Saturday, January 4, 2014

በአንባሳደር መሃመድ ሃስን የሚመሩ የመንግስት ሹማንቶች ሪያድ መንፉሃ ውስጥ ኢትዮጵያኑ እንዲጨፈጨፉ ሲያሴሩ የከረሙት ደባ መክሸፉ ተገለፀ !.

 ኢትዮጵያውያኑንን ከሳውዲ ፅጥታ ሃይሎች ለማጋጨጥ ዲፕሎማቱ በሰጡት የተሳሳተ መረጃ  ረበዕ ምሸት መንፉሃ ውስጥ በኢትዮጵያ ውያኑ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፍተሻ መካሄዱን የሚገልጹ የአካባቢው ነዋሪዎች ኤንባሲው ሲመኝ፡የነብረው ብጥብጥ ሁከት ባለመከሰቱ  የዲፕሎማቱ ሴራ መቀልበሱን  ያስረዳሉ ።   

ሰሞኑንን በስውዲ አረቢ ያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በስሩ ለሚገኙ የብሄር  ልማት ማህበራት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ባስተላለፈው የስብሰባ ጥሪ የሳውዲ መንግስት ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ ካስቀመጠው ማመዘኛ ውጭ የመኖሪያ ፈቃድ እያላቸው በግል ተቀጥረው ህይወታቸውን የሚመሩ አሊያም እንደማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን ጉዳዩቻቸውን በማስተካከል ጥረት ላይ ያሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በሃጅ እና ኡምራ ከገቡ እና በተለያዩ ግዜያት በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ ምድር በህገወጥ መንገድ እንደገቡ ከሚነገርላቸው ወገኖች ጋር በመፈረጅ ከሃገር እንዲወጡ ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ታድነው ከሃገር እንዲባረሩ ሰጥተው የነበረው መረጃ መክሸፉን ምንጮች ከሪያድ አስታውቀዋል።. 

የሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ኤንባሲ በደረሳቸው መረጃ መሰረት መንፉ ከ 10 ሺህ በሚበልጡ ልዩ የስውዲ ኮማንዲስቶች ዲሰምበር 25 2013 ረዕቡ ቀትር በኢትዮጵያ ሰአት አቋጣጠር ከቀኑ 6 ሰአት ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት በዘለቀው ድንገተኛ አሰሳ በባሀር እንደግቡ የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ጨምሮ አያሌ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን መይዛቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የጸጥታ ሃይላቱ ፍተሻ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ያነጣጠር መሆኑ ወገኖቻችን ሌሊቱን ክፉኛ ተሸብረው በጭንቀት ለማለፍ ቢገደዱም የሳውዲያኑ እርምጃ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ወገኖች ላይ ብቻ በመሆኑ ህብረተስቡ መረጋጋቱን ገልጸዋል. በዚህ አሰሳ ጥቆማ የተደረገባቸው የኢትዮጵያውያኑ ቤቶች ተሰብረው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ህገወጥ ሰዎችን ብቻ እየመረጡ እንደወስዱ የሚገልጹት እንዚህ ምንጮች የረበዕ ዕለት የቤት ለቤት እና የመንገድ ላይ ፈተሻው በከፈተኛ የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት የታገዘ እና ጥንቃቄ የተሞላበት እንደነበር በመግለጽ ቀደም ብሎ ከነበረው የተለየ እና ደንብ እና ስረአትን የጠበቀ አካሄድ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በኢትዮጵያውያኑ ዙሪያ ያቀረበው የተሳሳተ መረጃ የቱንም ያህል ግቡን እንዳልመታ አክለው ገልጸዋል. 

ህጋዊ እና ህገወጡን ለይቶ መናገር የተሳነው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ከባለቤቱ በላይ አውቂ መሆኑ ግራ የጋባቸው የሪያድ ነዋሪዎች ቀደም ብሎ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የስራበት በነበረው አሰራር በግል የእለተእለት እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተው እርሳቸውን ለመለወጥ ተስፋ ሰንቀው ከተለያዩ አሰሪ እና ሰራተኛ ደላሎች በከፍተኛ ወጪ የመኖሪያ ፈቃድ ገዝተው ዛሬ ባለዕዳ ሆነው ግራ የተጋቡ ወገኖቻችንን ህጋዊ መሆን የሚያስችላቸውን መላምት ከማፈላለግ ይልቅ ኢትዮጵያውያኑን እንወክላለን የሚሉ ዲፕሎማቶች በኤንባሲው ማህተም በተደገፈ በራሪ ወረቀት እርምጃ እንዲወሰድባቸው እያሰሙ ያለው ጩሀት ወግናዊነት ይጎደልው መሆኑን ያወጋሉ።. ይህን ተከትሎ ኤንባሲው በ 15 ቀን ውስጥ በተከታታይ እርስ በእርሱ የሚጣረዝ የማደናገሪያ ማስታወቂያዎችን በማውጣት ጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን አጭበርብረው መዝግበዋል የሚሉ ምንጮች ታህሳስ 07-2006 «የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን» የሚል ማስታወቂያ ባማወጣት ዲፕሎማቱ የሚፈልጉትን ያህል ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ከመዘገቡ በሃላ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጉዳዮቻቹህ በሂደት ላይ የሚገኝ ወገኖቻችንን ህገወጦች ስለሆናችሁ እጃችሁን በሰላም ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ስጡ የሚል ሌላ ማስታወቂያ በኤንባሲው አርማ እና ማህተም በተደገፈ በራሪ ወረቀት ቅስቀሳ መካሄዳቸው የመንግስት ሹማምንቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ መሽገው በወገኖቻችን ላይ ሲፈጽሙ የከረሙት ውንብድና አንዱ አካል መሆኑንን አስታውቀዋል። . ረ ብ ዕ ምሸት የሳውዲ ጽጥታ ሃይሎች ያደረጉት ፍተሻ በኢትዮጵያ ኤንባሲ ጥቆማ መሁኑንን አክለው የሚገልጹት የመንፉሃ አካባቢ ነዋሪዎች አንምባሳደር መሃመድ ሃሰን ቀደም ሲል ቆጨራ እና ጩቤ የታጠቁ በባህር የመጡ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን መንፉሃ ውስጥ መሽገዋል የሚል የተሳሳተ መረጃ በማስተላለፍ በወቅቱ ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገኖቻችን ሞት ምክንያት መሆኑንን አስታውሰዋል።. 

ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑንን ዲፕሎማቱ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መንፉሃ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እንዲዘምቱ ከሰጡት የተሳስተ መረጃ አናጻር ሳውዲያኑ የጸጥታ ሃይሎች የወስዱት እርምጃ ጥንቃቄ የተሞላበት በመሆኑ ከኤንባሲው የመንግስት ሹመኞች ይልቅ ትላንት በአደባባይ በጭካኔ ሲጨፈጭፉን የነበሩትን ባእዳዊያን ለማድነቅ ተገደናል ብለዋል:: በኢትዮጵያውያን የመንግስት ሹማምንቶች ህገወጥ ተብለው እጃቸውን በሰላም ለሳውዲ ጽጥታ ሃይሎች እንዲሰጡበበራሪ ወረቀት ሲበተንባቸው እና በዲፕሎማቱ ተላላኪዎች ማስጠንቀቂያ እና ማስፈራሪያ ሲደረግባቸው የነብሩ ወገኖች የድንገተኛው አሰሳ ሰለባ እንደነብሩ የሚናገሩ ምንጮች የጸጥታ ሃይሉ በአጭር ግዜ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ ምክሮቻቸውን ለግሰው እንደለቀቋቸው በመግለጽ ህግ ወጡን ከህጋዊ በመለየት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ዕለተ ረብዕ ባካሄዱት ጥንቃቄ የተሞላበት አሰሳ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ብለዋል:: 

 በመጨረሻ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ማምሻውን ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ህጋዊ ለመሆን ጉዳያቸው በሂደት ላይ የሚገኙ ወገኖችን ህጋዊ ማድረግ የሚቻልበትን መላምት እያፈላለግን ነው የሚለው አሰተያየት ሲሰጡ የስሙ ወገኖች ሰሞኑንን «ጉዳያቸው በሂደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ህገወጥ ካደረገው በኤንባሲው ማህተም አርማ ተደግፎ ከተበተነው በራሪ ወረቀት ጋር የሚጋጭ መሆኑንን ያስረዳሉ::  ትላንት ሃሙስ ምሸት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር የመሰብሰቢያ አዳርሻ የዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር ለተሰብሳቢው ካሰሙት ተስፋ ስቆራጭ ንግግር ጋር የሚጣረዝ በመሆኑ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ የሰጡት አስተያየት እርስ በእርሱ የሚጣረዝ መረጃ መሆኑንን በመጥቀስ በዲፕሎማቱ ማሀከል አለመግባባት መኖሩን የሚያሳይ አሊያም ህዝብን ለማደናገር ከቃል የማያልፍ የተለመደ ጩሀት መሆኑንን ይናገራሉ.       የዘውትር ደንበኛችን በውስጥ መስመራችን ያደረሰን  Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment