Sunday, January 12, 2014

የሳዑዲ ጉዳይ፡ የአስከሬኑ ሽኝት – ከነብዩ ሲራክ

እጣ ፈንታ …
ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለም ስንብት … ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት ! ከሬሳው ማስቀመጫ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጋር ላፍታ ባደረግነው ቆይታ የሰማሁት አሳዛኝ ነባራዊ ሁኔታ ውስጤን አደማው ። ሬሳውን ወደ ምንቀበልበት የጓዳ በር ለየራሳችን ቆዛዝመን ደረስን: ( ታሞ ፣ እህት ሚስቱ አስታምመውት ፣ ማንነቱ ታውቆ እና ወደ ሃገር መላኪያ ገንዘብ ተገኝቶ ዛሬ ወደ ሃገር ለመሄድ ተዘጋጅቷል ፣ ከምሽቱ 9:45 … የብርቱ ወዳጀ አብሮ አደግ ከፈን ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ወጣ … በተዘጋጀው የእንጨት ሳጥን ሆኖ ወደ አንቡላንስ ከመሸኘቱ በፊት በስትሬቸር እየተገፋ መጣና ለስንበት ፊቱ በአንድ የፊሊፒን የሬሳው ክፍል ሰራተኛ ተገለጠ … ያ ዘንካታ አይኑን ጨፍኖ ታጋድሟል …አንጀንታቸው የሚላወሰውን እህት ፣ ሚስት፣ ጓደኞች እና ጎረቤቶች ሃዘናቸውን እንደፈለጉ ጮኸው በማይገልጹበት ግቢ የወንድማቸውን በድን ተሰናበቱት … በሬሳው ክፍል ሃላፊ ባጫወተኝ አሳዛኝ ታሪክ ተጽናንቸ የነበርኩት እኔም እህት የወንድሟን ፣ ሚስት የባሏን ግንባር እየሳሙ በታመቀ የሃዘን ስሜት ድምጻቸውን አርቀው እያነቡ ሲሰናበቱት ሳይ ብርክ ያዘኝ ! ሽኝት … በእርግጥም እኒህኞቹ ወገኖችም ሆኖ ታሞ አስታመውት የሞተው ወንደም እድለኛ ነው! ነገ የሃገሩን አፈር ፣ ታሞ እያለ እናቱን ናፍቆ ሁለቴ ለመሄድ ተነስቶ በተመለሰበት አውሮፕላን ዛሬ በድኑ በውድ ዋጋ ተጭኖ ይደርሳል ! እናት እና ልጅ ተነፋፍቀው አልተገናኙም: ( እናም አልሰሜ እናት አለም ነገ ሬሳ ለመቀበል በጠዋት መርዶ ይጠብቃታል ! ህይወት እንዲህ ነው የሞተውን ነፍስ ይማር ! እናት እና መላ ቤተሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባል? ሌላ አሳዛኝ ታሪክ ትረካ በቪድዮ Ze-Habesha

No comments:

Post a Comment