የመረጃና የሃሳብ ነፃነትን ለጋራ ጥቅም እናውለው!
January 16, 2014
ቃልኪዳን ካሳሁን (ከኖርዌ)
ሀገሪቱ እየገነባች ያለው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የፈጣን ልማት ባለቤት አላደረጋትም። ባለፉት ሺ ዓመታት በኢትዮጵያ ያልነበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድንጀምርና በጋራ እንድናሳድግ እድል አልፈጠረም። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከመለያየትና ከፀረ እኩልነት አስተሳሰብ ወጥተው መከባበር፣ መደጋገፍና በልዩነት ውስጥ አንድ ሀገር መገንባት እንዲጀምሩ አላገዘም።
ይህ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት የዜጐችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አለማክበሩ ሊካድ አይችልም። ከምንም በላይ የዜጐች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እውን በመሆኑ ዛሬ በሀገሪቱ በርካታ የግል፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሕዝብ የህትመት ሚዲያዎች አይታተሙም። የማህበረሰብና የግል ሬዲዮ፣ ኤፍ ኤም ሬዲዮኖችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ አይደለም። የቴሌቪዥን አማራጮችም የሚሰፋበት ዕድል እንዳለ ተደጋግሞ ይገለጻል ግን ለናሙና እንካን የለም።
ጥያቄው ግን «የሃሳብ ነፃነት መብት መረጋገጥ ፋይዳው ምንድን ነው?» የሚለው ነው። ዜጐች ሃሳባቸውን በነፃነት የሚያንሸራሽሩት፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ያመኑበትን ለመፃፍ፣ ለመናገርና ለማስተላለፍ ነው። ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ፣ በአንድ ሃሳብም ሆነ በልዩነት ውስጥ ትልቋን ሀገር ለመገንባት ነው። በጋራ ጉዳያቸው ላይ ግልፅ አቋም ይዘው ለሕዝብ ጥቅም እንዲነሳሱ ማድረግም ነው።
ጥያቄው ግን «የሃሳብ ነፃነት መብት መረጋገጥ ፋይዳው ምንድን ነው?» የሚለው ነው። ዜጐች ሃሳባቸውን በነፃነት የሚያንሸራሽሩት፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ያመኑበትን ለመፃፍ፣ ለመናገርና ለማስተላለፍ ነው። ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ፣ በአንድ ሃሳብም ሆነ በልዩነት ውስጥ ትልቋን ሀገር ለመገንባት ነው። በጋራ ጉዳያቸው ላይ ግልፅ አቋም ይዘው ለሕዝብ ጥቅም እንዲነሳሱ ማድረግም ነው።
በሀገራችን ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ይመስላል። መንግሥት፣ ሕዝቡ፣ ሕዝባዊ ሚዲያውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሀገር ግንባታ ላይ አተኩረው ሲሰሩ አይስተዋልም። በዚያው ልክ አብዛኛው የግል የህትመት ሚዲያና የተቃዋሚው ጐራ ደግሞ በትችትና በእውነት ነገር ሲፅፉ፣ሲናገሩ መንግስት ተብዬው በማብጠልጠልና ብዙም ተጨባጭነት በሌላቸው አሉባልታዎች ላይ ተጠምደዋል። ገንቢ ትችትና አስተማሪ ዘገባ ለማቅረብ የሚሞክሩ ሚዲያዎች ቢኖሩም መንግስት ተብዬው ግን ብዙም አይዋጥለትም። የግሉ ፕሬስ መጠናከር የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ውጤት በመሆኑ አሁን ይበልጥ መቀጠል እንዳለበጥ የሚነገር አይደለምለ። መንግስት ተብዬው ግን በመረጃ ላይ ያልተመሠረተ፣ ሚዛናዊነት የጐደለው፣ ጥላቻና ክፋት የተላበሰ ነቀፌታ ያስተላልፋል። የትኛው ሀገርስ በዚህ መንገድ ተገንብቷል። ሀገራዊ በሆኑ የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ መዝመት ያልተቻለው ለምንድን ነው?
