To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, September 2, 2013
http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/02/344-5/
http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/02/344-5/
ይገርማል እንደዛ የተለፋለት፣እንቅልፍ ታጥቶለት ስንትና ስንት ወጪ የወጣበት የኢህአዴግ ሰልፍ የመስቀል አደባባይ ግራ ጉንጭ እንኳን በወጉ መሙላት አልቻለም!!በህዝቡ መካከል የነበረው ክፍት ቦታ በደንብ እየተወራጩ መሮጥ የሚያስችል ነበር፡፡ፖለስ ግን ሆነ ብሎ ህዝቡ በተንተን እንዲል ሲያደርግ አይቻለሁ፡፡ፕሮግራም መሪው ለብቻው ነበር መፈክር የሚያሰማው-የሚቀበለው አልነበረም፡፡ህዝቡ ፕሮግራሙን ሳይጠናቀቅ ነው ሰልችቶት የሄደው፡፡ተሸክሞት ያመጣውን ባነር እስካሁን ተሸከሙክ ካሁን በኋለስ ገደል ይግባ ይል ነበር፡፡በአስተባባሪዎች መካከል ጥል አለመግባባት ነበር..አንዷ ሰልፉ ሳይጠናቀቅ ወደቤቷእየሄደች ሌሎችም የሰፋሯሰዎች ተከትለዋት ወደ ቤት እየሄደች እያለ ሌላዋ አንቺን ደግሞ ማነው አስተባባሪ ያደረገሽ ሌላውስ እሺ ቢያንስ አንቺ እንዴት ስነሰስርአት አታስከብሪም ስትላት–ዞር ብላ በጎንዮሽ..እዩኝ ባይ—ስትላት አይቻለሁ ሰምቻለሁ፡፡ዋልታ ኢንፎርሜሽን አደባባዩ በህዝብ ይጥለቀለቃል ብሎ ያመጣው እና በቤተ መንግስት በኩል ለታሰቡ አጥለቅላቂዎች ታስቦ የነበረው ትልቅ እስክሪን ምንም ሳይታይበት ባደውን ተመልሷል፡፡መጨረሻ ላይ በኢቲቪ የሚተላለፍ የትራፊክ ወሬ ሲተላለፍበት አይቻለሁ፡፡የመጣውም ህዝብ ሰልፉ ላይ የተሳተፈው ያለቀልቡ ነበር፡፡ለምን? እንዴት? ብዙ ጉድ አለ—በዝርዝር ዛሬም ሌላ ቀንም ቢሆን በመረጃ አስደግፈን እናያለን፡፡ ትናንት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በተፈጸመው ህገወጥ ተግባር በጣም ስለተናደድኩኝ ለሊቱን አልነጋም ብሎኝ ነበር፡፡ ወደ ስድስት ሰኣት አካባቢ ለምን የኢህአዴግ ሰልፍና ጉዱን አላየውም ብዬ በመወሰን ትንሽ ተኛሁና ልክ አስር ሰአት ላይ ነቃሁ፡፡ሰፈር ሰልፍ ውጡ የተባለው(የተለፈፈው) 11 ሰአት ነበር ፡፡እኔ ቀድሜ መነንገድ ላይ ያለው የሰልፈኛ ሁኔታ ሁሉ እያየሁ ልሂድ ብዬ 10፡18 ላይ ከቤት ወጠሁ፡፡እንደወጣሁ ያጋጠመኝ ጨለማና ባዶ ነገር ብቻ ነበር፡፡ የመጣው ይምጣ ቤዬ ጉዞዬን ቀጠልኩኝ፡፡እንዳውም ሰው በየመንደሩ ተሰባስቦ የሆነ ነገር እየሰራ ቢሆንስ ብዬ ውስጥ ለውስጥ ሳይቀር ገባሁበት፡፡አሳቻ ቦታ ላይ አካባቢ ፖሊስ ሞልቶ ነበር፡፡ወደ ልደታ፣ወደ ሜክሲኮ እየተጠጋሁ ውስጥ ለውሰጥ ያስገባል ባልኩት መንገድ ሁሉ ምን እንዳለ ለማየት ሞከርኩኝ ከፖሊስ በስተቀር ምንም አልነበረም፡፡እንዲሁ እየዞርኩኝ መጨረሻ ሜክሲኮ ደረስኩኝ 11፡30 ነበር፡፡ መንገዱ በፌደራል ፖሊስ ከመታጠሩና ካንዳንድ መንገደኛ በቀር ሰው አልነበረም፡፡እየተፈተሸን ነበር የምናልፈው፡፡ የነገሩን መካበድ ሳየው የአዲስ አበባ ሳርና ቅጠልም የሚቀር አልመሰለኝም ነበር፡፡መስቀል አደባባይ እስክደረስ ድረስ-ከሜክሲኮ ማለቴ ነው-ሶስቴ ተፈትሻለሁ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መስቀል አደባባይ ሰው አይጠፋም እንደምንም ብለው የድምጻችን ይሰማ ሰዎችም ቢሆኑ ይገኛል ብዬ ብጠጋ በየጥጋ ጥጉ ተጠግተው (በዛ ያሉ) ከቆሙ የፌደራል ፖሊሶች በቀር ምንም የለም፡፡…ቀጥል እዚህ መቆም አይቻልም!!—- አሉኝ፡፡እዛ ስደረስ 12 ሰአት ሆኖ ነበር፡፡እሺ የት ልሄድ ብዬ ስጠይቅ አጠገቤ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ትዝ አለኝና ወደዘ አመራሁ፡፡እየገባሁ ዝናብ ጀመረ፡፡ከገባሁ በኋላ ግቢ ውስጥ ዛፍ ተደግፌ ብዙ ቆየሁ፡፡ ሙሽሮች ነበሩ-በተክሊል የሚያገቡ ማለቴ ነው፡፡ትምህርት የሚሰጡት አባትም ..ያው እንደምታውቁት ዛሬ. ሁላችንም በዚህ ሰልፍ ላይ እንድንገኝ ተጠርተናል፣እኛም እንድናስተላፍላችሁ ከላይ ወርዶልናልና አሁን ሰአቱ ነውና አብረን ድምጻችንን እንድናሰማ እላቿለሁ…አሉ፡፡እንደዚህ አይነት ቅስቀሳ ትናንት እየሱሰ ገዳም በሚባል ቤ/ክያን እና ጅማ አባ ጅፋር በሚባለው መስጂድም ሲተላለፍ ሰምቻለሁ፡፡እናም እዛ እስቲፋኖስ ሆኔ 1 ሰአት ሆነ፡፡ አንዴ ብሄር ብሄረሰቦች አንዴ የፈረንጂኛ ሙዚቃ እየተከፈተ ካሴቱን የሚቀይር አጥቶ እራን እየቀያየረ እያጫወተ በጣም ይጪሀል፣ስልችት ብሎጭ ነበር፡፡ ከቤተክርስቲያን ወጣሁና ይሄኔማ ሰው አይጠፋም ብዬ ወደ አደባባዬ አመራሁ፤ ከፖሊስና ከመንገደኛ በቀር የለም፡፡ሁለት ፈረንጅ ጋዜጠኞችም ነበሩ፡፡ብጠለልም በጣም ዝናብ መትቶኝ ነበር፡፡ ከህንጻ ስር መቆም ይቻል እንደሆን ፌደራል ፖሊሱን አስፈቀድኩት፡፡ፈቀደልኝ፡፡ሁለት (ሲቪል የለበሱ) ደህንነቶች ነበሩ-አብረውት፡፡ወሬ እያወሩ ነው፡፡ ድንገት ቅልስልስ መስዬ ይቅርታ 12 ሰአት ነበር ይጀመራል የተባለው ምነው ዘገየ ብዬ ስጠይቅ፡፡ከዛ ፌደራሉ አሀ ለዛ ነው የመጣኸው ቲኬት ነገር አለው እንዴ አለኝ፡፡የለውም ሰልፉን ፈልጌ ነው የመጣሁት ብዬ እያዋዛሁ ስነግረው አይ በዚህ አይነትማ እስከሶስት ሰአትም የሚመጡ አይመስለኝም፡፡ታዲያ አልተሳካም ማለት ነው አልኩት፡፡ —ያው ከዝናብ ጋር እየተጋፋ ለኢህአዴግ መስዋእተ የሚከፍል የለም ማለት ነው፤ካሁን በኋላ ሲያባራ ቢመጡም ካንገት በላይ ነው ማለት ይቻላል —አለኝ፡፡ ሁለቱ ደህንነቶችም ቀለል የሉ ናቸው፡፡ ግን ያባንዲራ ያቃጠሉት ድራሻቸው ጠፋ አይደል— አለ አንዱ፡፡እንዴት ባንዲራ ይቃጠላል ግን መለስም ጨርቅ ብሎታል የፈለገ ቢሆን ማቃጠል የከፋ ወንጀል ነው አለ ወደ ፌደራሉ እያየ፡፡ድንገት ወደ 1፡53 አካባቢ ጥቂት መፈክር የያዙ ቁርሳቸው የበሉ የማይመስሉ እናቶች፣ ጎዳና የሚጠርጉ ከነባርሜጣቸውና ቱታቸው፡—ሽብርተኝነትና አክራሪነት የልማት ጠንቅ ነው ..እያሉ ብቅ አሉ፡፡ከዛም ቪዲዮ ቀራጩ ነሽ የፖለስ አዛዡ ነሸ ሁሉም አንዳቸች ተአምር የተፈጠረ ይመስል ወዲህ ወደያ መሯሯጥ ጀመረ፡፡ እኔ ዘንድ ቆመው የነበሩትንም ፖሊሶች..አንተ ስማ ውጣ ከሱጋ..እየተባሉ እነዛ ጥቂት ሰዎች በጣም ብዙ ሆነው እንዲያጅቡ ተወሰዱ፡፡(ነገ በጣም ከባድ ፈተና አል አሁን ወደ ጥናልሂድ ቀጣዩን የ22 አመት መንግስት፣የ6ሚሊዮን ባለ አባል ይህን ያህል ድካምና ወጪ የወጣበት ሰልፍ እንዴት እንደተጠናቀቀ አካፍላቿለሁ-ከፈተናዎቼ በኋላ፡፡በአጠቃላይ የሂሳብ ስሌት ግን ሰማያዊ ለእንደዚህ አይነት ደል በመብቃቱ ሁላችንም ደስ ሊለን ይገባል፡፡በእርግጥ ዛሬ የፓርቲው ጽ/ቤጽ ድረስ ሄጄ እንዳየሁት ሁሉም ነገር ሰላም ነበር፣ ብርሁኑ ተ/ያሬድና ይድነቃቸው ከበደንም ጽፈት ቤቱ በር ላይ አይቻቸዋሉ፡፡ምናልባት ያልገባኝ ነገር ቢኖር ጽፈት ቤቱ በረ ላይ ለምን የድርጅቱ አርማ ያለባቸው ጨርቆችና ተ-ሸርቶች ድብልቅል ብለው ከቆሻሳ ጋር ተቀላቅለው መጣላቸውን ነው፡፡ፖሊስ ይሆን እንደዛ ያደረገው ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡እንደውም አንድ ወንድም ተ-ሸርቶቹን እየመረጠ ሊያሰገባ ሲል ሌላው ባክህ ተወው ብሎ መልሶ እዛው ሲጥው ሳይ ..ፓርቲው ሆነ ተብሎ በፖለስ የንብረት ብልሽት ሳይደርስበት አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳነሳ አድርጎኛል፡፡)ለዛሬው በዚህ ይብቃን፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment