Saturday, January 18, 2014

የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ና የተገዳዩ ገበሬ ልጅ ምኞት


የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ልጅ ብሌን እንደምትመለከቷት በቀለም አሸብርቃ በቻን 2014 የአፍሪካ ዋኝጫ እተካፈለ ለሚገኘው ቡድናችን መልካም ምኞቷን ገልጻለች፡፡አባትም ፎቶዋን በገጻቸው በመለጠፍ ምኞቷን አድርሰዋል፡፡ 
 My daughter, Blen, asked me to post on facebook her very best wishes for our Walya. "All the best Walya" from Blen.በማለት
ከብሌን አጠገብ ያለችውን የስምንት አመት ታዳጊ ደግሞ ተመልከቷት ፡፡ቴድሮስ በውጪ ጉዳይነት የሚወክሉት መንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ስለእናት ማስረሻ ወላጅ አባቷን ‹‹አባዬን››በግፍ ተነጥቃለች፡፡በመኝታዋ አልጋዋ ላይ እንዳለች የመታት ጥይትም ቀኝ እጇን ቆርጦ ወስዶታል፡፡
ብሌን ሙሉ ፈገግታዋ በፊቷ ላይ ይነበባል በአንጻሩ ስለእናት ፊት ላይ ፈገግታን መፍጠር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ለአቤቱታ አዲስ አበባ በመጣች ወቅት አግኝቼያት ለመገንዘብ ተረድቻለሁ፡፡
ክቡር ዶክተር ሆይ ስለእናት ፎቶዋን በፌስቡክ እንዲለጥፉላት አትጠይቅዎትም እርሷ ስለዋሊያዎቹ የምታውቀውም ምንም ነገር የለም ግን በልጅ አንደበት ‹‹አባቴ ለምን እንደተገደለና እጄ በምን ምክንያት እንዴቆረጥ እንደተፈረደብኝ አላውቅም እናም ፍትህ እንዳገኝ እርዱኝ››ትለዎታለች፡፡

No comments:

Post a Comment