Thursday, January 16, 2014

የህወሃት ኤፈርት ባለስልጣኖች ወደ ውጪ ሀገር በመሄድ የንግድ ድርጅት በግለሰብ ደረጃ እየገዙ ነው ተባለ


በቅርቡ ከሁለት ወር በፊት የኤፈርት ልኡክ ቡድን ወደ አሜሪካ ተልእኮ እንደነበርም አስረድቷል። 
ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የህወሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው ሲል የግንቦት 7 ሬዲዮ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።
(አባይ ሚዲያ) የኢትዮጵያ መንግስት የሆነው ህወሃት በሀገራችን ሰላምና ፍትህ፣ ልማትና እድገት እየመጣ ነው እያለ የተረጋጋ መሆኑን በማስመሰል በየጊዜው ይናገራል።  ነገርግን የሀገሪቱን ገንዘብ በተዘዋዋሪ በውጪ  በሚኖሩ የስርአቱ አግልጋዮች ስም የቦታና የንግድ ግዢ  በውጪ ሀገር የማድረግ ስራ በሰፊው እየተፋፈመ  መሆኑን የውስጥ ዜና ምንጮቻችን ገልፀዋል። በተለይም በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች በጉብኝት ስም ታማኝ ሰዎችን በመላክ የሀገሪቱን ገንዘብ በማሸሽ ቦታና የንግድ ማእከሎችን እንዲገዙ እየተደረገ ነው።       ህወሃት ራሱ ያልተረጋጋ እና አደጋ ያንጃበበት በመሆኑ ውስጣቸው መረጋጋት እንደሌለበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ታዲያ ይህንን ፍርሃት በመሸፈን በበላይነት የህወሃት ኤፈርት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን ገንዘብ የማሸሽን ዘዴ እንደ አንድ አማራጪ ወስደው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለማሸሽ እየተዘጋጁ ነው ሲል መረጃውን የላከልን ዘጋቢያችን አስታውቋል። 

No comments:

Post a Comment