Wednesday, January 29, 2014

የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጥቷል።



ወያኔ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመስጠት የተስማማው እንደ አ.አ. ሃምሌ 2007 መሆኑን Sudan Tribune በነሃሴ 4, 2007 አምዱ አጋልጧል። ዜናው እንደሚለው ከያንዳንዱ ወገኖች የተውጣጡ ሰባት የድንበር ባለሙያዎች አብረው ወሰኑን እንደከለሉት ይናገራል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በድንበር ዙሪያ ባለሙያ ከሚባሉት በህይወት ካሉት አንዱ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሲሆኑ እነዚህ ሰባት ባለሙያ የተባሉት ሰዎች ድንገት ከየት እንደመጡ ለማወቅ አልተቻለም። 

ወያኔ መሬት አሳልፈው የሚሰጡበት ምክንያት:-

ወያኔ ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ግዛት አማራዎች ብሎ የሚጠራቸው ህዝቡን በማስገደድና ግዛትን በማስፋፋት ያመጡት ግፍ እንጂ ህዝብ ፈልጎት የመጣ ዜግነት አይደለም ብሎ ስለሚያምን ድንበርም ሆነ ኢትዮጵያዊነት በውዴታ ባለመሆኑ አጎራባች አገሮች የሚያቀርቡትን የግዛት ይገባኛል ጥያቄዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በተግባር አሳይተዋል። ሰሞኑን ደግሞ ከሱንዳን በድጋሚ በመጣው የይገባኛል ጥያቄ ሱዳን ተጨማሪ መሬት እንደተሰጣት ይታወቃል። ከኤርትራ ጋር በሚደረገው ምስጢራዊ የእርቅ ደረድር 85ሺህ ኢትዮጵያውያን የወደቁለት ባድመ የተባለው መሬት በቅርቡ ለኤርትራ እንደሚመለስ መዘገቡ ይታወሳል።

http://www.sudantribune.com/spip.php?article22692

No comments:

Post a Comment