ደሀ-ዘመም” (በመጽሐፉ የተጠቀሰ) እንደሆነ ለማሳመን የሚሞክርበት ብልጠት፣ ራሱን ለሙስና ፅዩፍ አስመስሎ በማቅረብ ነው፤ ይህን አይነቱን ስሁት አመለካከት በሕዝብ ውስጥ ለማስረፅ ጥቂት የፖለቲካ መታመን-ጉድለት ጥርስ ያስነከሰባቸውን ጉምቱ ጓዶቹን “ሙሰኛ” በሚል ወንጅሎ በወህኒ የቃየል መስዋዕት ሲያደርጋቸው ተስተውሏል፤ እርምጃውንም በፓርላማው መድረክ ሳይቀር ሲኩራራበትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲያውለው ተመልክተናል (ከሩቁ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ፤ ከቅርቡ ደግሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ፣ የደህንነት ኃላፊው ወ/ስላሴ እና መሰል ባለሥልጣናትን እስር ልብ ይሏል)፡፡ የሚኒስትር ዴኤታው መጽሐፍ፣ መለስ እና ጓዶቹ ካደነቆሩን በግልባጩ ‘የዘረፋ መሪዎች’ የሚላቸው ሁለት የህወሓት ሰዎች፣ በባላንጣነት ተሰልፈው እንዴት የሀገር ሀብት ለመቀራመት ይሽቀዳደሙ እንደነበር አጋልጧል፤ አዜብ መስፍንን እና አርከበ እቁባይን፡፡
“እነ አርከበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው ጥቂት ወራት በፊት በህወሓት ውስጥ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የህወሓት ዳግም መከፋፈል ምክንያት ደግሞ በወ/ሮ አዜብ እና አርከብ ቡድኖች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው ነበር፡፡ መነሻው መረን የለቀቀ የጥቅም ግጭት ሲሆን ዓላማው የህወሓት ኢንዶመንቶችን መቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡” (ገፅ 25) ከዕለት ተዕለትም ይህ ሁኔታ የተካረረ ልዩነት ፈጥሮ፣ ፖለቲካዊ ቁመና በመላበሱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ህወሓት መገፋቱን እና መለስ በበረከት በኩል የድርጅቱን ካድሬዎች እያስጠቃ ነው የሚል ክስ ከማጎኑም ባሻገር፤ ወደኋላ ተጉዞ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተጠናቀቀበትን መዛግብት አቧራ በማራገፍ፣ ተጠያቂነቱን ከፍ ሲል ወደ መለስ ዜናዊ፣ ዝቅ ሲል ደግሞ ወደ በረከት ስምዖን በመወርወር ማጠቋቆሩ ያመጣውን ውጤት እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- “በሂደት አቶ አርከበ ይዞ ብቅ ያለው መቀስቀሻ የካድሬውን እና አባሉን ቁስል የነካ በመሆኑ ተቀባይነት አገኘ፡፡ በትግራይ ፕሮፓጋንዳ እና ድርጅት ተመድበው የሚሰሩ ቁልፍ ካድሬዎች ተቀላቀሉት፡፡” (ገፅ 26)
ይህንን ተከትሎ ወትሮም በደፋር ንግግሯ የምትታወቀውና አንጋፋ ታጋዮችን ሳይቀር በቁጣ የምታስረግደው ቀዳማዊት እመቤት የሰነዘረችው የመልስ ምት በመጽሐፉ ላይ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡- “ወ/ሮ አዜብ በበኩሏ አርከበና ቡድኖቹ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ክስ ይዛ ብቅ አለች፡፡ አርከበ በሚስቱና ቤተሰቦቹ የያዘውን ንብረት በመረጃ አስደግፋ አራገበች፡፡ ላውንደሪ ቤት፣ ፋርማሲ፣ ክሊኒክ፣ ሱፐር ማርኬት፣ መስታወት ማስመጣትና መሸጥ…፡፡ በትግራይና አዲስ አበባ የተፈጠሩት አዳዲስ ባለሀብቶች የአርከበና ቡድኖቹ እንደሆኑ በስም ዘርዝራ አሳወቀች፡፡ ስዬ በታሰረበት የሌብነት ወንጀል አርከበ እጁ እንደነበረ፣ በተለይም የስዬ ወንድም ለገዛቸው በርካታ መኪናዎች ቅናሽ እንዲያገኝ ማግባባቱን የፈፀመው አርከበ መሆኑን አጋለጠች፡፡” (ገፅ 26)
እዚህ ጋ አቶ ኤርሚያስ ‹‹አርከበ በሚስቱና በቤተሰቦቹ…›› ስለያዛቸውና አዜብ መስፍን በስም እየጠራች አጋለጠች ስላላቸው የንግድ ድርጅቶች በስም አንድ በአንድ እየጠቀሰ ይፋ ቢያደርግልን ኖሮ መረጃው ምሉዕ (ከ‹ኮሪደር ሀሜት› የዘለለ) ይሆን ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ከሁሉም ቁጭታችንን የሚያንረው፣ ደራሲው የንግድ ተቋማቱን ባለቤቶች በስም መጥቀስ እየቻለ (አቀራረቡ ለይቶ እንደሚያውቅ ያሳብቃልና) በደፈናው ያለፈው ወንጀል (ሕገ-ወጥ ዘረፋ) ይህ ብቻ አለመሆኑ ሲገባን ነው፤ በዚሁ ገፅ ዝቅ ብሎ የሰፈረው እንዲህ ይላልና፡- “በወቅቱ ሁለቱም ቡድኖች ‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት፣ የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም› የሚል ፖሊሲ ቀርፀው የህወሓት ባለሀብቶችን ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህ ፖሊሲ ምክንያት በአንድ ሌሊት ከሹፌርነት ወደ አስመጪና ላኪነት፣ ከጋራዥ ሰራተኛነት ወደ መኪና ዕቃ መለዋወጫ አስመጪነት፣ ከታጋይነት ወደ ሪል እስቴት ባለቤትነት፣ ከወታደርነት ወደ ፋብሪካ ባለቤትነት፣ ከህወሓት ምድብተኛ ካድሬ ወደግል ባንክ ከፍተኛ አክሲዮን ባለድርሻነት የተቀየሩ ሰዎችን መስማት የተለመደ ነበር፡፡” (ገፅ 26) እነዚህ ‹‹ተላላኪ›› እና ‹‹ሹፌር›› ባለሀብቶችን በስም አለመጥቀሱ ያስቆጫል፤ በተለይም ለመረጃው ከነበረው ቅርበት አኳያ ይሄ ጉዳይ እንደተራ ነገር በደፈናው ባይታለፍ ኖሮ፣ ለተቃውሞው ስብስብ በዋናነት ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኘቱ አይቀሬ ነበር፡፡
