Thursday, January 16, 2014

አንድነት ፓርቲ ለአማራ ክልል እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝብ ግልፅ እንዲሆን በደብዳቤ አሳሰበ ያሬድ አማረ


Finote nestanet
አንድነት ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ዙሪያ ጥር 18ቀን 2006ዓ.ም ህዝባዊ ውይይት እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ዙሪያ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝብ እንዲሰጥ በደብዳቤ ጠየቀ፡፡
የአንድነት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የግዴለሽ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጎዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱና የተለማመድው በመሆኑ አሁንም በተለመደው ግብሩ ለህዝብ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ሊካሄድ የታቀደው የድንበር ማካለል የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም እንደሚችል ፓርቲው ከፍተኛ ስጋት ስላደረበት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለና በሚስጥር የያዘው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደርም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ ድንበር ማካለሉ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ ለህዝቡ በአጭር ግዜ ውስጥ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ገልፀዋል ፡፡

No comments:

Post a Comment