Tuesday, January 28, 2014

ተመሰገን ደሳለኝ ለምን የተየቅሁህን አትመልስልንም???

ሰርካለም የእስክንድር ነጋ ባለቤት በመሆንዋ ብቻ እንደታሰረች ወህኒ ቤት ወለደች፡፡ የዳዊት ከበደ ሚስት እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ምንም በደል ደረሰባት ሲል አልሰማንም፡፡ እንዲደረስባት ፈልጌ አይደለም፡፡ ሰርካለም የተቃዋሚ ጋዜጠኛ ሚስት በመሆንዋ ከታሰረች ይዊት ከበደም ተቃዋሚ ጋዜጠኛ ነኝ ስለሚል ወያኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ማለትም በጠንካራ ተቃዋሚዎቹ ላይ ማዳላት ስለማያውቅ እንዴት ሳያስር ማራት ብዬ ስለተገርምኩ ነው፡፡
ተመስገን ደሳለኝ ምን አስተያትት አለህ? ሁሌ ቅዳሜ ቅዳሜ እስክንድ ነጋ ከታሰረ ወዲህ ዳዊት ከበደና አንተ ከጋራ ጓደኞቻችሁ ጋር ሰብሰብ እያላችሁ ምሳ በጋር እንደምትመገቡ ገልጸህ በመጨረሻው ቅዳሜ በድንገት ዳዊት ከበደ፣ ቆይ! ና አንዴ ብሎ መንግስት ሰኞ ይቅርታዬን አንስቶ ማክሰኞ ሊያስረኝ ስለሆነ ዛሬ ማታ ከአገር ልወጣ ነው አለህ፡፡ 
1. ዳዊት ከበደ ይህ መረጃ መች ደረሰው? 2. ሁሌ ቅዳሜ ቅዳሜ ከሌሎች ጓደኞቻችሁ ጋር ምሳ ለመቋደስ ትገናኙ ነበርና ለምን ከመጨረሻው ቅዳሜ በፊት አልነገረህም? 3. ጓደኞቼን መልሱልኝ ከማለት ይልቅ ለምን ምርጥ ጓደኞቼን መልሱልኝ አላልከውም ርእሱን፣ ምክንያቱም የዳዊት ከበደና የአንተ ጓዳኝነት ወጣ ያለና ሌሎች ጓደኞቻችሁን የማያሳትፍ በመሆኑ ነው፡፡ ዳዊት ከበደ ወደ ኤርፖርት ሲሄድ አንተ ብቻ ነህ ከሚስቱ ጋር ሆነህ የሸኘኸው፡፡ ሌሎቹ የጋራ ባልደረቦቻችሁ አንድ ማዕድ ላይ የነበራችሁ ሁሉ ለምን አልሸኙትም? 4. ምሳ ከበላችሁ በኋላ ዳዊት ከበደ አንተን ብቻ ነጥሎ ና አንዴ በማለት ከአገር ሊወጣ እንደሆነ ምስጢሩን ሲነግህ ሌሎቹ ጓደኞች ተብዬዎቹ እንዲያው በደፈናው እኔ ድሬዳዋ አልሄድም ያለውን ነው የሰሙት፡፡ ሌሎቹንም ለምን እንዳንተ አላመናቸውም፣ ለምን ጠረጠራቸው፣ እነርሱስ እናማን ናቸው? 5. ዋናው አነጋጋሪ ጉዳይ ዳዊት ከበደ መንግስት ሊያስረው እንደሆነ ከተረዳ በኋላ እንዴት በአጭር ጊዜ አሜርካ የመግቢያ ቪዛ አገኘ፡፡ ማንም እንደሚያውቀው የአሜሪካ ቪዛ ልክ መነሐሪያ ሄዶ የአወቶቡስ ቲኬት በፍጥነት እንደመግዛት ያህል ቀላል እንዳልሆነ አንተም በሚገባ የምታውቀው ይመስለኛል፡፡
እኔ Professional Detective አይደለሁም፡፤ የሆነ ሆኖ ዛሬ ላይ ሆኜ ትላንትን እያሰብኩ ተመስገን ደሳለኝን አንዳንድ ጉዳዮችን ብጠይቅ ቅር ይለዋል ብዬ አልገምትም፡፡ 1. ትላንት ስለ ዳዊት ከበደ የጻፍከውን ዛሬ መለስ ብለህ እያየህ ግለሰቡ የወያኔ ሰላይ ነበር ብለህ ብታምን ስህተት ይመስልሀል፣ ምክንያቱም እስረተኞችን ለመሰለል ቃሊቴ ወህኒ ቤት እስረኛ መስሎ ገባ፤ ዶ/ር ብርሁኑን ለመሰል እጅግ በረቀቀ ዜዴ አንተንም ሸውዶህ፣ ምናልባት ልታውቅ ትችላለህ ከአገር እንዲወጣ ተደረገ ፣ 2. የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግስታት ባላቸው ስምምነት መሠረት መንግስት Define በሚያደርገው ጥያቄ ብቻ ለልዩ ተልእኮ በአስቸኳይ የሚሰጥ የVIP VISA ለዳዊት ከበደ ተዘጋጀለትና ወያኔ የሰጠውን ልዩ ተልእኮ እንዲያሳካ ወደ ተመደበበት አገር ተነቃነቀ ብልህ አንተስ ምን ትላለህ ? 