የመጀመሪያው በጅምላ ህወሓት፣ መላው ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪን ተጠቃሚ ያደረገ የሚመስለው ኢትዮጵያዊ ስህተቱን እንዲያጠራ ስለሚያስችለው፣ በድርጅቱ እና በብሔሩ መሀከል ያለውን ነጭና ጥቁር ልዩነት እንዲያስተውል ይረዳው ነበር፤ ሌላው ደግሞ እነዚህን በፖለቲካ ውሳኔ ወደሀብት ማማ የወጡትን ግለሰቦች የትላንት ማንነት አብጠርጥሮ የሚያውቀው ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ… የዘረፋ ወንጀላቸውን ተፀይፎ በኢኮኖሚያዊ ማግለል (ሸቀጦቻቸውን ባለመግዛትም ሆነ አገልግሎታቸውን ባለመጠቀም) በተቃውሞ ጎራ እንዲሰለፍ ገፊ-ምክንያት ይሆነው ነበር የሚለው ጭብጥ ነው፡፡ ‹‹የመለስ ትሩፋቶች›› መጽሐፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከመጋረጃው ጀርባ ስለተፈፅሙ ህልቆ-መሳፍርት ያሌላቸው አሳፋሪ የህወሓት ሕገ-ወጥ ድርጊቶች እና እብሪቶችን ተንትኖ አስነብቦናል፡፡ ከእነዚህ መሀልም የስምንቱ ኮሎኔሎች ‹‹ጀብድ››ን እዚህ ጋ መጥቀሱ አግባብነት አለው ብዬ አምናለሁ፤ ከ268-269 ባሉ ገፆች እንደተተረከው፣ በምርጫ 97 ማግስት በአንዱ ዕለት በወታደራዊ የደንብ ልብስ የተንቆጠቆጡ ስምንት ከፍተኛ መኮንኖች በሶስት ሄሌኮፕተር ተሳፍረው አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ፤ በቀጥታም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ወደነበረው አባተ ስጦታው ቢሮ በማምራት፣ መሬት እንደሚሰጥ መረጃ ደርሷቸው ከጦር ግንባር እንደመጡ ይነግሩታል፤ እያንዳንዳቸውም ‹‹ዘመቻ ፀሀይ ግባት የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ኃየሎም አርአያ የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ዛላአንበሳ የቤት ማሕበር››… የሚል እና መሰል የማህደር ስያሜ ያላቸው የአስራ ሁለት መኮንኖች ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘ ወረቀት ይሰጡታል፤ እንደ ብራ መብረቅ ድንገት ባጋጠመው ክስተት ክፉኛ የተረበሸው ከንቲባም እንዲህ ያለ መመሪያ እንዳልወረደ ለማስረዳት ሲሞክር፣ ለዚህ ዓይነቱ እሰጥ-ገባ ጊዜ ያልነበራቸው የጦር አበጋዞቹ አብረቅራቂ ሽጉጦቻቸውን በመምዘዝ ግንባሩ ላይ ደቅነው በወቅቱ ፋሽን በነበረው ኢህአዴጋዊ ፍረጃ ‹‹የቅንጅት ተላላኪ መሆንህን ደርሰንበታል››፣ ‹‹ኢህአዴግ እንዲሸነፍ ያደረጋችሁት እንዳንተ ያሉ ሰርጎ-ገቦች ናቸው››፣ ‹‹እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳለን››… የሚሉ ማስፈራሪያዎችን አዥጎድጉደው በማስጠንቀቅ ነፍስ-ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ወጥረው ይይዙታል፤ ይህን ጊዜ የህወሓት አባል የሆነው ምክትል ከንቲባው ነጋ በርሔ፣ የአባተን ቢሮ በርግዶ ሳይታሰብ ዘው በማለቱ፣ አንደኛው ኮሎኔል ያነጣጠረውን መሳሪያ ከአይን በፈጠነ ቅፅበት አዙሮ ይደቅንበታል፡፡ ሁኔታውን ከጉዳይ ያልጣፈው ነጋ በርሔም ባለሽጉጦቹን የጦር አበጋዞች በባዶ እጁ እንዲህ ሲል ተጋፈጣቸው፡-
“ነፍጥ ከእናንተ በፊት አንግበን ተራራ ደርምሰናል፡፡ የምታስፈራሩትን ሂዱና ሌላ ቦታ አስፈራሩ!”
ከፍተኛ መኮንኖቹም በድንጋጤ መሳሪያዎቻቸውን በመዘዙበት ፍጥነት ወደአፎቱ መልሰውና የምክትል ከንቲባውን የስድብ ውርጅብኝ በፀጥታ አዳምጠው ሲያበቁ፣ አባተን ይቅርታ እንዲጠይቁት ይታዘዛሉ፤ እንዲያ በጥንካሬያቸው ለማንም የሰው ልጅ የማይበገሩ መስለው ሲንጎማለሉ የነበሩት ቆፍጣናዎቹ ኮሎኔሎች ባንዴ እንደፊኛ ተንፍሰው በፍርሃት የታዘዙትን ይፈፅማሉ፤ ከዚህ በኋላም ህወሓቱ ነጋ በርሔ በተረጋጋ አንደበት ዋናው ከንቲባውም ጭምር እንዲሰማ ድምፁን አጉልቶ የሚከተለውን ‹‹ምርጥ›› ምክር ለገሳቸው፡ –
“ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ጥያቄያችሁን ብታቀርቡ ኖሮ አባተ እንኳን ቤተሰባችሁን ጥላችሁ ግንባራችሁን ለጥይት ለምትሰጡት ቀርቶ ለሌላውም አይጨክንም፡፡ ያውም ከቀናት በኋላ ጠላት (ቅንጅት) ተረክቦ ለሚዘርፋት አዲስ አበባ!” (ገፅ 255) ከንቲባውም መሬቱን ፈቀደ፤ ነጋም ወደ መቀሌ እንዲዘዋወር ተደርጎ፣ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴን እና የትግራይ ክልል ካቢኔን ተቀላቀለ፤ ከጊዜ በኋላም በበረከት ስምዖን በተመራ ግምገማ ላይ በአስቸኳይ አዲስ አበባ መጥቶ ይህንን ጉዳይ እንዲያስረዳ ቢጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ ይቀራል፡፡ ደራሲውም ‹‹ዘመን አለፈና አዲሱ ለገሰን ለማገዝ ኢህአዴግ ቢሮ የሥልጠና ማዕከል በምክትል ሚኒስትርነት ማዕርግ ተመደበ›› ሲል የሆሊውድ ፊልምን የሚያስንቀውን ታሪክ ይደመድማል፡፡ በርግጥ አባተም ቢሆን ይህ አስፈሪ ገጠመኙ እንደድንቅ ቃለ-ተውኔት ሁሉ፣ በህወሓት መሪዎች ተደርሶ በኮሎኔሎቹ እና በነጋ የተተወነ መሆኑን ለመረዳት በርካታ ወራት እንደፈጀበት
ተጠቅሷል፡፡
