Thursday, January 16, 2014

ከልቤ አዝኜ ፃፍኩት::) የቤንሻንጉል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ወሰነ:: Nigus kifle.

ከልቤ አዝኜ ፃፍኩት::)

የቤንሻንጉል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ወሰነ:: ፓርቲው ከዚህ ውሳኔ የደረሰው የድርጅቱ ሊቀመምበር የነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምና ሌሎች አመራሮች በሴራ ፖለቲካ በመታሰራቸው ሲሆን የክልሉ ህዝቦች እራሳቸውን ችለው አገር ቢመሰርቱ ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑና የተፈጥሮ ሃብቱ ደግሞ የተትረፈረፈ በመሆኑ የእያንዳንዱ ነዋሪ ኑሮ በከፍተኛ ፍጥነት መቀየር እንደሚችል በክልሉ የሚገኙት ተቀራራቢ ባህል ያላቸው ብሄረሰቦች መግባባት ላይ በመድረሳቸው ነው::
ሆኖም ታማኝ ምንጮች እንደዘገቡት ከሆነ፣ ለክልሉ ፖለቲከኞች የመገንጠል ሃሳብን ያቀረበውና ከጀርባ ሆኖ የሚመራው የግብፅ መንግስት ሲሆን የግብፅ መንግስት ክልሉ ከተገነጠለ በኌላ እየተገነባ ያለውን የአባይ ግድብ በማቆም በምትኩ የቤንሻንጉል ህዝብን በየአመቱ በከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ለማበልፀግ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነው::
ይህ የአንቀፅ 39 ቅዥት ነው!! ሊሆንም ላይሆንም የሚችል ህልም::
አይበለውና ግብፅ በሚካሄደው ድርድር አልስማማም ብላ ግድቡን ለማፍረስ ብትወስንና ጦርነት ቢነሳ የሚዋጋው የትኛው ኢትዮጵያዊ ነው? ማለቴ ድሮ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ አንድ አገር ስለነበረች ለአገር ዘብ ቆሞ ህይወትን መገበር ብዙም የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይሆንም ነበር:: አሁን ግን ነገሮች ተቀያይረዋል የትኛውም ክልል ባሻው ሰዓት ኢትዮጵያዊነት ደበረኝ ካለ እንደ ኤርትራ ሊነካው ይችላል ተብሎ በሕገመንግስቱ ተደንግጓል:: እናስ ነገ ሃብቱን ወይም ቅራቅንቦውን ሰብስቦ ናላው በዞረ ዘረኛ ፖለቲከኛ ተነሳስቶ ላሽ ሊል ለሚችል ክልል እንዴት ነው ህይወትን የሚያክል ክቡር ነገር መሰዋት ለማድረግ የሚከፍል ሞኝ ዜጋ የሚገኘው? ጃዋርና ተከታዬቹን ያየና ፍርሃት የወረረው በሙሉ ልብ አገር አለኝ ብሎ ኦሮሚያ ላይ ቋሚ ነገር ኢንቨስት የሚያደርገው?
እስኪ አስቡት፣ ባድመ ተወረረች በማለት ሆ ብሎ በመነሳት በአስከፊው ጦርነት ተሳትፎ ለኢቶጵያ ሉአላዊነት መከበር እንደቅጠል የረገፈው ትውልድ ወገን ትግራይ ብትገነጠል ምን ሊሰማው እንደሚችል ? ሟቾቹስ ለማን ሲሉ ሞቱ ይባላል?
(አያቶቻችን ከአራቱም የአገራችን መዓዘን ተመው አገራችንን በነጭ ላለማስደፈር አድዋ ላይ ተዋድቀው ነፃነትን አስረክበውን እኛ የልጅ ልጆቻቸው በአጥንትና በደማቸው ያቆዩልንን አገር ባሻን ሰዓት እንደ የመንደር የእግርኳስ ቡድን መበታተን እንችላለን ብለን ስናስብ ከልቤ አዝኜ ፃፍኩት::)
Nigus kifle.

No comments:

Post a Comment