Tuesday, January 28, 2014

ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላከ ድብዳቤለሚመለከተው ሁሉ .....!
በዓዲግራት ከተማ በደረሰን ድብደባ በጣም አዝኛለሁ። ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው። ህወሓት ከሽፍታ በላይ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ሽፍቶች ሰለማዊ ሰውን ላይበድሉ ይችላሉና።

እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።

የድብደባው ዓላማ (አንድ) ከህዝብ ጋር እንዳንገናኝ፣ (ሁለት) ስንበትነው የነበረው የዓረና አጀንዳ ስሜት ኮርኳሪ ስለነበር፣ (ሦስት) የዓዲግራት ህዝብ ጥሩ አቀባበል ስላደረገልንና ህወሓቶች ስለሰጉ (አራት) እኛ ተስፋ ቆርጠን ቀጣይ ስብሰባዎቻችን እንድንሰርዝ ለማስገደድ ነበር።

ትግሉ ይቀጥላል። ቆርጠን ተነስተናል። ከዓዲግራት ድብደባ የባሰ ሊመጣ አይችልም። በዓዲግራት መስዋእት ሁነናል። የዓዲግራት ድብደባ የትግላችን አስፈላጊነት አረጋግጦልናል።

ተስፋ መቁረጥ የለም። ወደ ኋላ አንድም ኢንች ፍንክች አልልም። በዓዲግራት'ኮ ሙቻለሁ። አልቅሻለሁ። ሐዘኔን ጨርሻለሁ። ሁለተኛ ሞት የለም። ስለዚህ ካሁን በኋላ ሞት የለም። ትግሉ ይቀጥላል። ሰው ሁሉ ለነፃነቱ ይነሳ። ህወሓት ለማንም ሊሆን እንደማይችል አረጋግጠዋል።

(የዓድግራት ድብደባ ዝርዝር ጉዳይ እፅፋለሁ። አሁን ትንሽ ድካም ይሰማኛል)።

አብረሃ ደስታ

It is so!!!

2 comments:

 1. በአዲግራት ከተማ በነ አብርሃ ደስታ ላይ ስለደረሰው የወያኔ ፋሽሽታዊ ድብደባና እንግልት እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ይህ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ነው፡፡ በጥቂት አላዋቂ ግለሰቦች ተነድፎ ሲተገበር የቆየው የወያኔ ዘረኛና ከፋፋይ ፖሊሲ በጊዜ ሂደት እየተጋለጠ ተቀባይነት ሲያጣ የመጨረሻ አማራጭ የሚደርገው የጠመንጃ አፈ ሙዝን ብቻ ነው፡፡ ለውጥ የማያቋርጥ ሂደት ነው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ እውነት በወያኔ አባላት ዘንድ አይሠራም፡፤ ምክንያቱም ፈጣሪቸው መለስ ዜናዊ እራሱ Change is Dynamic የሚለውን እውነት ሳይረዳ ነው የሄደው፡፡ ለዚህም ማስረጃው ትግራይ ውስጥ ስንጥቅ አይኖርም ብሎ የተናገረው ብዙ ሰውን ሲያስቅ የሚኖር አባባል ነው፡፡ በእርሱ ፍልስፍና ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ሁሉም በጅምላ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ብቻ ያራምዳል ብሎ ማሰቡ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ከተፈጥሮ ጋር መጣላት ነው፡፡ ምክንያቱም ሃጎስና ለተኪዳን ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች በመሆናችው ተፈጥሮ በለገሳቸው የተለያየ አዕምሮ አንዱ ከሌላው የተለየ ያሰባል፡፡ እንግዲህ ይህ በተለይ የማሰብ ነፃነቱ Made in መለስ ሰናዊ በሆኑ ካድሬዎችና ጥቅመኞች ተገድቦ አርቲፊሻል ወያኔYaዊ አስተሳሰብ ብቻ ማራመድ አለባቸው፣ ለዚያውም ለነስብሃት ነጋና ሐለቃ ፀጋዬ ጥቅም ማስጠበቂያነት ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡
  አቶ አስገደ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንደዚሁም ሌሎች የለውጥ አራማጆች ምንም የሠሩት ወንጀል የለም፡፡ እስከ መቸ በሻገተና በዛገ የመለሰስ ዜናዊ የስህተት ፍልስፍና እንመራለን፡፡ እስከ መቸ 2 + 2 = 5 ወይንም ወተት ጥቁር ነው እያልን እንኖራለን በማለት ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብረው ወያኔን ለመታገልና በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ መግዛት ጊዜው ያለፈበት ሠይጣናዊ ድርጊት ከመለስ ዜናዊ ጋር አብሮ የሞተ ከንቱ ፍልስፋና ስለሆነ መቅረት አለበት ብለው ቢታገሉ ሌሎችም በጊዜ ሂደት እየባነኑ የሚነቁ የትግራ ልጆች ይከተሏቸዋል ማለት ነው፡፡ አስገደን ወይም አብርሃን መደብደብ፣ ማሰርና መግደል ትግሉን አያስቀረውም፡፡ ትግራይ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት በርካታ አሰገደዎችና አብርሃ ደስታዎች እየተፈጠሩ በመሆኑ ወያኔና ፀረ ሕዝብ ፍልስፍናው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚጠፉ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
  ያለጥርጥር ወያኔን እናቸንፋለን!
  ድል ለመላው የኢትዮጵ ሕዝብ!!!

  ReplyDelete
 2. exactly ,,ይህ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ነው ,,አቶ አስገደ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንደዚሁም ሌሎች የለውጥ አራማጆች ምንም የሠሩት ወንጀል የለም
  እስከ መቸ በሻገተና በዛገ የመለሰስ ዜናዊ የስህተት ፍልስፍና እንመራለን ??

  ያለጥርጥር ወያኔን እናቸንፋለን!
  ድል ለመላው የኢትዮጵ ሕዝብ!!!

  ReplyDelete