በሌላ ምዕራፍ ደግሞ፤ በምርጫው ቀን እኩለ ሌሊት ተቋቁሞ፣ በአርከበ እቁባይ እና በጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲመራ የተደረገው ‹‹የፖለቲካ ፀጥታ ጥምር ኮሚቴ››፣ ከ1978 ዓ.ም በፊት ወደ ትግል የገቡና ማዕረጋቸው ከኮሎኔል በላይ የሆነ የህወሓት መኮንኖች ቦሌ ላይ መሬት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን አስነብቦናል፡፡ በአናቱም፣ ከኮሎኔል በታች ያሉ የህወሓት ታጋዮች በሌሎች ማስፋፊያ ከተሞች መሬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ሁኔታ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲህ ያወጋናል፡- “…ወሬው ባድመና ጾረና ጦር ግንባር ድረስ ተዳረሰ፡፡ ወታደራዊ መኮንኖቹ ምሽጋቸውን እየለቀቁ በጦር ሂሊኮፕተሮች ጭምር እየተሳፈሩ አዲሳባን ወረሯት፡፡ የክፍለ ከተሞች ግቢ አቧራ በጠጣ የኮከብ ጋሻና ጦር ክምር የተሸከመ ካኪ ተጥለቀለቀ፡፡” (ገፅ 255-256) ዘመነኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ‹‹…አንዳንድ እንሰሳት ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል ያልተፃፈ ሕግ ማደሩን ከውስጥ-አወቅ ምስክርነት የምንረዳው ከህወሓት ውጪ ያሉት ኢህአዴግን የመሰረቱ ድርጅቶች የአመራር አባላት ብቻ የወሰዷትን መሬት በግምገማ እንዲመልሱ መገደዳቸው በዚሁ መጽሐፍ መስፈሩን ስናስተውል ነው፡፡ በወቅቱም በግምገማው ፊት-አውራሪ በረከት ስምዖን የተዘጋጀ ‹‹ከምርጫው በኋላ የድርጅታችንን ስም ያጎደፉና የሕዝቡን ቅሬታ ያባባሱ ተግባራት›› የሚል ሃያ ገፅ ሰነድ የመነሻ ሃሳብ ሆኖ ቀርቦ ነበር፤ የግምገማው ውጤትም የተዘረፈ መሬት ማስመለሻ ፎርምን ህወሓት ያልሆኑ ከ600 በላይ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንዲሞሉ አስገድዶ ተጠናቅቋል፡፡
ለአብነትም ደራሲው ‹‹ለታሪክ የተቀመጠው የይቅርታ ፎርም›› ብሎ በመጽሐፉ ያሰፈረውንና በአንድ የብአዴን አመራር የተሞላውን እንደወረደ ልጥቀሰው፡- “ለቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር እኔ ህላዊ ዮሴፍ ድርጅቴ ኢህአዴግና መንግስት የጣለብኝን አደራና ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመሬት ወረራ ላይ በመሰማራት አንድ መሬት ወስጃለሁ፡፡ በመሆኑም ይህን ያለአግባብ የወሰድኩትን መሬት አስተዳደሩ እንዲረከበኝ በማክበር እጠይቃለሁ፡፡ ድርጅቴ ኢህአዴግና በእሱ የሚመራው መንግስትም ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ከእንግዲህ ወዲያ በየትኛውም የድርጅቴንና የመንግስት ስም በሚያጎድፍ ተግባራት ላለመሰማራት ቃል እገባለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር ህላዊ ዮሴፍ
ግልባጭ
ለአዲስ አበባ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለቦሌ ክፍለ ከተማ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለኢህአዴግ ጽ/ቤት” (ገፅ 257)
የሆነው ሆነ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ መጽሔት ላይ እንዲህ በቀላሉ ጠቅሰን የማንጨርሳቸውን በርካታ አይን ያወጡ ድርጅታዊ እና ግለሰባዊ ዘረፋዎችን ልባችን ቀጥ እስኪል ድረስ አስነብቦናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዛሬ በየመድረኩ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›፣ ‹መለስ መሲህ ነው!›… አይነት ፕሮፓጋንዳ በማድመቅ ግንባር-ቀደም እየሆነ የመጣው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ራሱ የዘረፋው ተቋዳሽእንደነበረ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡-
“ከሁሉም የሚያሳዝነው ሀገራችንን በዓለም መድረክ በማስጠራቱ የምንወደው ኃይሌ፣ በአስታራቂ ሽማግሌነቱ የምናመሰግነው ኃይሌ፣ በዓለም አደባባይ አልቅሶ ያስለቀሰን ኃይሌ ‹ኃይሌና አለም ሪል ስቴት› በሚል የድርጅት ስም በመስከረም 7/1998 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ 50,000 ካሬ ሜትር ሕጋዊ ሰውነት በነዋሪው ድምፅ ከተገፈፈው አርከበ እቁባይ እጅ ወስዷል፡፡ መቼም ታላቁ ሯጭ እየተካሄደ ያለው ውንብድና አዲስ አበባን ማጥፋት እንደሆነ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡” (ገፅ 400-401)
…የወዶ ተሳዳጁ የኦህዴድ ካድሬ፣ ከሁለት ዓስርታት በላይ ሲነገርና ሲፃፍ የነበረውን ርዕሰ-ጉዳይ ለማጠናከር በርካታ የመጽሐፉን ገጾች ሰውቷል፡፡ ይህ የህወሓት ብቸኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጠቅላይነት ትርክት፣ ገዢ የተቃውሞው መከራከሪያ መሆኑን በሚገባ የሚያውቀው ኤርሚያስ፣ በተለይም ባገለገለበት አዲስ አበባ ዙሪያ ያልተገለጡ የሚመስሉ ሁነቶችን አስተሳስሮ ለመተረክ ጥሯል፡፡ በርግጥ ለእግረ-መንገድ ያህል አንድ ጥርጣሬ ጥለን እንለፍ፤ ይህን መስመር አብዝቶ ማብራራት፣ ተደማጭነትን እና የፖለቲካ ሁለተኛ ዕድልን እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ከመረዳቱ አኳያ፤ የተባሉትን በምልዐት መቀበሉ ጥቂትም ቢሆን አስቸጋሪ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ አልፎም፣ የትግሪኛ ተናጋሪውን እና ህወሓትን ቀላቅሎ ወደመመልከት እንዳያሻግረን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረጉም ሊታወስ ይገባል፡፡
(በሚቀጥለው ሳምንት ይህንኑ መጽሐፍ በማጣቀሻነት እያወሳን፣ የህወሓትን የፖለቲካ የበላይነት እና ጠቅላይነት የሚያሳዩ ወጎችን እንዳስሳለን)

Saturday, September 20, 2014

UN Experts Urge Ethiopia To Stop Using Anti-Terrorism Legislation To Curb Human Rights

September19,2014

ethiopian demo 1
GENEVA – A group of United Nations human rights experts* today urged the Government ofEthiopia to stop misusing anti-terrorism legislation to curb freedoms of expression and association in the country, amid reports that people continue to be detained arbitrarily.
The experts’ call comes on the eve of the consideration by Ethiopia of a series of recommendations made earlier this year by members of the Human Rights Council in a process known as theUniversal Periodic Review and which applies equally to all 193 UN Members States. These recommendations are aimed at improving the protection and promotion of human rights in the country, including in the context of counter-terrorism measures.
“Two years after we first raised the alarm, we are still receiving numerous reports on how the anti-terrorism law is being used to target journalists, bloggers, human rights defenders and opposition politicians in Ethiopia,” the experts said. “Torture and inhuman treatment in detention are gross violations of fundamental human rights.”
“Confronting terrorism is important, but it has to be done in adherence to international human rights to be effective,” the independent experts stressed. “Anti-terrorism provisions need to be clearly defined in Ethiopian criminal law, and they must not be abused.”
The experts have repeatedly highlighted issues such as unfair trials, with defendants often having no access to a lawyer. “The right to a fair trial, the right to freedom of opinion and expression, and the right to freedom of association continue to be violated by the application of the anti-terrorism law,” they warned.
“We call upon the Government of Ethiopia to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism,” the experts said.  “Let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carry out their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.”
The human rights experts reiterated their call on the Ethiopian authorities to respect individuals’ fundamental rights and to apply anti-terrorism legislation cautiously and in accordance with Ethiopia’s international human rights obligations.
“We also urge the Government of Ethiopia to respond positively to the outstanding request to visit by the Special Rapporteurs on freedom of peaceful assembly and association, on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment and on the situation of human rights defenders,” they concluded.
(*) The experts:  Special Rapporteur on the promotion and protection of human rights and fundamental freedoms while countering terrorism, Ben Emmerson; Special Rapporteur on the rights to freedom of peaceful assembly and of association, Maina Kiai; Special Rapporteur on the promotion and protection of the right to freedom of opinion and expression, David Kaye; Special Rapporteur on the situation of human rights defenders, Michel Forst; Special Rapporteur on the Independence of Judges and Lawyers, Gabriela Knaul; Special Rapporteur on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment, Juan Méndez.
A full version of this press release is available in English via OHCHR.

የቀድሞው “የአብዮት አድናቂ” ኑዛዜ (“Confession of the Ex-Revo” ) አዘጋጅ Zone 9


በፍቃዱ ዘ ኃይሉ
 
ርዕሱን  አላስታውሰውም ‘ንጂ እ.ኤ.አ በ2011 Arab Uprising በመባል የሚታወሰውን አብዮትተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን ፌስቡከኞችም (በተለይ ዲያስፖራ የሚገኙ) ግንቦት 20 ላይ (ልክ በኢሕአዴግ የ20ኛ አገዛዝ ዕድሜ)   “Anger day” በሚል በፌስቡክ አብዮትመጥራታቸውን ተቃውሜ አንዲት ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ በዓመቱ ደግሞ ‹‹ አብዮት ወረት ነው›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ አብዮት ለማስነሳት ፍላጎት ያላቸው በርካቶች እንዳሉ ገልጬ ነገር ግን ይጎድላቸዋል የሚባሉትንነገሮች ዘርዝሬ ጽፌ ነበር፡፡ በነዚህ ሁለት ጽሑፎች ላይ፣ ላዩን አብዮትን የተቃወምኩ ቢመስልም እውነታው ግን ጽሑፎቹ በተጻፉበትወቅት ሕዝቡም፣ ተቃዋሚ ልሂቃኑም፣ ሁኔታዎቹም ለአብዮት ዝግጁ አይደሉም የሚል ዝንባሌ ማሳየቱ ነበር፡፡
ከሌላ ዓመት በኋላደግሞ ‹‹ስለለውጥ›› በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎችን በ‹‹ዞን 9›› ላይ በግል ተነሳሽነት ማስፈር ጀምሬ ነበር፡፡ ጽሑፉን የጀመርኩት ‹‹ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በምርጫ ይለቃል?›› በሚል ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹አይለቅም›› የምልባቸውን ምክንያቶች ካስቀመጥኩ በኋላ የለውጥ አማራጭ የምላቸውን (አብዮት፣ሰላማዊ አለመታዘዝ /civil disobedience/ የመሳሰሉትን) በየዘርፉ እየቀነጫጨብኩ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ ከዚያም ‹‹የለውጥ ፍርሃት››፣ ‹‹የሥርዓት ለውጥ እና ሃይማኖት››፣ ‹‹የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት እና የማኅበራት ሚና›› የሚሉ ርዕሶችን በማንሳት በሐሳቦቹ ላይ በሐቀኝነት ለመከራከር ጥረት አድርጌያለሁ (ከዚህ በላይ አልገፋሁበትም እንጂ)፡፡ በበኩሌ ስለአብዮት በደንብ ያነበብኩትም፣ ያሰብኩትም፣ የጻፍኩትም፣ የተረዳሁትም ያኔ ነበር፡፡ ያኔ በአብዮት ላይ የነበረኝ እምነት ተሸርሽሮ ግማሽ ደርሶ ነበር፡፡ ተንጠፍጥፎ ያለቀው ግን አሁንም በዓመቱ (በ2006 አጋማሽ) ነው፡፡ አንባቢ ከአብዮት አድናቂነት ወደ ዝግመተ ለውጥ አራማጅነት (በ ‹‹ያ ትውልድ›› ሰዎች አጠራር ከRevo ወደ Sabo) የተሸጋገርኩበትን የሐሳብ ዳገት (ከፈለጋችሁ ቁልቁለት በሉት) ይረዳ ዘንድ በመጠኑ ዘርዘርአድርጌ ማስረዳት አለብኝ፡፡ (ታዲያ አብዮት አድናቆቱም ቢሆን ከወረቀት እንዳላለፈ ልብ በሉልኝ)፡፡
እነዚያን ተከታታይ ጽሑፎች በጻፍኩበት ሰሞን  ‹አብዮት ‹‹እቆጣጠረዋለሁ›› ብለው ያሰቡትንነገር ግን ድንገት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን የሚችል እሳትን መለኮስ› እንደሆነ እያሰብኩ ባለሁበት ሰሞን ግብጻውያን ሙርሲን ለመጣል ያምጹ ጀመር፡፡ የግብጹ ድጋሚ አመጽ (አብዮት) በጣም የተዘበራረቀ ስሜት ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ሙርሲ እኔ በግሌ ከማምንባቸውና ቋሚም ከሆኑ የዲሞክራሲ መርሆች እያፈነገጠ ነበር፡፡ ስለዚህ የግብጾች ማበይ ምክንያታዊ ነው ብዬ አምኛለሁ፤ እንዲያውም ሕዝብ አንዴ ‹ከነቃ አይሆንም ዕቃ› ብዬ ነበር፡፡ የግብጽ ሕዝብ የሚፈልገውን ዓይነት ሥርዓት እስከሚያገኝ እያበየ ይቀጥላል የሚል ግምት ነበረኝ- ልክ እንደ ፈረንሳዮቹ ተከታታይ አብዮቶች፡፡  ነገር ግን የግብጽ ሕዝብ እያበየ ቢቀጥልም እንኳን የፈለገውን ላያገኝ እንደሚችል የተረዳሁት ወታደራዊ ክንፍ ቀስ በቀስ አገሪቱን በአብዮቱ ተከልሎ ሲጠቀልላት ስመለከት ነበር ፡፡ ከአገራችን የደርግ አመጣጥ አልለይ ብሎኝ ‹አብዮቶች ሁሉ አንድ ናቸው እንዴ?› እስከሚያስብል ድረስ ተመሳስሎብኝም ነበር፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ እና ፕሬሶች በአንዳች ተዋስኦ ይናጡ ጀመር፡፡ ተዋስኦው የተጀመረው የጃዋር መሐመድን ‹ኦሮሞ ቅድሚያ›(Oromo First) የአልጄዚራ ምላሹን ተከትሎ ነበር፡፡ ብዙዎች ይሄን ወቅት የሚያስታውሱት እንደአላስፈላጊ የንትርክ ወቅት ቢሆንም፣በበኩሌ ብዙዎች ቆም ብለው አቋማቸውን እና የአቋማቸውን መሠረት እንዲፈትሹ፣ በታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ኩነቶች ላይ ንባባቸውን እንዲቀጥሉ ያስታወሰ መልካም አጋጣሚ ነው ባይ ነኝ፡፡ ይህ አጋጣሚ በስመ ተቃዋሚ (dissent) የአንድ ኢሕአዴግን ከሥልጣን መውረድ ብቻ እንደ ለውጥ ግብ አድርገን በጋራ ስንንቀሳቀስ የነበርን ተቃዋሚ ግለሰቦች እና ቡድኖች እርስ በርስ ያሉትን ልዩነቶች እና ልዩነቶቻችንን የምናቻችልባቸውን መንገዶች እንድናስተውል መንገድ ፈጥሯል፡፡ ብዙዎቻችን የማንፈልገውን እንጂ የምንፈልገው ምን እንደሆነ በቅጡ እንደማናውቅ፣ትግላችን ከመርሕ ይልቅ በእልሕ እንደሚመራ ያጋለጠ፣ ራሳችንን እንድንገመግም ያስገደደ አጋጣሚ ነበር፡፡
