Friday, January 10, 2014

”በበኩሌ የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ ነኝ ” !! በኢትዮጵያዊነቴ እንጂ፡ በጠባብ ብሔረተኝነት አልወናበድም እምዬ አፄ ምኒሊክ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባብረው ባያዋጉና ባያሸንፉ፡ የኛም አያቶች ዕጣቸው ይኽ ነበረ!!!!!!! “


እነዚህ አፍሪካውያን የኮንጎ ተወላጆች ናቸው። በገዛ ሃገራቸው የቤልጂየም ቅኝ ተገዢዎች ሆነው፡ በሰንሰለት የታሰሩ የነጮች ባሪያ ሆነው፡ የመከራ ጊዜ ያሳለፉ ምስኪኖች ነበሩ። በግራና ቀኝ ጠመንጃ የያዙት ደግሞ ልክ ሙሶሊኒ የጣሊያኑ ወራሪ ሠራዊት አሰማርቶ ሃገራችን ኢትዮጵያን በወረረ ወቅት የነመለስ ዘናዊ አባትና አያትን ባንዳ አድርጎ እንደመለመላቸው የገዛ ሃገራቸውን ዜጋ እየወጉና እያሰቃዩ የነበሩ ወራዳ ባንዳዎች ናቸው።
የሰሞኑ ወያኔ በእጅ አዙር ቴዲ አፍሮ ላይ ያዘመተው ዘመቻ፡ ቀድሞውኑ የተዘጋጀ የወያኔ ሰላይ መሠሪዎች ተግባር ነው። ቴዲ አፍሮ ለሚናገራቸው ቃላቶች በሳል ወጣት አርቲስት መሆኑን እናውቃለን።

ጭንቅላታቸው ማሰብ የተሳናቸውን ጥቂት የምሁር መሃይማንና በበታች ስሜት የሚሰቃዩትን የነጃዋር መሃመድ ሃይማኖታዊ አክራሪ አድመኞችን ጭምር ነው።
በበኩሌ የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ ነኝ ” በኢትዮጵያዊነቴ እንጂ፡ በጠባብ ብሔረተኝነት አልወናበድም “
ኦሮሚያ የሚባል መሬትና ቦታ በኢትዮጵያ ታሪክ የሌለ ነገር ነው። ወያኔ ከተማ ከገባ በኋላ ግን የኦሮሞ ብሔረሰብን ለማጋጨት ትናንሽ አስተሳሰብ ያላቸውን የምሁር መሃይማንን ሞልቶ ወከባ ፈጠረ። ኦነግ የሚባለውም ተጃጃለበት፤ የኦሮሞ ሕዝብም አንዲት ኢትዮጵያ፤ አንድ ሕዝብ ብሎ ፋሽስት ወያኔዎችን ለማንበርከክ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተነስቷል።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!!!!

No comments:

Post a Comment