Saturday, January 4, 2014

ከ318 ሚ. ብር በላይ በሙስና ወንጀል መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉት ሁለት የውጭ ሀገር ዜጐች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ወሰነ


816Ethiopian_Corruption_C_tn
በሙስና ወንጀል የሚፈለጉት የውጭ ሀገር ዜጐች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ተወሰነ፡፡ በኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ግዢ ከሌሎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር በመመሳጠር በፈፀሙት የሙስና ወንጀል፣ መንግስትን ከ318 ሚ. ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉት ሁለት የውጭ ሀገር ዜጐች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ወሰነ፡፡
ባለፈው ማክሰኞ ከፍተኛው ፍ/ቤት ግለሰቦቹ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ የወሰነው በጋዜጣ የተደረገላቸውን ጥሪ አክብረው ባለመገኘታቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ሚስተር ጂሲስ ባራሶይን እና ሚስተር ናሪሽ ቻንድራ፤ በክስ መዝገቡ ከተካተቱት የኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች ከአቶ ሞገስ በላቸው፣ መኮንን ብርሃኔና መስፍን ብርሃኔ ጋር በመመሳጠር ህንድ በሚገኘው “ኮብራ” የተሰኘ ኩባንያቸው አማካይነት ግምታቸው ከ17 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ 3520 አሮጌና የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን ትራንስፎርመሮች አዲስ በማስመሰል ያቀረቡ ሲሆን በዚህም በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ የጥቅም ተካፋይ ሆነዋል ተብሏል፡፡
የሌሎቹ ተከሳሾች ጠበቆች የተረጋገጠ የሰነድ ማስረጃ ለኮሚሽኑ አቃቤ ህግ እንዲያደርሱ፤ አቃቤ ህግዋ ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ባሉት ተከሳሾች በቀረበው የቅድመ ክስ መቃወሚያ ላይ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ያዘዘው ፍ/ቤቱ፤ ለጥር 13 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Source-www.addisadmassnews.com

No comments:

Post a Comment