ከዚህ ድንጋጤ ውስጥነው ‹አምባገነን መሪዎቻችን ከሕዝብ ጉያ የወጡ› የአስተሳሰብ ችግር የወለዳቸው የመሆናቸው ሐቅ ዘልቆ የገባኝ (ወይም genuinely comprehend ማድረግ የተቻለኝ) ስለዚህ አብዮት ሲፀነስ ዓላማው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ የተለወጠ መሪ ማስቀመጥ ቢሆንም ሲወለድ ግን አንድም ያልተለወጠ ሕዝብ የተለወጠ መሪ መውለድ ስለማይችል፣ አንድም ደግሞ የተለወጠ መሪ እና ያልተለወጠ ሕዝብ  መዋሐድ ስለማይችሉ፣ አብዮቱ (ዓላማው) ይጨናገፋል፡፡
በዚሁ ጊዜ ነበር የቅርብጊዜ ምሳሌያችንን የአረብ አብዮትን መልሼ በወፍ በረር ለመገምገም የተገደድኩት፡፡ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ…. ከተሳካው የከሸፈው፣ከለማው የወደመው ይበዛል፡፡ የአምባገነን መገርሰስ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፤ ከነዚህኞቹ ለውጦች ይልቅ የእኛው ፊውዳሊዝምን ገርስሶ- ወታደራዊ አምባገነንነትን ያመጣው አብዮት የተሻለ ኪሳራ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡ (እዚህጋ በኢሕአፓ፣ መኢሶን እና ሌሎችም የደርግ ፓርቲዎች መካከል የተደረገው የድኅረ አብዮት የሥልጣን ሽኩቻ ሳቢያ የጠፋውን ሕይወት ሳንቆጥር መሆኑ ነው፡፡) ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ በብርቱካናማ አብዮቷ የምትደነቀው ዩክሬን አበየች፡፡(‹“የተውኩትን ነገር ተነግሬ፣ ተመክሬ ባገር ምን ጎትቶ አመጣብኝ፣ የአብዮትን ነገር?" Another revolution? ብዬ ትዊት አድርጌም› ነበር) አብዮቷ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የአካሏ ክፋይ የሆነችው ክሬሚያን በማሳጣት ይጀምራል፡፡ ምዕራብ ዩክሬናውያን ሲያብዩ ‹የአገራችን መንግሥት ከምዕብራባውያን ይልቅ ምስራቃውያን (ራሺያ….) አደላ› ብለው ቢሆንም በውጤቱ ግን ጭራሽ ራሺያ ክሬሚያን ጠቅልላ አረፈችው፡፡ልብ በሉ! አብዮቱ ከተነሳበት 360 ዲግሪ ዞሮ ተጠናቀቀ፡፡ ለነገሩ አልተጠናቀቀም፤ አሁን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ተሸጋግሯል፡፡
ይኼኔ ነበር በግል ጦማሬ ላይ ጥር 2006 ‹‹Are revolutions meant to be betrayed?›› ብዬ በመጠየቅ የጻፍኩት፡፡ ዜጎች አብዮትን ሲጀምሩት የማይታዩ ችግሮች ሲጨርሱት የሚስተዋለው ‹ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም› ነበር የጽሑፌ አንኳር ሐሳብ፡፡ ‹‹ሌባ›› ያልኳቸው  በሕዝባዊ አብዮት ስም የግል ሕልማቸውን የሚያሳኩ አጀንዳ ያላቸውን ቡድኖች (interest groups) ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ እውነታ ደግሞ እነዚህ ዓይነቶቹ interest groups ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በአብዮት ለውጥ አማጭነት ተስፋ ስቆርጥ የመጀመሪያ ጥያቄዬ ‹‹ሳያብዩ ለውጥ ማምጣት ይቻላል?›› የሚል ነበር፡፡ የመጀመሪያ መልሴ ‹‹እንግሊዝ›› ነበረች፡፡ የእንግሊዝ ሕዝብና መንግሥት በሕግ የበላይነት ላይ ለማንም ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ የዓለምን ግማሽ በገዙበት ጊዜም አሁንም አብየው አያውቁም- እንግሊዛውያን፡፡ ምክንያቱም ተወያይተው ችግራቸውን መፍታት ይችላሉ፡፡ ሕዝብና መንግሥት ሲለወጡ ሁሉም በሰላም ይካሄዳል፡፡
ይህንን የመጨረሻ አቋሜን ያውቅ የነበረ ወዳጄ፣ ‹‹እህ አሁንስ?›› አለኝ ‹አብዮት ልታስነሳ አሲረሃል› ተብዬ ተጠርጥሬ ከታሰርኩ በኋላ  ሊጎበኘኝ መጥቶ፡፡ ‹‹አየኸው አይደል፣ ያለአብዮት ለውጥ እንደማይመጣ?›› የሚገርመው፣ የኔና የጓደኞቼ በሕገ-ወጣዊ ማንአለብኝነት መታሰርና፣ የመንግሥት (ፖሊስ) ተጠያቂነት ማጣት ውስጥም ሕዝባዊ አለመለወጥ ነው የሚታየኝ፡፡ መንግሥት አሁንም ቢሆን የሚያስጨንቀው ‹‹የውጭ ኃይሎች ጫጫታ›› እንጂ የውስጥ ሰዎች ጥያቄ አይደለም፡፡ በእኛ ላይ የደረሰው (ሐሳብን በመግለጽ ጦስ መታሰር) በሌሎች ላይ ሲደርስ የነበረ፣ እየደረሰ ያለ ፣ ወደፊትም የሚደርስ መሆኑ ቢታወቀውም ሕዝባችን ግን ‹‹መብቴን ማስጠበቅ አለብኝ›› ከማለት ይልቅ ‹‹ዝም ብል ይሻለኛል›› (ጎመን በጤና) mode ውስጥ ነው፡፡ ሕዝብ ገና አልተለወጠም፤ የለውጥ ጣዕሙም የገባው አይመስልም፡፡ ሌሎች ሰላማዊ የትግል አማራጮችም ገና በኢትዮጵያ አልተሞከሩም፡፡ ሕዝቡ ጣዕሙን የማያውቀውን ለውጥ ከመስጠት በፊት ደግሞ የለውጡን ጣዕም አውቆ ለውጡን ራሱ ጠይቆ፣ ራሱ እንዲያመጣው ማንቃት ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ እንግሊዛውያኑ እንደሚሉት ‹ጋሪው ከፈረሱ ቀድሞ› አይሆንም! ለወዳጄም ይህንኑ ሃሳቤን ነበር የነገርኩት፡፡
ለነገሩ ይህንን ሁሉአልኩ እንጂ ክፍሉ ታደሰ በ‹‹ያ ትውልድ›› (ቅጽ 1) ላይ  ‹ኃይሌፊዳ በ1965 በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ አብዮት ይነሳል ብዬ አልገምትም ብሎ ነበር› እንዳለው ካልሆንኩ በቀር እኔም በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይነሳል የሚል ምንም ግምት የለኝም፤ በመጨረሻም በአቤ ቶክቻው ዋዘኛ አባባል ‹‹ካጠፋሁ፣ልጥፋ!››

የአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ 10 ሚሊዮን ብር ታገደ


  • 2878
     
    Share
(አዲስ አድማስ) ሙያው ቴዎድሮስ ተሾመና በደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ መካከል በተመሰረተው የመብት ይገባኛል ፍትሃብሄር ክርክር፣ ፍ/ቤት በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ላይ የ10 ሚሊዮን ብር እግድ ከትናንት በስቲያ አስተላለፈ፡፡ ከሳሽ ደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ፤ ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም ለፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፤ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለእይታ ያበቃው “ሦስት ማዕዘን” የተሰኘ ፊልም ጻሪክ በ2000 ዓ.ም ካሳተሙት “ፍቅር ሲበቀል” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሃፍ የተወሰደ ነው የሚል አቤቱታ አሰምተዋል፡፡
tewedros teshome
“ሦስት ማዕዘን” የተሰኘው ፊልም መፅሃፋቸው ታትሞ ከወጣ ከ5 ዓመት በኋላ ለዕይታ እንደበቃ በክሳቸው የጠቆሙት ከሳሽ፤ አርቲስት ቴዎድሮስ ያለደራሲው ፈቃድ የቦታና ገፀ-ባህርያት ስሞችን በመቀያየር ብቻ የመፅሀፉን መሰረታዊ ጭብጥና የታሪክ ፍሰት በፊልሙ ውስጥ መጠቀሙን አመልክተዋል፡፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ፊልሙን በተደጋጋሚ ለተመልካች በማሳየት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በክስ ማመልከቻው ላይ የጠቆሙት ደራሲው፤ ተከሳሽ በፈፀሙት ተግባር ከፍተኛ የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸውና ፊልሙ የመፅሃፉ ቀጣይ ህትመት ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ በመጠቆም የ10 ሚሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል፡፡
ከሳሽ የመፅሃፉን ጭብጥ፣ መቼትና የተለያዩ ታሪኮች ከ“ሶስት መአዘን” ፊልም ታሪክ ጋር በማመሳከር ለፍ/ቤቱ በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው መስከረም 6 በዋለው ችሎት፤ የክስ ማመልከቻው ለተከሳሽ ደርሶ መልስ እንዲሰጥበትና የከሳሽ ምስክሮች እንዲቀርቡ ለጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ጳጉሜ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፉት ማመልከቻ የ10 ሚሊዮን ብር ክስ ማቅረባቸውንና ቢፈረድላቸው ፍርዱን የሚያስፈፅሙበት ንብረት እንደማያገኙ በመጥቀስ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች ካላቸው ገንዘብ ላይ 10 ሚሊዮን ብር እንዲታገድላቸው ማመልከታቸውን ያስታወሰው ፍ/ቤቱ፤ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በዘመን ባንክ ከሚገኘው የሂሳብ ደብተራቸው 10 ሚሊዮን ብር እስከ ቀጣዩ ቀጠሮ ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ፊልሙን በተደጋጋሚ ለተመልካች በማሳየት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በክስ ማመልከቻው ላይ የጠቆሙት ደራሲው፤ ተከሳሽ በፈፀሙት ተግባር ከፍተኛ የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸውና ፊልሙ የመፅሃፉ ቀጣይ ህትመት ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ በመጠቆም የ10 ሚሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል፡፡
ከሳሽ የመፅሃፉን ጭብጥ፣ መቼትና የተለያዩ ታሪኮች ከ“ሶስት መአዘን” ፊልም ታሪክ ጋር በማመሳከር ለፍ/ቤቱ በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው መስከረም 6 በዋለው ችሎት፤ የክስ ማመልከቻው ለተከሳሽ ደርሶ መልስ እንዲሰጥበትና የከሳሽ ምስክሮች እንዲቀርቡ ለጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ጳጉሜ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፉት ማመልከቻ የ10 ሚሊዮን ብር ክስ ማቅረባቸውንና ቢፈረድላቸው ፍርዱን የሚያስፈፅሙበት ንብረት እንደማያገኙ በመጥቀስ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች ካላቸው ገንዘብ ላይ 10 ሚሊዮን ብር እንዲታገድላቸው ማመልከታቸውን ያስታወሰው ፍ/ቤቱ፤ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በዘመን ባንክ ከሚገኘው የሂሳብ ደብተራቸው 10 ሚሊዮን ብር እስከ ቀጣዩ ቀጠሮ ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
Ze-Habesha

