Saturday, January 11, 2014

ኦሮሞና አማራን ለመለየት የተዘጋጀው የወያኔ ወንፊት ጥቅጥቅ ይልና ኦሮሞንና አማራን ለመለየትና ለመከፋፈል አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል , ተወደደም ተጠላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በኦሮሞና በአማራው እጅ መሆኑ መዘንጋት የለበትም!!!



የሚገርመውና የማይረሳው ቁም ነገር ደግሞ ይህ ነበር፡፡ የአክሱም ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው ሲለው የተናደደው የጋሽ ቶጋ ልጅ ተሾመ ነው ሮም የነበረውን የአክሱም ሐውልት ያስመለሰው፡፡ ብዙ ውስብስብና አስቸጋሪ ውጣ ውረዶች ቢኖሩበትም ባድመ ምኑ ነው የተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ውለታ ቢሶቹን ትግራዮች የታደጋቸው፡፡
ወያኔ የኦሮሞን ሕዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት በአሁን ሰዓት የሚጠቀምበትን ስልት እምዬ ምኒልክ እንዳልተጠቀሙበት ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪ ባልሆንም እንዳንድ እውነታዎችን ብጠቅስ ለተመራማሪዎች ግብዓት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከሰፈረበት የመልካምድር አቀማመጥ አንጻር ባህሉ ልዩነት ሊኖረው ችሏል፡፡ እኔ ባህል ስል የእምነት ባህል፣ የአለባበስ ባሕል፣ የጋብቻ ባህል፣ የአኗኗር ባህል፣ ወዘተ. ነጮቹ Cultural Diffusion እንደሚሉት ሊመጋገብ ይችላል፡፡ በሸዋ አካባቢ ያለው ኦሮሞ ከአማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ ጋር ተቀራርቦ በመኖሩ በሁለቱ ቢሔረሰቦች መካከል እንዳንድ የባህል ውርርስ ቢታይ ዛሬ ወያኔ እንደሚያናፍሰው ሳይሆን አብሮ በመኖር ሂደት የተፈጠረ ማህበራዊ ግኑኝነት በመሆኑ ሊፋቅ የማይችል ነው፡፡ በሐረር አካባቢ የሚኖር ኦሮሞ እንዳንድ ባህል ከሶማሌ፣ ከአደሬ፣ ከአፋር፣ ከኢሳ፣ ወዘተ በአለባበስ፣ በንግግር ፣ በጋብቻ፣ ወዘተ ቢመሳሰል ምንም ሀጢአት የለውም፡፡ የቦረና ኦሮሞ ከገሪ፣ ገሪ መሮ፣ ሶማሌ፣ ወዘተ ባህል ሊለዋወጥ ግድ ነው፡፡ የአርሲ ኦሮሞም እነደዚሁ ከአካባቢው ህዝብ ጋር የባህል ልውውጥ ሊኖረው ይችላል፡፡ ታዲያ ምንድነው ችግሩ? ምን ይሁን ነው የሚባው?
ሕዝብ ለሕዝብ አብሮ በመኖር ሂደት ባህል ሊጋራ መቻሉ ዛሬ እንደ ሃጢአት ተቆጥሮ የአሮሞንና አማራን ሕዝብ ለረጅም ጊዜ አብረው በመኖር ያካበቱትን ማህበራዊ እሴት አፈራርሶ 150 ዓመት ወደ ኋላ ለመሄድ ጊዜን Rewind ለማድረግ እንደመሞከር ነው፡፡ እንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ እኔ አማራ ነኝ፡፡ ብሆንም ግን ተወልጄ ባደግሁበት አካባቢ እየተመገብኩ የኖርኩትን ጩኮና ጨጨብሳ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ስለሆነ ያንተ ባህል አይደለምና ተው ብሎ ከፊቴ የሚቆም ምን ዓይነት ኃይል ያለው ሰው ሊኖር ይችላል? የሰው ስም እየጠቀስኩ እከሌ የሚባል ኦሮሞ ብዬ አስተያየት ለመስጠት ብቸገርም በተለይ አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ግን ለምን ስለ አብሮነት አጥብቀው አይከራከሩም ብል የተሳታትኩ አይመስለኝም፡፡ አንድነት ኃይል ነው፡፡ ከአምባላጌ ተራራና ከደደቢት የተነሱ እፍኝ የማይሞሉ መሃይም እረኞች በነደፉት የተሳሳተ የመከፋፈል ፍልስፍና ለምን ምርኮኛ ሆኑ ብዬ ብጠይቃቸው ከድፍረት አይቆጠርብኝም፡፡ ምክንያቱም እንደ አቶ ቡልቻ ካለ አንጋፋ ምሁርና ታዛቢ ሽማግሌ ለኦሮሞው ከትግሬው ይልቅ አማራው በዘር፣ በሃይማኖት፣ በባህል ትስስር፣ ወዘተ. እንደሚቀርበው ይጠፋቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ የዶ/ር በያንን ወቅታዊ የእርምት መግለጫ ስለተከታተልኩ አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ዶ/ሮ መራራ ጉዲና ግን ግዴታው ነው፡፡ ለምን ቢባል ኦሮሞና አማራን ለመለየት የተዘጋጀው የወያኔ ወንፊት ሸዋ ላይ ሲደርስ ጥቅጥቅ ይልና ኦሮሞንና አማራን ለመለየትና ለመከፋፈል አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል ብዬ አምናለሁ፡፡
ወደድንም ጠላንም በአንድ ነገር መስማማት አለብን፡፡ አሁን ያለንበት ጊዜ የሥልጣኔና ወደፈት የመራመድ እንጂ የወያኔው ፈላስፋ መለስ ዜናዊ አጥልቆልን የሄደውን የመከፋፈልና የመለያየት ጥቡቆ አናወለወቅም ብለን የምንጃጃልበት ወቅት አይደለም፡፡ ወያኔ የራሱን አገር እያለማና ሕዝቡን እያበለፀገ ኦሮሞና አማራን ግን እንደ ጀዋር ዓይነት፣ አረቦች ወሰክ የሚሉት ዓይነት ካድሬ በማሰለፍ ለማጋጨት ሲሞክር ይታያል፡፡ ለማጠቃልል በመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ነሳሁተን የስብሃት ነጋን አባባልና የትግራይ ህዝብን ዝምታ አሁንም እደግማለሁ፡፡ የአክሱም ስልጣኔ ተንቤንን፣ እነደርታንና አጋሜን አይመለከትም የሚል ከፋፋይ ፍልስፍና ቢያቀርብም የእነዚህ ሦስት አውራጃ ትግሬዎች ግን በአሁኑ ሰዓት ከሌላው ትግራይ ሕዝብ ጋር አብረን ተጠቃሚ ነን፣ ደግሞስ ይሄ የጃጀና የዞረበት ሽማግሌ የፈለገውን ቢያወራ ማን ይሰማዋል በማለት የስርዓቱ ተጠቃሚነታቸውን ቀጥለውበታል፡፡ ኦሮሞና አማራም ልክ እንደዚሁ ጀዋርም ሆነ ሌላ ከፋከፈይና ገንጣይ ወያኔ የሚያወራውን ቦታባለምስጠት ስለወደፊቱ ማሰብ አለባቸው፡፡ ተወደደም ተጠላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በኦሮሞና በአማራው እጅ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ 

ፍቅር፣ ሰላምና ብልጽግና ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን፡፡

No comments:

Post a Comment