Thursday, January 23, 2014

አንዲት ኢትዮጵያዊት ቤይሩት ውስጥ በመኪና አደጋ ሞተች በግሩም ተ/ሀይማኖት



በቤይሩት ባለፈው ቅደሜ ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊት በመኪና አደጋ መሞቷ ታወቀ፡፡

ቅዳሜ ጠዋት ላይ ይህ አደጋ የደረሰባት መሆኑን የቅርብ ወዳጆቿ ገልጸውልኛል፡፡ ሟች አምስት ወንድምና እህቶቿን ለማስተዳደር ባለባት ሀላፊነት ሁለት ቦታ በተመላላሽ የምትስራ መሆኑን የቅርብ ጓደኞቿ ገልጸውልኛል፡፡ (ተመላላስ የሚባለው ኮንትራት ሄደው ሲጠፉ ወይም በነጻ ቪዛ ሄደው በግል ቤት ተከራይተው ሰርተው ወደቤታቸው ሲመለሱ ነው፡፡)

አንደኛው ቦታ በጠዋት ለመሄድ ሌሊት አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ወደ መጀመሪያ ስራዋ ስትሄድ ነው አደጋው የደረሰው፡፡ በሰዓቱ ሱዳናዊያኖች አይተው ለፖሊስ በመንገራቸው ሬሳዋ ሊነሳ ችሏል፡፡ መረጃውን የሰጡኝ ሰዎች በሶስት ፎቶ አስደግፈው ስለሆነ ያቀበሉኝ በአንደኛው ፎቶ ላይ አንገቷ ተቆርጦ ከራሷ በላይ ያለው ክፍል ለብቻው ይታያል፡፡ በኋላ ሆስፒታል ተሰፈቶ ቦታው ተመልሷል ሁለተኛው ፎቶ ይታያል፡፡

ቤሩት ውስጥ በመኪና አደጋ የሚሞቱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሚ የሞተችው የዚህችን ልጅ ሬሳን ወደ ሀገር ለማሳፈር አምስት ሺህ ዶላር የተጠየቀ ሲሆን በሰዓቱ ይህን ያህል የሚደርስ ሳንቲም ማግኘቱ ከባድ ስለሆነ እርዳታ ማሰባሰብ ታስቦ ነበር፡፡ በዚህን ወቅት ለኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም እና ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጋዜጠኛ ነጋሸ መሀመድ ሁኔታውን እስረድቼያቸው ፍቃደኛ ከሆኑልኝ በኋላ ግን ገጪው ተገኝቶ እኔ እከፍላለሁ በማለቱ ሀሳባችን ሰረዝን፡፡ ለጋዜጠኛ ነጋሽ ማህመድ እና ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ለወደን ደራሽነታችሁን አሳይታችኋል እና ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

ለአሁኑ ፎቶውን ያልተጠቀምኩትም ሆነ ስሟን ያልጠቀስኩት ቤተሰቦች መስማታቸውን አለመስማታቸውን ማስረጃ ሰለሌለኝ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment