Saturday, January 4, 2014

የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ (ኢሕአፓ)


ከ ሕዳር 19 ቀን እስከ ሕዳር 21 2006 ዓ.ም. ባሉት ቀናት የተካሄደው 5ኛው የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በሀገራዊ በዓለም አቀፍና በድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ የሆነ ውይይት አድርጎና የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፎ ለሚመለከታቸው የፓርቲው አባላትና አካላት መመሪያዎችን አስተላልፏል ።
መደበኛው ስብሰባው ሀገራችን ያልችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት መርምሮ ከተለያዩ ግንዛቤዎች ላይ የደረሰ ሲሆን ትግሉን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ቁንጮ በመሆን የወያኔን አምባገነነ ቡድን ሲያሽከረክር የቆየውን መለስ ዜናዊን የተካ ግለሰብ አለመከሰቱና በቡድኑ ውስጥ የውህደት ችግር መኖሩ ከግምት ውስጥ ማስገባት የሚቻል ቢሆንም አሁንም ቢሆን በስልጣን ላይ ያለው ይህ አጥፊ ቡድን በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ አፈናና ብዝበዛ በሰፊው መቀጠሉን መደበኛ ስብሰባው ተገንዝቧል። የዜጎች መብት አለመከበሩን፤ የዜጎች አፈና እስራትና ግድያ በሰፊው የቀጠሉ መሆናቸውን፤በጋዜጠኞች፤ በመምህራን በተማሪዎች፤ በሰራተኞችና በአርሶ አደሮች ላይ እየተካሄዱ ያሉት አፈና፤ እስራትና ግድያ በሰፊው የቀጠሉበት ሁነታ መኖሩን፤ በሃይማኖቱ ውስጥ ጣልቃ የመግባትና የሃይማኖት ተቋሞችን በቡድኑ ቁጥጥር ስር የማድረጉ አስከፊ ተግባር በሰፊው ቀጥሎ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው የመብት መገደብና አፈና ተጠናክሮ መቀጠሉን፤ በሳኡዲ አረበያና በሌሎች ቦታዎች በደል ለሚደርስባቸው ወገኖቻችን ስቃይ ምንጩ የወያኔ አገዛዝ መሆኑን፤ ሕዝባችን በድህነት እየማቀቀና በዋጋ ግሽበት እየተሰቃየ የአገራችን አንጡራ ሀብት ግን አሁንም በገፍ እየተዘረፈ መሆኑን፤ ወያኔ የሀገራችንን መሬት ለባእዳን እየቸበቸበ አርሶ አደሩን ከመሬቱ እያፈናቀለና ችግር ላይ እየጣለ መሆኑና ሌሎችንም በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት መደበኛው ስብሰባ በሰፊው ተወያይቶ ከግንዛቤ ላይ ደርሷል። ወቅቱ የወያኔ አገዛዝ ከመቸውም ጊዜ በላይ ከሕዝብ የተነጠለበት በመሆኑ ሕዝባዊ ትግሉን አፋፋሞ ይህን አፋኝና አምባገነነ አገዛዝ ማስወገድ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ድምዳሜ ላይ ደርሷል።
EPRP.com

No comments:

Post a Comment