ሰብኣዊ ድረገጽ እንደሚያምነው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሁሉንም አጋርነት ይሻል። ትልቁ የዴሞክራሲ መገለጫ የመረጃ ነፃነትና ሃሳብን ያለገደብ የማራመድ ጉዳይም የህግ ጥበቃና የሥርዓት ዋስትና ሊያገኝ ይገባል። ይሄ ደግሞ ገና ከጠዋቱ በመንግስት በኩል እውን ያልሆነ ስራ ነው። ያም ሆኖ ሚዲያዎቻችን
አንደኛ፡- የሀገራችን የግልም ሆነ የሕዝብ ሚዲያዎች ለእውነትና ለሕዝብ ጥቅም እንዲቆሙ የጋዜጠኝነት የሙያ ሥነምግባር ያስገድዳቸዋል። ይህን ዓለምን ያግባባ መርህ በመጣስ በእንዝህላልነት ሕዝብን የዘነጉ አንዳንድ የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ህዝቦችን ለቀውስ ዳርገዋል። ባልተጨበጠ መረጃና በእውነት ላይ ያልተመሠረቱ «ልብሰቀይ» የልቦለድ ዘገባዎችም ብዙዎችን ጋዜጠኞች በሕግ አስጠይቀዋል። በሀገራችንም ቢሆን ከመነሻው አንስቶ በተሳሳተ መንገድ የበቀለ የአንዳንድ የህትመት ውጤቶች ጉዞ አልቀጠለም። ሥርዓትና ሕግ ብቻ ሳይሆን ከሙያ ሥነምግባሩና መርሁ ጋር ተላትመዋልና። ስለዚህ ከዚህ ዓይነት ስህተት ልንወጣ ይገባል።
ሁለተኛ፡- መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሊተች ይችላል። ግን ውጤቱንና ያስመዘገበውን ስኬት መጥቀስና መተንተንም ሐጢያት አይደለም። ዞሮ ዞሮ የሚገነባው ሀገር ነው። ሀገርና ሕዝብ ለመጥቀም የሚያስብና ኃላፊነት ያለው ሚዲያ ደግሞ ገንቢ ትችትን ሲያቀርብ፣ የስኬት እውነቱን በመካድ መሆን የለበትም፤ አይገባምም። ይህን የሚስቱ የሀገራችን አንዳንድ ሚዲያዎች የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ሂደት መሆኑን የሃሳብ ነፃነትም ሁሉንም የሚመለከት የሕግና ሥርዓት ልጓም እንዳለው ይዘነጉታል። በዚህም ቀስበቀስ እየኮሰሱ ከጨዋታ ለመውጣት ይዳረጋሉ።
ሦስተኛ፡- የዓለም ታዋቂ የሕትመት ውጤቶች በምርመራ ዘገባ በገንቢ ትችት እና በብሔራዊ ጉዳይ ላይ ባለመደራደር ነው የሚታወቁት። በእኛ ሀገር የትኛው የምርምር ሥራና አስተማሪ ዘገባ ቀረበ። በመቼውም ጊዜ የሙስና ወንጀል የመልካም አስተዳደር ጥሰት መንግሥትን አነቃ? መልስ መስጠት ያስቸግራል። እርግጥ ነው በጠንካራ ምርመራ ላይ የተመሠረተ ዘገባ ያደክማል። አቅምና መስዋዕትነት መክፈልን ይጠይቃል። ጊዜም ይፈልጋል። ለለብለብ ገበያም አይመችም። መጀመር ያለበት የሚዲያ ባህል ግን ይሄው ነው። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችንን የሚያሳድግ ሀገራችን የጀመረችውን ለውጥ በጥንካሬ የሚያስቀጥል ነውና።
የሕገ መንግሥታችን አንቀፅ 29ም ሆነ የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ 590/2000 ሥራ ላይ መዋል የሚጋብዘው በእውነትና በሚዛናዊነት ላይ የተመሠረተ ሃሳብን ማንሸራሸር ነው። ሕዝብን የሚከፋፍል ሀገርን የሚበድል ትውልድን እውነት የማያስተምር ዘገባ የሃሳብ ነፃነትን ይገድላል። ይባስ ብሎ «በሬ ወለደ…» እያሉ መዘገብ የሕግ ተጠያቂነትንም ሊያስከትል ይችላል። የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውንም ያቀጭጫል እንጂ አያሳድግም። ስለዚህ የሃሳብ ነፃነትና የመረጃ ነፃነት ዋነኛ መሣሪያ የሆነው የሕዝብና የግል ሚዲያ ለሕዝብና ለእውነት ይሥራ። ለሀገር ጥቅም ይቁም። መንግሥት ፓርቲና ግለሰብ ኃላፊ ናቸው። ሀገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ መሆናቸውን ዘወትር የሚያስታውስ የሚዲያ አስተሳሰብ ይፍጠር። ያኔ የመረጃና የሃሳብ ነፃነታችን ለጋራ ጥቅም ይውላል።
