Thursday, January 16, 2014

መረጃ ቅበላውን ለማኮላሸት ስንል አቅጣጫችን እንዳይስት …(ጋዜጠኝ ነብዩ ሲራክ)


January 16, 2014
Nebiyu Sirakበመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት እና በተለይም በሳውዲ አረቢያ በምንገኝ ስደተኞች ዙሪያ መረጃ ማቅረብ ከጀመርኩበት ከአስር አመታት በላይ ተቆጥረዋል። ዘመነኛው ፊስ ቡክ ቀልባችን ከሳበው ወዲህም በርካታ ወዳጆችን አፍርቸ መረጃ ከማቀበል አልፎ በማቀርባቸው መረጃዎች ዙሪያ ምክክት ውይይት ስናደርግ ከአምስት አመት በላይ ሆኖናል። ይህ ሒደት ብዙ አስተምሮናል!
በረጅሙ መረጃ ቅበላ ያለፍነው ዱላ ቀረሽ ሙግትና እሰጣ ገባ አንድ ሆነን አንድነትን ፣ ዜጎችን ከመከራ እንታደግ የሚል አንድ አላማ ይዘን በአደባባይ እየፎከርን ፣ በአንድ ቋንቋ ተግባብተን የተለያየ ቋንቋ እየተናገርን ከርመናል። በግል ጉዳዩ እንደሚያገባው ዜጋ ትናነትም ሆነ ዛሬ ወደፊትም ከተገፊው የሰማሁትን ብሶትና ምሬት ፍንትው ካለ የድምጽና የምስል መረጃ ጋር አቀርባለሁ ! ይህን ሳደርግ ታዲያ የሚታይ የሚሰማው እውነትነትን አረጋግጨው እንኳ ከሰብዕና ጋር በተቆራኘ ህሊናችን እንዳያቆስል በሚል መረጃውን በድፍን አስተላልፊ ለመሄድ የተገደድኩባቸው አጋጣሚዎች የሉም አልልም ፣ አሉ ! ዳሩ ግና መረጃውን ሳስተላልፈው የሚጠራጠሩኝን አመኔታ ለማግኘት አልፎ አልፎ ሳልወድ በግድ ምስሎችና የድምጽ መረጃዎችን ይፋ ለማድረግም የተገደድኩባቸው አጋጣሚዎች አሉ።
ከሁሉም በላይ የሚቀርበውን መረጃ ከሰብአዊነት እና ሰው ከመሆን ጋር ማገናዘብና የህሊና ፍርድ መስጠት የተሳናቸው ወገኖች በእውነት ውሸት ሙግት ውስጥ ሊከቱኝ ይሞክራሉ ። በስደተኛው ማህበራዊው ኑሮ ዙሪያ ያቀረብኩትን መረጃ ከሰብአዊነት ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት ፍቅር ፣ በስደተኛው ዙሪያ ባለ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገ ገሃድ በማይታይ ኢ ፍትሃው እሳቤ ጎራ ለይተን ስንሟገት ከርምናል ። የዚህ ሁሉ ድምር ደግሞ ዛሬ ላይ ለአደጋ ዳርጎን እዚህ ደርሰናል …
ዛሬም ካለፈው አንማርምና ከነዋሪው ተቀብየ ወደ እናንተ የማደርሳቸውን የግፉአን ዜጎች ሮሮና ጩኸት ከሰብአዊነት ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት ፍቅር ፣ በስደተኛው ዙሪያ ባለ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገ ገሃድ በማይታይ ኢ ፍትሃው እሳቤ ጎራ ለይተን የምንፏከት ሁሉ ወዮልን ! ሰሞኑን በግል በተከፈተብኝ ዘመቻ አሳዛኙ በውስጥ መስመር የሚላኩ ስድብነ ዛቻና ማስፈራሪያዎች አይደሉም። የማቀርበውን መረጃን ማደናቀፊያ መጠቀሚያ ሃይማኖትን ዘር ሆኖ ሲታይ ያማል። ለሰራው ያሳዝናል። እናንት ቦለቲከኞች ሆይ! ዝም ልታስብሉኝ አትችሉምና ስልቱ ቢቀያየርም ሳልበገርላችሁ እንደምጓዝ ላሳውቃችሁ ግድ ይለኛል። በምክክር የያዛችሁት ዘመቻ የረከሰ አካሔድ ነውና ከጥፋት ባጠትቆጠቡ ወዮልን ! መቆሚያ መቀመጫችሁ ፣ መነሻ መውደቂያችሁን አበክሮ የሚረዳ አምላክ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ህሊናችሁ ስሜታችሁ ያተገናኛችሁ እለት ታዝናችሁ ! ከራሳችሁ ጋር የታረቃችሁ ዘንድ በሰራችሁት ስራ ኑሯችሁ በጸጸት የተሞላ ይሆናልና ተጠንቀቁ ! መረጃ ቅበላውን ለማኮላሸት ስንል አቅጣጫችን እንዳንስት ! ከዚህ ውጭ የምለው የለም ….!
ሰላም
ነቢዩ ሲራክ

No comments:

Post a Comment