በሰሞኑ የኢህአዴግ ስልጠና ላይ የመምህራኑ ምላሽ


    ከመስከረም 5,2007 . ጀምሮ መንግስት የአቅምግንባታ እያለ የጠራው ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል::ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት 1983 . ጀምሮየተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወቅሲሆን የዘንድሮውም ከበፊቶቹ ምንም የተለየ ሀሳብያለተነሳበት እና ድግግሞሽ የበዛበት ብሎም ገዢውፓርቲ ለኢትዮጵያዊነት እና ለመምህርነት ሙያያለውን አይን ያወጣ ጥላቻ ያሳየበት ነበር::

ስልጠናው እንደተጀመረ መምህራኑን የማሰልጠን ድፍረቱን እና እድሉን ያገኙት አቶ ኤፍሬም ግዛው የተሰኙ የአዲስ አበባከተማ አሰተዳደር ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ናቸው:: አቶ ኤፍሬም በንግግራቸው ወቅት በተደጋጋሚ ሀገሪቷ ከየትኛውምዘመን በተለየ በኢኮኖሚያዊ እድገቱ እና ሰላም በማረጋገጡ ዘንድ ስኬታማ መሆን እንደቻለች ለማስረዳት ሞክረዋል::

እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ የኢህአዴግ ትልቁ ችግር እራሱን ሞቶ ከተቀበረውየደርግ ስርአት ጋር እያነጻጸረ ህዝቡን ለመሸወድ የሚያደርገው ቀቢጸ ተስፋ ነው:: እድገት ውድድር መሆኑን እናምናለን ሆኖምይህ ስርአት መወዳደር ካለበት ባላፉት 24 አመታት በእነጋና ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ከታዩት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊእድገቶች ጋር እንጂ ከሞተ ስርአት ጋር ሊሆን አይገባውም:: ሌላው የሰላም ጉዳይ ሰላም አንድ አይነት ትርጓሜ የለውምየጥይት ድምጽ ወይም የቦንብ ፍንዳታ አለመስማት ብቻውን ሰላም አለ ሊያስብል የሚችልበት ምንም አይነት መርህአይኖርም::

ማሰብ ለቻለ እና ህሊና ላለው ሰው አዛውንቶች እና ህጻናት ጎዳና ወድቀው መመልከት ሰላምን ይነሳልበሀገራቸው መኖርስላልቻሉ በስደት አለም የበረሀው ሙቀት የባህር ራት የሆኑት ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ መስማትም ሰላምን ይነሳልአንድየሚበላው ያጣ ህጻን ከውሻ ጋር ተሻምቶ ሲመገብ መመልከትም ሰላምን ይነሳል:: በአጠቃላይ በግልጽ የጥይት ድምስአለመስማት እንደስኬት ልንቆጥረው የሚገባ አይደለም ድምጽ ሳይሰማ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ጊዜ ይቁጠራቸው:: ግለሰብ ናቸው::

እኚህ ግለሰብ በተደጋጋሚ ነፍጠኛጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ በማለት መምህራኑን ብሎም ሰፊውን የሀገራችንንህዝብ ሲሳደቡ ውለው ከርመዋል ነገር ግን እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ በአሁኑወቅት በሀገራችን ያለው ብቸኛው ነፍጠኛጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ ለእኔ ብቻ ተዉት እያለ ያለው ኢህአዴግ ብቻእና ብቻ ነው::
ከዚህ ስልጠና ለመታዘብ እንደቻልነው ገዢው ፓርቲ ትልቅ የተማሩ ሰዎች እጥረት አለበት ይህንንም እራሱ ኢህአዴግ ሆንብሎ ያደረገው በመሆኑ እነደ መምህር የዚህችን ሀገር የነገ እጣ ፋንታ ስንመለከት ያስፈራል::

                                                                     በመጨረሻ እኛ መምህራን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥሪውንእያስተላለፈ ሌሎች አካላትም ከመምህራኑ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ይቆሙ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል::
ድል ለመምህራን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
መስከረም 10,2007 .
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