Sunday, January 12, 2014

የሰሜን ጎንደር የእስር ቤት አዛዥ ተገደሉ


ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢዎች ከጎንደር እንደገለጹት ኮማንደር አለባቸው የተባሉት የሰሜን ጎንደር ዞን የወይኔ ቤት አዛዥ የተገደሉት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ነው። ኮማንደሩ በጥይት መመታታቸው ቢገለጽም ዘጋቢያችን ማን እንደገደላቸው ለማወቅ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። የግለሰቡ አስከሬን ወደ ተወለዱበት በየዳ ወረዳ መላኩ ታውቋል።
አወጋን እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል። ድርጅቱ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ባወጣው መረጃ ” የሰሜን ጎንደር የማረሚያ ቤት ሀላፊ ኮማንደር መተከል አያልሰዉ እርምጃ ተወሰደበት ” ብሎአል:: አርምጃዉ የተወሰደዉ ትናት ማታ ሰባት ሰአት ሲሆን በተደጋጋሚ ከግፍ ስራዉ እንዲቆጠብ መልክት ቢደረሰዉም አሻፈረኝ በማለቱ ተገድሏል ” ብሎአል።
የኢሳት ዘጋቢዎች ሟቹን ኮማንደር አለባቸው ሲሉት አወጋን ደግሞ ኮማንደር መተከል ብሎታል። በጉዳዩ ላይ የሰሜን ጎንደር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊን ለማነጋገር ሙከራ ብናድርግም አልተሳካልንም።

No comments:

Post a Comment