Monday, September 15, 2014

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን የስራ ማቆም አድማ ልናደርግ እንችላለን ሲሉ ወያኔን አስጠነቀቁ

-የዩንቨርስቲው ስልጠና በግሩፕ እንዲደረግ ቢሞከርም ከፍተኛ አለመግባባት በመፈጠሩ ተበትኗል።
-ሽመልስ ከማል ከለገሃር ሙልሙል ጫት ቤት ተጠርቶ አለቃ ጸጋይ ፊት በመቅረብ ማስጠንቀቂያ ተሰቶታል።
-ለአንድ ሳምንት ያህል ሊሰጥ የታሰበው እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን የተጀመረው የወያኔ የልማታዊ ዲሞክራሲ ስልጠና ገን ክጅምሩ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ከተለያዩ መምህራን የተሰበሰቡ መረጃዎች ጠቁመዋል። 

 

 ገና ስልጠና ከመጀመሩ መምህራኑ መንግስት ያለብንን ችግር እና የሃገሪቱም ሁኔታ ማገናዘብ እና መፍታት ካልቻለ የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን ሲሉ በጭብጫባ የታጀበ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ይህ የግዳጅ ስልጠና በተለያዩ አደራሾች የተጀመረ ሲሆን መምህራኑ እንዳሉት የውይይቱ የመግቢያ ሰነድ ተረስቶ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና በመምህራን ሕይወት ዙሪያ ከባድ የሆነ ንትርክ ተገጥሞ ለወያኔ አሰልጣኞች ከባድ ጋሬጣ ሆነው እንደነበር መምህራኑ ክላኩት መልእክት ለማወቅ ተችሏል። የመምህራኑ ስልጠና በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን ለወያኔ የእግር እሳት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በዛሬው እለት ጠዋት በሽመልስ ከማል ሲመራ የነበረው እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢንዱስትሪ ካምፓስ ተማሪዎች የግዳጅ ስልጠና በጩኸት ቢበተንም ሽመልስ ከማል ደንግጦ ከስብሰባ አደራሹ በመውጣት ተደብቆ የጠፋ እና ወደ ተለመደው የጫት ሱስ ተግባሩ የሄደ መሆኑን ሁኒታውን ሲከታተሉ የነበሩ እና አብረውት በአስተባባሪነት እና በተባባሪ አሰልጣኝነት የተመደቡ ካድሬዎች ጠቁመዋል። ለአለቆቹ ሪፖርት ሳያደርግ ወደ ጫት ቤት ያቀናው ሽመልስ ከማል በአስቸኳይ የስልክ ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ካለው የአለቃ ጸጋይ ቢሮ ተጠርቶ በመሄድ ከስልጠናው ጋር በተያያዝ ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲሆን ከቢሮው ሲወጣ ፊቱ ተለዋውጦ እና ደንግጦ እንደነበር አስተባባሪዎቹ እና ተባባሪ አሰልጣኞቹ ከሰጡኝ መረጃ ለማወቅ ችያለው።
የስልጠናው አስተባባሪዎች ስልጠናውን ለመቀጠል አቶ ሽመልስ ከማልን ትተውት ወደ አ አ ዩ ኢንዱስትሪ ካምፓስ ቢደርሱም ተማሪው ከተባለበት ሰአት ሁለት ሰአታት ያህል በመዘግየት ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በየግሩፑ ቢመጣም የግሩፕ ስልጠና አስተባባሪ እና አሰልጣኝ ካድሬዎች ተማሪውን በፍጹም ሊያሳምኑት ያልቻሉ ሲሆን ተማሬው አቴንዳስ ሲደረግ የታደለውን ኖትቡክ እና ቢክ እስክርቢቶ እንዳልተጠቀመበት ታውቛል።ብዚህ ስልጠና ላይ ተዋት ተማሪው በጩኸት እና በፉጨት ስለረበሸ የውሃ እና የሻይ አቅርቦት ተከልክሏል።ምንሊክ ሳልሳዊ
የከሰአት በኋላ ስልጠና በግሩፕ የተከፋፈለ ሲሆን ይህንን ያደረጉት ተማሪው በጋራ ሆኖ ተቃውሞ እንዳያሰማ እና በግሩፑ ተቃውሞ ቢኖር እንኳን በቀላሉ መቆጣጠር እንዲቻል ተማሪው ጎን ለጎን እንዳያወራ አራርቆ በማስቀመጥ
ተማሪው እርስ በ እርስ እንዳይደጋገፍ ለማድረግ ነው። አሰልጣኞቹ ካድሬዎች ስልጠናውን በተማሪው መሰላቸት በመደናበራቸው 9 ሰአት ስልጠናውን ጀምረው ወዲያው ተማሪው ጥያቄ ካለው ብለው ጥያቄ እንዲጠይቅ ሲያደርጉ ከተጠየቁ ጥያቄዎች መካከል ስልጠናው ጥቅም የለውም?፣ አላማው ምንድነው?፣የቀድሞ ስራቶችን ክፋት ብቻ ለምን ታወራላችሁ ?፣ ራሳችሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ለምን ከኋላቀር የቀድሞ ንጉሳውያን አስተዳደር ጋር ትመዝናላችሁ፡? ከናንተ በፊት መንግስታት እንጂ የሚበድሉት በህዝብ መካከል ፍቅር እና የሃይማኖት መቻቻል ነበር ይህን አምናቹሃል አሁን የት ገባ?፤ ወደ ኋላ እየተመለስን ከምናላዝን ለምን አሁን ባሉት እና ወደፊት በሚኖሩት አስቸጋሪ ፈተናዎች እና ጉዳዮች ላይ አናተኩርም ? ወዘተ የሚሉ ጥያቂዎች ቢነሱም ምላሾቻቸው የማያረኩ የተድብሰበሱ እና የሚያደናግሩ ነበሩ ። እንዲሁም በነገው እለት በነጻ ፕሬስ በጋዜጠኞች እና በመንግስት መካከል ስላለው ሁኔታ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ ስልጠናው በተማሪው መሰላቸት እና ጉርምርምታ 9 ሰአት ጀምሮ 10.30 ተበትኗል።

No comments:

Post a Comment