***ብዕር እንደ እሳት ይፋጃል***
የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ካከተመ በኋላ እና አለም ወደ አንድ የርዕዮት ዓለም ካምፕ እየገባች ባለችበት አጋጣሚ የስልጣን አክሊል የደፉት ገዢዎቻችን የነፃውን ፕሬስ ዓለም በዚች ሀገር እውን እንዲሆን ሁኔታዎችን ብናመቻች የሰለጠነው አለም ያከብረናል በማለታቸው በርካታ ጋዜጦችና መጽሄቶች ለህትመት በቅተው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ሆኖም ግን የነፃው ፕሬስ አርበኞች አደገኛውን የጎሳ ፖለቲካ መርዝ ለማርከስ እና የስርዓቱን ብልሹ አሰራር እንደ እሳት በሚፋጅ ብእራቸው ስለተቹ ጥሩ ነገርም ከተሰራ በማመስገናቸው የተነሳ የአገዛዙ አማካሪዎችም ሆኑ ፊት አውራሪዎች በበጎ አይን አልተመለከቷቸውም፡፡ የተለያዩ ስልቶችንም እየተጠቀሙ የነፃውን ፕሬስ አባላት የመበተን እርምጃ ወስደዋል፡፡
ለማንኛውም ከሁለት አስርተአመት በላይ ወጣትና አንጋፋ ጋዜጠኞች እንዲሁም ጥቂትአሳታሚዎች እንደ ጥጃ እየታሰሩና እየተፈቱ የተለኰሰው የፕሬስ ሻማ ድፍን እንዳይል ከባድ መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ፣ ክፍሌ ሙላት፣ ከፍያለው ማሞ ወዘተ ወደ ውጪ ሀገር የሄዱት ለሽርሽር አይደለም? በነፃው ፕሬስ መንደር መኖር ስላልቻሉ እንጂ፡፡
አለም አቀፍ እውቅና ያለውጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት አለሙ ወንጀለኞች አይደሉም ብዙ አምደኞችም ታፍነው የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ ጨለማ ቤት ውስጥ የተወረወሩት ለነፃው ፕሬስ ህልውና ሲሉ እጃቸው እስኪዝል በመፃፋቸው ይመስለኛል፡፡ስለሆነም ብዙዎች የተሰደዱለትና የታሰሩለት እንዲሁም አንዳንዶች ውድ ህይወታቸውን ቤዛ ያደረጉለት የነፃው ፕሬስ እስከወዲያኛው እንዳይዘጋ ከተፈለገ ህዝቡ እና አሳታሚዎች መተባበር ይገባቸዋል ባይ ነኝ፡፡የፕሬስ እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ለአንድ ነፃ ህብረተሰብ መሠረት ከመሆናቸው ባሻገር አንድ መንግስት ጠንካራ እንዲሆን ያስችላሉ ተብሎ ስለሚገመት በብዙ ሀገራት እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ነፃው ፕሬስ ሊያድግ የሚችለው ደግሞ በነፃነትና በውይይት እንጂ በማፈን አይመስለኝም ፤ ኦክሲጂን ለሰው ልጆች አስፈላጊ እንደሆነው ሁሉ ነፃነትም እንዲሁ ለፕሬስ ወሳኝ ነው፡፡
የፕሬስና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነድ (UDHR) ( አንቀጽ 19) በአውሮፓ ሰብአዊመብት ኮንቬንሽን (አንቀጽ 10) በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ኮንቬንሽን (አንቀጽ 13) በአፍሪካ የሰብአዊመብቶች ቻርተር (አንቀጽ 9) እና በኢትዮጵያው ህገ መንግስት (አንቀጽ29) ላይ ሰፍረዋል፡፡
ነፃው ፕሬስ ሰላምን ለማስፈን ማህበረሰቡ ዲሲፕሊን እንዲኖረው ለማድረግ፣ መብታችን እና ነፃነታችን እንዳይደፈር፣ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍኑ ሁነኛ ሚና ስለሚኖረው መንከባከብ ይገባል፡፡ በፖለቲካው ምህዳር ደግሞ ነፃው ፕሬስ ሰዎች ከባርነት ነፃ እንዲወጡ፣ እንዳይጨቆኑ፣ ሥቃይ እንዳይደርስባቸው መፍትሄ ጠቋሚ ነው፡፡ለአምባገነን ብዕር እንደ እሳት ስለሚፈሯት ያጠፏታል! እውነት ስለምትነገርበት።
ነፃው ፕሬስ ሰላምን ለማስፈን ማህበረሰቡ ዲሲፕሊን እንዲኖረው ለማድረግ፣ መብታችን እና ነፃነታችን እንዳይደፈር፣ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍኑ ሁነኛ ሚና ስለሚኖረው መንከባከብ ይገባል፡፡ በፖለቲካው ምህዳር ደግሞ ነፃው ፕሬስ ሰዎች ከባርነት ነፃ እንዲወጡ፣ እንዳይጨቆኑ፣ ሥቃይ እንዳይደርስባቸው መፍትሄ ጠቋሚ ነው፡፡ለአምባገነን ብዕር እንደ እሳት ስለሚፈሯት ያጠፏታል! እውነት ስለምትነገርበት።
ትክክለኛ መረጃ ሙሉ ሰው ያደርጋል።
http://ecadforum.com/
No comments:
Post a Comment