Saturday, January 4, 2014

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስራች ጉባኤ በአዲስ ቪው ሆቴል ተከናወነ


XXX

የግዛቸው ካቢኔ በወጣቶች ተገንብቷል
ዛሬ በአዲስ ቪው ሆቴል ኢንጂነር ግዛቸው በአብዛኛው በወጣት የተያዘውን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል።
‹‹የካቢኔ አባላቱን ከመምረጤ በፊት አባላቱ አስተያየትና ጥቆማ እንዲሰጡኝ በሩን ክፍት በማድረግ የብዙዎችን አስተያየት ተቀብያለሁ፡፡ሌላው መስፈርቱ የትምህርት ዝግጅት፣የፖለቲካ ልምድና ተባብሮ የመስራት ባህል ለመመልከት ሞክሪያለሁ፡፡በዚሁ መሰረትም የሚከተሉትን ሰዎች የካቢኔ አባላት እንዲሆኑ ወስኛለሁ››ያሉት ግዛቸው ሽፈራው ናቸው ፡፡ከካቢኔው አባላት መካከል ከ65 በመቶ በላይ በወጣቶች የተገነባ ነው፡፡ስድስት የማስተርስ ሰባት ባችለር ሁለት ዲፕሎማ ያላቸው መሆናቸውን ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝራቸውም የሚከተሉት ናቸው፦
1) አቶ ተክሌ በቀለ ——- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት
3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ
4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ
6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ
7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ
8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ
9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ
10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ
11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ
12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- ( የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስራች ጉባኤ በአዲስ ቪው ሆቴል እየተከናወነ ነው
VV
የብሄራዊ ምክር ቤቱን በአፈጉባኤነት ሊመሩ የሚችሉ ሰዎች ምርጫ ተከናውኗል፡፡በዚሁ መሰረትም አቶ አበበ አካሉ አፈጉባኤ፣ጸሐፊ ፍቃዱ ሰጠኝ፣ምክትል ጸሐፊ ዋና ጸሐፊ አቶ ነቢዮ ባዘዘው በመሆን ተመርጠው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment