Saturday, January 11, 2014

የደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞችን 24 ሰአት አሰረች፣ ሻንጣቸውም አልተመለሰም፡፡

https://www.facebook.com/DireTubeFans

ሀሙስ ጠዋት በስማቸው ከካፍ የተላከላቸውን አክሪዲቴሽን (ጨዋታ የመዘገብ እና ወደደቡብ አፍሪካ የመግቢያ ወረቀት) እንዲሁም የጉዞ መስፈርቶችን አሟልተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቻን ውድድር ለመዘገብ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀኑት የስፖርት ጋዜጠኞቹ ፍስሀ ይድነቃቸው ከኢቢኤስ ስፖርት፣ ኢብራሂም ሻፊ ከአዲስ ጉዳይ፣ ይስሀቅ በላይ ከሀትሪክ ስፖርት ለ24 ሰአት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ 

በደቡብ አፍሪካ ሰአት አቆጣጠር ሀሙስ ከቀኑ 7፡30 ጆሀንስበርግ ቢገቡም የኢሚግሬሽን ሰዎች ካፍ የላከውን የይለፍ ወረቀት አንቀበልም በህገወጥ መንገድ ነው የገባችሁት በማለት ሶስቱንም ጋዜጠኞች በኤርፖርት አካባቢ እሚገኝ ከመሬት በታች በሁነ እስር ቤት ውስጥ ለ24 ሰአት አስረው አቆይተዋቸዋል፡፤ እንደ ኢቢሱ ፍስሀ ይድነቃቸው ከሆነ ለኢሚግሬሽን ሀላፊዎቹ ከዚህ ቀደም ደቡብ አፍሪካ መጥተን መመለሳችንን የአለም አቀፉ ጋዜጠኞች ማህበር አባል መሆናችንን የሚገልፅ ዶክመንቶችን ብናሳያቸውም አሰራራችን ቀይረናል በሚል ሊያደምጡን ፍቃደኛ አልሆኑም ብሎአል፡፡

ከሰው እንዳንገኛኝም ስልኮቻችንን ቢቀሙንም ከእስር ልንወጣ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ ለእስር ቤቱ ጠባቂ ገንዘብ በመስጠት ስልክ ወደ ኢትዮጵያ ኢምባሲ ለመደወል ችለናል፣ የኢምባሲ ሰዎችም አድራሻችሁ እኮ ጠፋን ብለው ጭንቀት ላይ እንደነበሩ ተረድተናል ኢምባሲውና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን መያዛችን ከሰሙ ሰአት ጀምሮ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የደቡብ አፍሪካ የኢምግሬሽን ሰዎች ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም ብሎአል፡፡

አቶ ጁነዲን እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰዎች መያዛችንን የሰሙት ቤቴል ከተባለ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም የደቡብ አፍሪካ የኢምግሬሽን ፖሊሶች ከሰው እንዳንገናኝ ስለከለከሉን የት እንዳለን ለማወቅ ተቸግረው ነበር ያለው ጋዜጠኛ ፍስሀ ከደቡብ አፍሪካ ስንመለስ ፓስፖርታችን ብቻ ነው ይዘን የተመለስነው የሶስታችንም ሻንጣዎች እዛው ደቡብ አፍሪካ አስቀርተዋቸዋል ብሎአል፡፡

ልክ እንደነ ፍስሀ በተመሳሳይ በካፍ ደብዳቤ የሄዱት ሌሎች 4ት ጋዜጠኞች እንዲገቡ ሲፈቀድላቸው የተወሰኑት ወደ እስርቤት መወሰዳቸውን ተናግሮአል፡፡

ከነዚህም መካከል ፎቶግራፈሩ ደመቀ እንደሚገኝበት ታውቆአል፤፤ አዲስ አበባ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይገቡ ቪዛ አልሰጥም ብሎአል፡፤ የኢትዮጵያ የቻን ቡድንም በቪዛ ምክንያት ጉዞውን ከሩቡዕ ወደ አርብ መቀየሩ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ቡድን ተካላካይ የሆነው ቶክ ጀምስ ሻንጣ ደቡብ አፍሪካ ኤርፖርት ውስጥ መጥፋቱም ታውቃል፡፤

ታደለ አሰፋ
More News update @http://diretu.be/sport

No comments:

Post a Comment