Thursday, January 23, 2014

አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት በቃ ልንለው ይገባል ( ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ )


 • Gezahegn Abebeማብቄያ የሌለው የወያኔ አረመናዌ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ጊዜ ሰሞኑን ለእራሴ አንድ ጥያቄ ጠየቁትኝ እስከመቼ ነው የወያኔ መቀለጃ እና መጫወቻ ሆነን የምንኖረው እስከመቼ ነው ወያኔ ህዝባችንን እያሰቃየ እና እየጨቆነ የሚኖረው እስከመቼ ነው ዜጓች መብታቸው ታፍኖና ነጻነታቸው ተረግጦ በሃገራቸው መብታቸው ሳይከበር እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቋጠሩ የሚኖሮት እኔ እንደማስበው በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየመራ ያለው የወያኔ መንግስት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን ሊያጠፋ የተነሳ መንግስት ይመስለኛል ግን እስከ መቼ ነው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በዚህ ርኩስ ባህሪውና ድርጊቱ የሚቀጥለው ? በቃልንለው ይገባል::
  መቼም ይህ ጥያቄ የሁላችንም ሀገር ወዳድ እና ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው እስከመቼ _?
  እኛ ኢትዮጵያኖች መብታችን ተረግጦ ነጻነታችን ተገፎ በዲሞክራሲ ቸነፈር ተመተን መኖር ከጀመርን ይኸው ከድፍን ሁለት አስር አመታቶች በላይ አስቆጠርን በእነዚህ ዓመታቶች ብዙዎች ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት ታግለዋል አሁንም ቡዙዎች በሚችሉት መንገድ ሁሉ ይኼ ዘረኛውን እና አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት ይገኛሉ::ነገር ግን ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት የታገሉ ብዙዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው ለብዙ መከራ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ የሀገሪቷ ዜጓች ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው በወያኔ ካድሬዎች ጭካኔ የተሞላበት ኢ ሰበአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በሰቃይ እና በመከራ ውስጥ ሲገኙ አንዳንዶቹም በሚደርስባቸው ስቃይ እና በወያኔ መጥፎ ሴራ እዛው ወህኒ ቤት ውስጥ እይውታቸው እያለፈ ይገኛል:: ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነን በቅርቡ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ እርቃ በምትገኘው ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱት ከ40 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያ ዜጓቻችን ምስክር ነው:: አረ ስንቱ ይዘረዘራል የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም :: ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ አመታቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች መሻሻል እና መስተካከል ሲገባቸው ነገሮች ሁሉ በተገላቢጦሽ እስራቱ፣ግድያው፣ስደቱ፣ድህነቱ ፣ ሁሉ ነገር እየባሰ እና ከጊዜ ወደ ጊዚ እየጨመረ መምጣቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጣም አሳሳቤና አስጌ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመልካች ነገር ነው::
  ወያኔዎች እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የሀገሬቱን ሀብት እየዘረፉ እና እየቦጠቦጦ እንዳሻቸው መኖርን አልበቃም ብሏቸው ቅንጣትም ያክል ስለ ኢትዮጵያም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ እንደሌላቸው በሚያሳይ መንገድ በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት ለግል እና ለእራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ቀደምት አባቶቻችን ለሀገራችን ዳር ድንበር መስዋዕት የሆኑለትን እና ደማቸውን ያፈሰሱለትን መሬታችንን ድንበራችንን እንኮን ሳይቀር ለባህድ አገራት በመስጠት ላይ እንዳሉ ሲሰማ ማንንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ የሚያስቆጣ እና የሚያንገበግብ ነው ብዬ አስባለው:: በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ወያኔዎች የገዛ ወገኖቻችንን የሀገሪቱን ዜጓች ሀብት እና ንብረት ካፈሩበት ሀገርና መሬት ላይ ሀብትና ንብረታቸውን እየዘረፉና ቤታቸውን እየፈረሱ ከሚኖሩበት ቄዬ እያባረሩ ለውጭ አገር ሰዎች ደግሞ የሀገሬቷን መሬት እየቸበቸቡ መኖርን የለመዱበት ተግባራቸው መሆኑ ነው ::
  እያደር ብዙ ይሰማል እንደሚባለው የወያኔን መንግስት አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም ፡፡ ወያኔ እያደረገው ስላለው አረመናዊ ድርጊቶ ፋታ ልንሰጠው አይገባም :: አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐልምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ሲበላሽና ፣ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሃገራችንን ዳር ድንበር የወያኔ መንግስት ለባዕድ አሳልፎ ሲሰጥ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆድደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል እንዲያውም በምን አለብኝነት የኢትዮጵያን ቅርጽ እና ታሪክ የሚያበላሸውን የወያኔ እንቅስቃሴ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ዘር፣ ጎሳና ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን እያጠፋ ባለው በወያኔ መንግስት ላይ ሆ ብለን በአንድነት በመነሳትና በመጮህ ይበቃል ልንለው እና ልናስቆመው የግድ ነው፡፡
  በቃ በቃ በቃ !!!
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

No comments:

Post a Comment