Monday, September 15, 2014

በህወሀት እና በአጋር ፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ ነው


እስከ ጳጉሜ42006ዓ.ምድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት  ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: 


በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በአርበኞች ግንባር ቁጥጥር ስር ለመዋል እንደተቃረበ፣ በአመራሩ እንዝህላልነት ህዝቡ ከኢህአዴግ እየራቀ እና ለድርጅቱ ጀርባውን እንደሰጠ ከመድረክ ተገልጽዋል:: በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮች የተቀሰው አካባቢ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሚሆኑ አባላት እጥረት እንዳለ፣ ህዝቡ በተደጋጋሚ በአካባቢው አመራሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደሚያደርስ ገልጸው ይህም ሊሆን የቻለው በአካባቢው ያለው የሀይል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል::
1231607_10151872226524743_661233572_nበሌላ በኩል በብኣዴን እና በኦህዴድ ውስጥ የሚገኙ አባላት ድርጅታዊ ታማኝነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ በርካታ አባላት በየሄዱበት ሀገር ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን መጪው የ2007 ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶች አባላታቸውን ጠንክረው እንዲያንቀሳቅሱ በተጨማሪም የሚዲያው ክፍል ልማታዊ አርቲስቶች ወደ ህዝቡ ልብ እንዲገቡ መሰራት እንዳለበት ለዚህም እቅድ ተነድፎ በቅርቡ ለሚዲያው ክፍል ገቢ እንደሚሆን እና ስራው ተግባራዊ እንደሚሆን ከመድረክ ተገልጹአል::
በሌላ በኩል ህወሀት በ2007 ቴዎድሮስ አድሀኖምን የድርጅቱ ኮከብ በማድረግ ላቅ ብሎ ለመታየት የሚያደርገው ሙከራ በአንዳንድ የኦህዴድ እና የብአዴን አባላት ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ነገር ጸድቶ ትክክለኛ የህወሀት ስራ አስፈጻሚ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ደህዴን እንድሆነ ለማወቅ ተችሉአል::
በተያያዘ ዜና ህወሀት እና የተቃዋሚው ቡድን ለእርቀ ሰላም ይቀመጡ ዘንድ በአፍቃሪ ህወሀቶች ዘንድ ውስጥ ውሰጡን ስራ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣ ይህንንም ስራ በበላይነት ይዘው እየሰሩ ያሉት አቶ መነገሻ ስዩም እንደሆኑ በተጨማሪም አሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጥላሁን በየነ በቡድኑ ውስጥ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችልዋል::
የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከየትኛው ወገን እንደተነሳ ባይታወቅም የተለያዩ አስተያየት ሰጪ የኢህአዴግ አባላት ህዝቡ ከኢህአዴግ በተቃራኒ በመቆሙ በተለይም በሐገር ውስጥ በትግራይ ክልል የአረና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት በመሀል ኢትዮጵያ ደግሞ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች መጠናከር በሚጠሩት ሰልፍ ላይ የሚገኘው የህዝብ ቁጥረ ከእለት ወደ እለት መጨመር በውጪ ሀገራት ደገሞ ግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደ አንድ መስመር መምጣት በህወሀት ነባር አመራሮች ለድርጅታቸው እንደ አደጋ በመታየቱ የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከህወሀት አመራሮች ሊነሳ እንደሚችል ይገመታል፣ በተቃዋሚው በኩል በእርቀ ሰላሙ ዙሪያ ያለው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

source http://www.zehabesha.com/

No comments:

Post a Comment