Friday, January 17, 2014

በደ/ጎንደር ፎገራ ወረዳ በአስተዳዳሪው ትዕዛዝ አንድ ሰው ሲገደል ዘጠኙ መቁሰላቸው ተሰማ


የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)


ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው በደ/ጎንደር ፎገራ ወረዳ ሻጋ ቀበሌ 2007 . ለሚደረገው ምርጫ ዝግጅት ሲባል የአካባቢውን የወልና የግጦሽመሬት ለወጣቶች እንዲሰጥ ብአዴን በደብዳቤ አዝዞ ነበር፡፡ እንደአሰተያየት ሰጪዎች የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት ባወጣው አዋጅና መመሪያመሰረት የወልና የግጦሽ መሬት ለማከፋፈል 80% የማህበረሰብ ክፍል ፈቃደኛ መሆን እንዳለበት ይገልፃል፡፡ በአማራ ክልል የመንግስት መስሪያ ቤትሰራተኛ የሆኑ ግለሰብ ለፍኖጸ-ነፃነት እንደገለፁት ለምርጫ ሲባል በህገወጥ መንገድ የሚደረገውን አካሄድ የአካባቢው ነዋሪዎች በመቃወማቸውየወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰሜ ፈረደ በአካባቢው ነዋሪ ላይ ተኩስ እንዲከፈት በማዘዝ ጌጡ አበራ የተባለ 25 ዓመት ወጣት ጥይት የተገደለ
ሲገደል ዘጠኝ ሰዎች ቁስለዋል ሆነዋል፡፡
1. 
እንየው አደረው የቆሰለ
2. 
አምላኩ ሙጨ የቆሰለ
3. 
ጌጡ የሻነው የቆሰለ
4. 
አምላኩ ጫኔ የቆሰለ
5. 
ታድሎ አሸነፍ የቆሰለ
6. 
አዝማረ ተባበር የቆሰለ
7. 
አወቀ ቢለው የቆሰለ
8. 
ጋሻው መርየ የቆሰለ
9. 
ያምላክ ጫኔ የቆሰለ
አካባቢው አሁንም አለመረጋጋት ሰፍኗል፣በልዩ ኃይል ጥበቃ ስር ነው፡፡

No comments:

Post a Comment