Wednesday, January 15, 2014

" የዜግነት ውርደቱን ዳር እስከዳር ጨልሞበት እያየ፡" አሁንም የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ታየ ብሎ የሚዘምር፡ አይኑን በጨው ያጠበ ኢትዮጵያዊ አለ እንዴ?

" የዜግነት ውርደቱን ዳር እስከዳር ጨልሞበት እያየ፡" አሁንም የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ታየ ብሎ የሚዘምር፡ አይኑን በጨው ያጠበ ኢትዮጵያዊ አለ እንዴ? ለነገሩ የፋሽስት ወያኔ የጥፋት ፖለቲካ ወያላዎችና አራጋቢዎች ወይም የወያኔ የቀጥታና የተዘዋዋሪ አባሎች " ኢትዮጵያዊ " ተብለው አይጠሩም!
የተዘዋዋሪ ወያኔ ወያላዎች የሚባሉት መሃል ሰፋሪ ሆነው ለማምታታት እኔ ፖለቲካ አልወድም፤ ፖለቲካን ምንትስ በሩቁ የሚሉ ናቸው። ሰንደቅዓላማችንን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ዓርማችንን አውለብልቦ ለመዘመርም ሆነ ሃገርን የሚያክል ነገር ለማክበር በመጀመሪያ ሃገራችንና ሕዝባችንን ያዋረደውን ወያኔ የሚባለውን DDMS (DEDEBIT DEVIL MINDED SPIRIT) ቫይረስ ማስወገድ፤ ማውገዝ፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ማድረግ የዜግነትን ክብር አስመልሶ ወደ ነጻነት የሚያመራ መንገድ ነው።
አንድ በውጭ ሃገር አዲስ የተፈጠረ፤ በበታችነት ስሜት እራሱን ያጠቃ ጸረ ኢትዮጵያዊያን ጥቂት የጃዋር መሃመድ ፋራ ቡድን በፓልቶክና በተለያዩ ድህረ ገጾች ሲጃጃሉ የቁቤ ጀነሬሽን ነን ሲሉ ሰምተናል። ወይ ውርደት ብለን አላለፍናቸውም። ፋራ የሚለው የአራዳው ቃል ለነዚህ የሚስማማ  በቂ ነው። ምክንያቱም በራሳቸው ጊዜ በፈጠራ ታሪክ እራሳቸውን ያጃጃሉ ከዘመናዊው ዓለም ወደ ጥንታዊው የንትርክና የጸብ እንዲሁም ጥልቅ የሆነ የበታችነት ስሜት የሚያንጸባርቁ የጸረ አንድነት ቡድኖች ናቸው። የአንድነታችንና የነጻነታችንን አባት እምዬ አጼ ምኒልክን ሲተቹ ብልግናቸው ከምንም በላይ ነው።
የሚገርመው ነገር ቀለም ቆጥረው፤ የአካዳሚክስ እውቀታቸው በተለያዩ ሙያዎች እስከ ፒ ኤች ዲ ዲግሪ ያለቸው ሆነው ነገሮችን እንዳያገናዝቡ እራሳቸውን በራሳቸው ያደደቡ መሆናቸው ከሚናገሯቸው ጸያፍ ቃላቶች አድምጠናል። በርግጥም ፋራ የሚለው ቃል ለነዚህ ዘልዛላዎች በጣም ተስማሚ ነው። ከዘመናዊው አስተሳሰብ ወደ ጥንታዊው የባርነት ዘመን እራሳቸውን ያዘቀጡ፤ የዜግነት ውርደትን ተሸክመው የዜግነት ክብር በብሔረተኝነት የሚገኝ መስሏቸው በብሔራቸው የሚያመልኩ ወራዳዎች ስለሆኑ " የኢትዮጵያ አምላክ ልቡና ይስጣቸው "።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!!!!!!!!!!!!

No comments:

Post a Comment