Sunday, January 26, 2014

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው” አለ January 26/2014


“የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ 
ባወጣው መግለጫው አስታወቀ።


ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ ወሳኝና ህዝባዊ ጥሪ እንደሆነ ታሪካዊ ምስክርናውን በመስጠት፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥ ለዘለቄታው ይሰፍን ዘንድ የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።

No comments:

Post a Comment