Thursday, January 30, 2014

አዲስ አበባ፤UNESCOደካማ የትምህርት አሰጣጥ መሃይምነትን ያስፋፋል አለ


unesco_logo_0በዓለም ዙሪያ ሩብ ቢሊዮን የሚገመቱ ሕፃናት መሠረታዊዉን የማንበብና የሂሳብ መደቦች መማር እንዳልቻሉ የተመ የትምህርት፤ ሳይንስና ባህል ድርጅት UNESCO አመለከተ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባ በድሃ ሀገራት ከሚገኙ አራት ታዳጊ ወጣቶች አንዱ ዐረፍተ ነገርን አስተካክሎ ማንበብ እንደማይችል ያመለከተ ሲሆን፤ ከሰሃራ በስተደቡብ በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት እንዲህ ያሉት ልጆች ቁጥር 40 በመቶ መድረሱን ገልጿል።
በየቦታዉ የሚታየዉ ደካማ የትምህርት አሰጣጥ መሃይምነትን ቀደም ሲል ከተገመተዉ በላይ እንዳስፋፋም UNESCO ትምህርትን በተመለከዉ 11ኛዉ ዓመታዊ ዘገባዉ አስታዉቋል። የትምህርት ፖሊሲም በርካታ ልጆች ወደትምህርት ቤት እንዲሄዱ ብቻ ሳይሆን እኩል እድልና የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ በሚለዉ ላይ እንዲያተኩርም ድርጅቱ ጠይቋል።
በድርጅቱ የትምህርት ለሁሉም ፕሮጀክት ዳይሬክተር ፓዉሊን ሮዝ ዘገባዉ በጥቅሉ በመላዉ ዓለም በመማር ማስተማር ሂደት ያለዉን ቀዉስ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፤ «ዘገባዉ በመላዉ ዓለም በሚታየዉ የመማር ማስተማር ቀዉስ ላይ ያተኮረ ሲሆን 250 ሚሊዮን ልጆች መሠረታዊ የሚባለዉን ትምህርት እንዳላገኙ ያመለክታል። እናም ዘገባዉ መምህራንን ማፍራት ላይ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲዉል እና ምርጥ መምህራን እነዚህን ልጆች እንዲያስተምሩ መደረጉን ማረጋገጥና የመማር ነገር እንደዋዛ እንዳይታይ ያሳስባል።»
የወደፊት ትዉልድ እጣፈንታ በመምህራን እጅ ላይ መሆኑን ያመለከቱት የUNESCO ዋና ዳይሬክተር ኢሪና ቦኮቫ በበኩላቸዉ በመጪዉ የጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ከአምስት ሚሊዮን በላይ መምህራን እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።
Source/http://www.dw.de/

No comments:

Post a Comment