Saturday, January 4, 2014

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ ታዘዙ



ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ። የባለስልጣኖች አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል።

የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ ነው የሚል ምክንያት መሰጠቱ ታውቋል። ባለስልጣናቱ ከኢሳት በተጨማሪ ለአሜሪካ ድምጽ እና ለአንዳንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ድረገጾችም መረጃ እንዳይሰጡ ታዘዋል። መመሪያውን ያወጡት የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት እና ኮሚኬሽን መስሪያ ቤት በጋራ በመሆን ነው። በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባ በሚቀጥሉት ቀናት ይኖረናል።

No comments:

Post a Comment