3. ዳዊት ከበደን CPJ እንደሸለመው በመጽሀፍህ ገልጸሀል፡፡ ወያኔስ ዶ/ር ብርሃኑን በመሰለሉ ምን ሸለመው፣ ወይንስ መረጃው ገና አልደረሰህም ? 4. በመጽሐፍህ ገጽ 161 ላይ ደዊት ከበደ ትግሬ ነው፡፡ እንዲያውም ከትግሬነቱም በላ የጠቅላይ ሚኒስተሩ የትውልድ መንደር ልጅ ነው፡፡ አደዋ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቶ መለስ አባት አቶ ዜናዊ ትዳር ሲይዙ የዳዊት አባት አቶ ከበደ አጃቢና ሽማግሌ ነበሩ፡፡ … ዳዊት እንደነገረኝ … በማለት የአንተና የዳዊት ከበደ ጓደኝነት እጅግ በጣም ጠበቅ ያለ እንደሆነ ለማስረዳት ሞክረሀል፡፡ ትልቁ የኔ ጥያቄ የሚያተኩረው እዚህ ላይ ነው፡፡ ከዳዊት ከበደ ጋር ባለህ ቀረቤታ ደዊት ከበደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ለመሰለል ወያኔ እንደላከው ትንሽም ፍንጭ አልነበረህም ወይ፣ መቸም የደብቅሀል ብዬ አልገምትምና ነው፡፡ 5. በዚሁ መጽሐፍ ገጽ 161 ላይ ለዚህ ነው ደጋግሜ ጊዜው የትግሬ ነው የሚሉ ሴረኞችን አትስማ የምልህ፡፡ ጊዜው የትግሬ አይደለም፡፡ … ወዘተ ብለሆል፡፡አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሁኔታ ጊዜው የማን ነው፣ መልሼ ልጠይቅህ፡፡ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የጉራጌ፣ የጋምቤላ፣ ወይንስ የከንባታ፡፡ በአፍሪካ ሥልጣን በጠመንጃ ሲያዝ ጊዜው የጉልበተኞቹና የደጋፊዎቻቸው ሲሆን እየታየ እንዴት አንተ ይህ ሐቅ ይጠፋሀል፡፡መሰሪዎች ናቸው ስትል ወያኔንና ደጋፊዎቹን የሚቃወሙትን ሁሉ ማውገዝህ ነው፣ ለምን? የአማራ ብሔረ ሰብ እንደሆነ በያትኛውም ክልል Restricted from every privilege. ሥራ መቀጠር አይችሉም፣ ያላመነበትን የመቃወም መብት የለውም፡፡ በአማራ ክልል እንኳን የአማራ ተወላጅ ቦታ የለውም፡፡ የሰቆጣ (ዋግሕምራ) ልጆች አማርኛ ጠንቅው መናገራቸውንና አገው ቢሆኑም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በመሆናቸው አማራን ለማታለልና ለመሸንገል በብዙ የአማራ ከተሞች በባለስልጣንነት ይመደባሉ፡፡ በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች ክልሎች አሠራሩ ተመሳሳይ ነው፡፤ እንግዲህ ወንደማችን ተመስገን ደሣለኝ ጊዜው የትግሬ ነው አትበሉ የምትለን ምን መሠረት አድርገህ ነው፡፡ በአማራ ክልል ከ60% በላይ የመነግስት መ/ቤት ሠራተኞች ትግሬዎች ናቸው፡፡ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ ወዘተ. እንደዚሁ፡፡ ሻንገይ ዩኒቨርሲቴ ውስጥ እየተማሩ ናቸው ከሚባሉ 3000 ወጣቶች ወስጥ ከትግሬ በስተቀር ሌላ አንድም የለም፡፡በመከላከያ፣ በፖሊስ፣ በደህንነት፣ በውጭ ጉዳይ፣ ወዘተ. ቁልፍ ቦታ ላይ የተመደቡት ትግሬዎች ናቸው፡፡ በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማ፣ በክልል መስተዳድር ጽ/ቤቶች ውስጥ እንደዚሁ አብዛኛዎቹ ትግሬዎች ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በሃይማኖት ተቋማት በአብያተ ቤተክርስቲያናትና በመስጊዶች ሁሉንም ነገር እየተቆጣጠሩ ያሉት ትግሬዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በየትኛውም ትግራይ ከተማ አንድም የሌላ ብሔረሰብ ተወላጅ በአስተማሪነት፣ በንግድ፣ ወይም በሌላ ሥራ የተመደበ ሰው የለም፡፡ ለዚህም ነው ትግራይ ውስጥ ምን እንደሚደረግ ማንም የማያውቀው፡፡
6. ከፍ ሲል በመጠኑ በዘረዘረኩልህ ምክንቶች ጊዜው የትግሬ ነው የሚሉ ሁሉ አንተ እንደምትኮንናቸው መሰሪዎች ሳይሆኑ በአውነት ላይ የተመሰረተ ብሶታቸውን ነው የሚገልጹት፡፡ ዳዊት ከበደ እረሱን ደብቆ ሲንቀሳቀስ የነበረ ስውር የወያኔ ሰላይ ነበረ፡፡ አሁን ራሱን ይፋ በማውጣት ለምን ተልእኮ በልዩ ቪዛ ከአገር እንደወጣ እንድናውቅ አደረገን፡፡ በመጨረሻ አንድ ጠያቄ ላቅርብልህና አስተያቴን ልቋጭ፡፡ “ማንነትህን እንድነግርህ ጓደኞችህ እነማን እነደሆኑ ንገረኝ” ኢንዲሉ ጓደኛህ ዳዊት ከበደን አሁን በውል ስላወቅነው አንተንም የሱ ቢጤ የወያኔ ሰላይ ነህ ወይ ብዬ ብጠይቅህ መቸም ዱብዳ አይሆንብህም፡፡ ወያኔ ዳዊት ከበደን በውጭ አገር አንተን በአገር ውስጥ ተመሳሳይ ስራ እንድትሰሩ መድቧችኋል ብዬ እንዳስብ ተገድጃለሁ፡፡ ለምን ብትለኝ የዳዊትን ስውር ተልኦኮ ተረድተህ ተቃዋሚዎችን ለመታደግ ምንም ጥረት ስታደርግ አላየሁም፡፡ ለዚህች አገር ዴሞክረሲ፣ ሠላም፣ ፍትህና አገራዊ መግባባት እንዲመጣ ምሁራዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ያሉትን አንጋፋ አገር ወዳዶችን መሰለልና እንቅስቃሴአቸወን በየእለቱ ለወያኔ ደህንነቶች ማቀበል እግዚአብሄር ይቅር የማይለው ትልቅ በደል ነውና ተጠንቀቅ፡፡ በመጨረሸም ጓደኞቼን መልሱልኝ ላልከው መናጆ አደርገህ የዘረዘርካቸውን ሁሉ ነውነወይንስ ምርጥ ጎደኛህን ወዲ አደዋ፣ የሥላሴ ሠፈሩን ልጅ ዳዊት ከበደን??? እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና የዋህ ሕዝቧን ይጠብቅ፣ መሰሪዎችን እንደዚሁ እንደ ዳዊት ከበደ በግልጽ እንድናውቅ ያጋልጣቸው፡፡ 
አሜን! ፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 5 ቁጥር 163 ህዳር 15 2004 ዓ. ም. የመለስ አምልኮ “ጓደኞቼን መልሱልኝ” በተመስገን ደሳለኝ ገጽ 156-162

No comments:

Post a Comment