Friday, January 3, 2014

የህወሀት ባለስልጣናት የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ሙስና ለመከላከል ብቃቱ ጎሏቸዋል በሚል እንደተነጋገሩና ጉዳዩ በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ክፍል ሲታይ ቆይቶ በመጨረሻም ይፋ ተደርጎ” ሶስቱም ጄኔራሎች በያዙት ማእረግ ሃለፊነታቸው ቀንሶ እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል። ይሁን እንጅ ጄ/ል ሞላ እና ጄ/ል ሳህረ ከጄኔራል አበባው ጋር በአድማው የተሳተፉት ሆን ተብሎ ጄ/ሉን ከስልጣን ተፎካካሪነት ለማስወጣትና ፍትሀዊ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን ለተቀሩት የሰራዊቱ አባላት ለማሳየት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል ሳሞራን ይተካሉ ተብለው የሚታሰቡት በቅርቡ የሌ/ጄ ማእረግ ያገኙት ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ናቸው። የተለያዩ ወታደራዊ አዛዦችን በማነጋገር ስለነበረው ሙሉ ድራማ ከዜናው በሁዋላ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

No comments:

Post a Comment