Sunday, January 12, 2014

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?(ግርማ ሞገስ)


ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር። በጣት የሚቆጠረው የነገብረ ሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮና የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፣ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሰሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

No comments:

Post a Comment